Get Mystery Box with random crypto!

የ2023 የታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊ የሆነው የ14 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሔማን በቀለ 25,00 | ትምህርት ሚኒስቴር

የ2023 የታዳጊ ሳይንቲስቶች ሽልማት አሸናፊ የሆነው የ14 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ሔማን በቀለ 25,000 ዶላር ተበረከተለት።

በአሜሪካ ቨርጂንያ ነዋሪ የሆነው ታዳጊ ሔማን ሽልማቱን ያገኘው የቆዳ ካንሰርን ለማከም የሚያስችል ሳሙና በመፍጠሩ ነው።

ሳሙናው በአነስተኛ ዋጋ ($.50) ለገበያ የሚቀርብ መሆኑ ተመልክቷል።

"ታዳጊዎች በዓለም ላይ መልካም ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ አምናለሁ" የሚለው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪው ሔማን፤ ለባዮሎጂ እና ቴክኖሎጂ ትምህርት አይነቶች ሁሌም ልዩ ፍላጎት እንደነበረው ይገልፃል።

ውድድሩ የፈጠራ ሃሳቡን ለማውጣትና ውጤታማ እንዲሆን ጥሩ አጋጣሚ እንደፈጠረለት ገልጿል።

ላለፉት አራት ወራት በውድድሩ ለመጨረሻ ዙር ከደረሱ ሌሎች ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ጋር America’s Top Young Scientist ለመባል ብርቱ ፉክክን ሲያደርግ ቆይቷል።

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የፈጠራ ውጤቱን የበለጠ በማበልፀግና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በማቋቋም ሳሙናውን ለሚፈልጉ ሰዎች በአነስተኛ ዋጋ ለማቅረብ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

@News_For_Student
@News_For_Student