Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ ተገለፀ በዐማራ ክል | ትምህርት ሚኒስቴር

በአማራ ክልል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ ተገለፀ

በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መደበኛ ሥራቸው በቅርቡ እንደማይመለሱ፣ የክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አስታውቋል፡፡

የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ የሚገኙ ዐሥሩም ዩኒቨርሲቲዎች፣ የክልሉ ጸጥታዊ ኹኔታ እስኪሻሻል ድረስ ተማሪዎቻቸውን እንደማይጠሩ፣ የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል፡፡

ተለዋዋጭነት ባለው የክልሉ ጸጥታ ምክንያት መንገድ መዘጋቱ፣ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ግጭት ቢነሣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ሓላፊነት መውሰድ ስለማይችሉ፣ እንዲሁም ከምግብ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ያቀርቡ የነበሩ አካላት፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ማስታወቃቸው፣ ለፎረሙ ውሳኔ መሠረት እንደኾኑ ጸሐፊው አስረድተዋል፡፡

ይኹንና ያነጋገርናቸው ተማሪዎች፣ በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲዎቹ ቢጠሯቸው እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡ የተማሪዎቹ ወላጆች በአንጻሩ፣ የፎረሙን ውሳኔ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል ሢል የአሜሪካ ድምፅ ነው የዘገበው።

@News_For_Student
@News_For_Student