Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርት ሚኒስቴር

የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የቴሌግራም ቻናል አርማ news_for_student — ትምህርት ሚኒስቴር
የሰርጥ አድራሻ: @news_for_student
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2
የሰርጥ መግለጫ

ማንኛውንም ማስታወቂያ ለማሰራት ያናግሩን @News_Promotion_Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-11-27 15:12:57
አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 24 እና 25/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በቅጣት መመዝገቢያ ቀን ህዳር 26/2016 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 27/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➢ አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ

@News_For_Student
@News_For_Student
19.1K viewsedited  12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-24 17:15:03
በ2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ህዳር 23/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➢ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናው ኮፒው፣
➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናው ኮፒው፣
➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናው ኮፒው፣
➢ አራት 3X4 ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።

(የዩኒቨርሲቲውን ዝርዝር መልዕክት ከላይ ይመልከቱ።)

@News_For_Student
@News_For_Student
22.5K views14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-20 16:34:51
የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ የመግብያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የተመደቡበትም ዩኒቨርስቲ በ፦
1.Website: https://result.ethernet.edu.et
2.TelegramBot: @moestudentbot ላይ መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

በትግራይ ክልል በኮቪድ ወረርሽኝ እንዲሁም በአስከፊው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ፈተናቸውን መውሰድ ያልቻሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በዚህ ዓመት መፈተናቸው ይታወሳል።

እንደ ክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ፤ ፈተናው ላይ ከተቀመጡት ከ9000 በላይ ተማሪዎች 73.09 በመቶ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እና 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል።

በአጠቃላይ በክልሉ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.2K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-15 13:11:51
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ከታች የተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፦

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ
6. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ

@News_For_Student
@News_For_Student
14.0K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-13 06:54:44
ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም የሁሉም የመጀመሪያ ዓመት (Freshman) ወይም የ2015 ዓ.ም መደበኛ ሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 13 እና 14/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ጥሪው በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ በሪሚዳል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና በ2014 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተርን ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች withdrawal የሞላችሁ ተማሪዎችን ይመለከታል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.9K views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-11 08:37:34
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ማለፊያ ነጥብ በማምጣት በ2016 ዓ.ም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተርን ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች withdrawal የሞላችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የሪሜዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ #ነባር የሪሜዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከህዳር 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም መሆኑን ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የሪሜዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.7K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 13:43:09
ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም (ትምህርት ሚኒስቴር) የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር እና የዩኔስኮ ብሄራዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ከአለም አቀፍ የትምህርት ቢሮ (UNESCO-IBE) ቦርድ ፕሬዝዳንት ስቪን ኦስትቬት ጋር በፈረንሳይ በሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መስሪያቤት የጎንዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የትምህርት ሥርዓት ለማሻሻል እና ለማዘመን ያከናወናቸውንና በመተግበር ላይ ያሉ የለውጥ ተግባራትን አቅርበዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያ በተለይም በዘርፉ በተለዩ የትምህርት መስኮች ላይ የውጭ ልምድ እንደሚያስፈልጋት በአጽናኦት የተናገሩ ሲሆን የዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው የትምህርት ስርዓቱን በአዲስ መልክ ለማሻሻልና ለማዘመን ሚኒስቴሩ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው ቢሮው ጥረታቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.7K views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-09 07:25:14
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ ጦርነት እና በኮቪድ-19 ምክንያት ወደትምህርት ገበታቸው መመለስ ላልቻሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

በተገለፁት ምክንያቶች ወደትምህርት ገበታችሁ መመለስ ያልቻላችሁ የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ማስረጃችሁን ከሚመለከተው ህጋዊ አካል በመያዝ ከጥቅምት 27/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በየትምህርት ክፍላችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

@News_For_Student
@News_For_Student
13.0K views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-08 06:32:47
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለነባር የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ እንዳለስተላለፈ ገልጿል፡፡

የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ጥሪ እስካሁን እንዳልተላለፈ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ፤ ተደጋጋሚ የመግቢያ ቀንን የተመለከቱ ጥያቄዎች በተማሪዎች እየቀረቡለት መሆኑንም አስረድቷል፡፡

በመሆኑም ትክክለኛውን የመግቢያ ጊዜ እስከሚያሳውቅ ድረስ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student
12.9K views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-07 07:49:15
#BuleHoraUniversity

በ2015 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2014 ዓ.ም ትምህርት ጀምራችሁ በአንደኛ ሴሚስተር በውጤትና በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal በመሙላት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ጊዜ ህዳር 01 እና 02/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በተቋሙ ዋናው ግቢ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሂዱ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አድርጓል፡፡

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል፡፡)

@News_For_Student
@News_For_Student
14.3K views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ