Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 66.96 በመቶዎቹ 50 በመቶና ከዚ | ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 66.96 በመቶዎቹ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ተገለፀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በማኅበራዊ ገፁ ባወጣው መልዕክት እንደገፀው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 73.09% በተፈጥሮ ሳይንስ እና 51.38% በማኅበራዊ ሳይንስ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን አሳውቋል።

በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በድረ-ገጽ eaes.et ወይም በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በአገልግሎቱ ድረ-ገጽ ላይ እንዲሁም በትግራይ ትምህርት ቢሮ በአካል በመቅረብ እስከ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ድረስ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተመላክቷል።

በተያያዘ በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል።

ሙሴ ኪዳነ የተባለ የቀላሚኖ ትምህርት ቤት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው ተማሪ መሆኑን ለመመልከት ችለናል።

@News_For_Student
@News_For_Student