Get Mystery Box with random crypto!

በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይተገበራል | ትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይተገበራል፡፡ -ትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የመንግሥት እና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከዓለም አቀፍና ከውጭ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሁም በትግራይ ክልል በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል እንደሚተገበር ተናግረዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ ከሥራና የተግባር የትምህርት አይነቶች በስተቀር በሁሉም የቀለም ትምህርት ዓይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበር ጠቁመዋል፡፡ በሥራና የተግባር ትምህርት አይነቶች ላይ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል ብለዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ2015 ዓ. ም ጀምሮ መተግበር መጀመሩ ይታወቃል። #MoE

@News_For_Student
@News_For_Student