Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 497 ትምህርት ቤቶች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት | ትምህርት ሚኒስቴር

በአማራ ክልል በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 497 ትምህርት ቤቶች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

በክልሉ በ2015 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ 214,997 ተማሪዎች ምዝገባ ያደረጉ ሲሆን 210,323 ተማሪዎች ወይም 97.8 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

በክልሉ 574 ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ማስፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከነዚህም 497 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹት ኃላፊዋ፤ በ77 ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ የማለፊያውን ነጥብ እንዳለመጣ ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ 60 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት (600 እና በላይ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፤ 500 እና በላይ ለማኅበራዊ ሳይንስ) ማስመዝገባቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student