Get Mystery Box with random crypto!

'በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የያዝነው አቅጣጫ የሚቀጥል ነው። ወደኋላ የምንመልሰው አይደለም።' | ትምህርት ሚኒስቴር

"በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የያዝነው አቅጣጫ የሚቀጥል ነው። ወደኋላ የምንመልሰው አይደለም።"

- የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የትምህርት ዘርፍ ማሻሻያዎች እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አስመልክተው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከኢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

መንግሥት በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የያዘውን አቅጣጫ አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

"የመልቀቂያ ፈተና አሰጣጡን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ይሠራል" ብለዋል።

በዚህም በግንቦት ወር መጨረሻ የሚከናወነው የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ድብልቅ / Hybrid በሆነ መልኩ እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

ፈተናው በከፊል በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአካል፥ በከፊል ደግሞ በኦንላይን (በተለይ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች) የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ፈተናውን መስጠት የመንግሥትን ወጪ ይቀንሳል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህን ለማሳካት ለፈተናው የሚሆኑ ታብሌቶችን የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባም በኦንላይን ይከናወናል ብለዋል።

@News_For_Student
@News_For_Student