Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተጠናቀቀ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አ | ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተጠናቀቀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።

የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ፤ዥ አገር አቀፍ ፈተናው በተያዘለት ዕቅድ እንዲጠናቀቅ ያደረጋችሁ ከፌደራል እስከ ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርሲቲዎች ያላችሁ ተቋሞች፣ የትምህርት ኣመራሮች እና መምህራን፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያላችሁ የፀጥታ እና ደህንንት ተቋሞች እና ኣመራሮች፤ ከተለያዩ ኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጣችሁ ፈታኞች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን "  ብለዋል።

ሃላፊው " ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ተፈታኝ  ተማሪዎቻችን ከናንተ የሚጠበቀው ሁሉ ስለደረጋችሁ ለናንተም የላቀ ምስጋና ይገባቹሃል " ሲሉ አክለዋል። 

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ/ም  ለአራት ተከታታይ ቀናት በትግራይ ክልል ሲሰጥ የቆየውን የ12 ክፍል አገራዊ ፈተና ከ9,000 በላይ ተማሪዎች መፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያሳያል።

ብሔራዊ ፈተናው የተሰጠው በመቐላ፣ አዲግራት፣ አክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ውጤቱን ባጠረ ጊዜ ለማሳወቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@News_For_Student
@News_For_Student