Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠ | ትምህርት ሚኒስቴር

ሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን መረጃ በአስቸኳይ እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ተቋማቱ በየፕሮግራሙ ያሉ ተማሪዎች መረጃን እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እንዲልኩ ሚኒስቴሩ ጠይቋል።

በተጠቀሰው ጊዜ መረጃውን የማያሳውቅ የትምህርት ተቋም ተፈታኝ ተማሪ እንደሌለው እንደሚታሰብ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የመውጫ ፈተና በመንግሥት እና በግል ተቋማት በድምሩ 150,184 ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ወስደው 61,054 ተፈታኞች ወይም 40.65 በመቶዎቹ ማለፋቸው ይታወሳል።

(በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጄና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

@News_For_Student
@News_For_Student