Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት እንደሚከተለ | ትምህርት ሚኒስቴር

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡-

1. እንደማንኛውም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ወጪያቸውን በመንግስት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎችን ፈትኖ ይቀበላል፣

2. በአሁኑ ሰዓት በማታው ክፍለ ጊዜ (Extension) በግል እየተማሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች በመደበኛው ክፍለ ጊዜም (Regular) ተመሳሳይ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጠነኛ ክፍያ የሚያስተምር ይሆናል፣

3. ዩኒቨርሲቲው በፊት ከነበረው ከትምህርት ሚኒስቴር ከሚላክለት የተማሪዎች ቅበላ ውጭ በልዩነት ፈትኖ ተማሪዎችን ቢቀበልም ከዚህ በፊት በመንግስት ከሚመደብለት የተማሪዎች ቁጥር ያነሰ አይሆንም፤

4. አዋጁ በግልጽ እንዳስቀመጠው ሁሉንም የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ የትምህርት ተቋም እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል

በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መዳረሻ ፣ የእውቀት መገብያ መናኸሪያ እንዲሆን እንጂ ራስ ገዝ አስተዳደር ያስፈለገው የገንዘብ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ብቻ ተቀብሎ የሚያስተምር ተቋም እንዳይሆን ታስቦ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ይህ ማለት አንድ ተማሪ ወደ ተቋሙ ለመማር አስቦ ሲመጣ እንደማንኛውም ተማሪ ከክፍያው በፊት የተቋሙን የትምህርት መመዘኛ መስፈርቶች (Admission paper) ሲያገኝ ብቻ ይሆናል::

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
@News_For_Student
@News_For_Student