Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ውጤት ቅሬታ ፎርም አሞላል ቅደም ተከተል እንዴት ነው? በቅድሚያ ወደ http: | ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ውጤት ቅሬታ ፎርም አሞላል ቅደም ተከተል እንዴት ነው?

በቅድሚያ ወደ http://eaes.et ግቡ

በመቀጠል እንደተለመደው ሬጂስትሬሽን ቁጥር እና ስማችሁን አስገቡ

ከዚያም ከውጤት ማሳያው ሥር በታች በኩል በአረንጓዴ ቀለም ላይ ያረፈ
submit your complain if any
የሚለውን ተጫኑ


በመቀጠል ከሚመጡት የቅሬታ አይነቶች ውስጥ እናንተ ቅሬታ ማቅረብ የገለጋችሁበትን አንዱን ምረጡ።

የስም ስህተት ፣ የተሳሳተ ፎቶ ግራፍ ፣ የተሳሳተ የትምህርት መስክ (ሶሻል/ናቹራል) ፣ የተሳሳተ ጾታ ፣ የተሳሳተ ውጤት ፣ የተሳሳተ የዕይታ ሁኔታ (ማየት የሚችል/ማየት የተሳነው) ምርጫ እና ሌላ የሚል ይሰጣችኋል።

ለምሳሌ፦

ውጤቱ ላይ ከሆነ ቅሬታ ማቅረብ የፈለጋችሁት  Result problem  የሚለውን ተጫኑ

ከዚያም ከእያንዳንዱ ትምህርት ውጤት ጎን  ቅሬታ መጻፊያ ያመጣላችኋል

ከዚያም ቅሬታ ማስገባት የፈለጋችሁበት የትምህርት አይነት ጋር በመሄድ ቅሬታችሁን መጻፍ እና ስትጨርሱ submit የሚለውን ተጫኑ።

ማስታወሻ

ቅሬታ የምታስገቡት በሥራ ሰአት ቢሆን ይመረጣል።
@News_for_Student
@News_for_Student