Get Mystery Box with random crypto!

በ12ኛ ክፍል ፈተና ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ ጥቅምት 14 | ትምህርት ሚኒስቴር

በ12ኛ ክፍል ፈተና ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ ጥቅምት 14 ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ተገለጸ

በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች፤ የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሰታውቋል።

በልዩ ኹኔታ በአዳማና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር ለሚፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ በመሆኑ፤ ምርጫቸው ውስጥ በማካተት መመደብ እንደሚችሉም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በዚህም መሰረት በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት ለመማር ያለፋ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ድረስ ማስተካከል  እንደሚችሉ ተመላክቷል።

@News_For_Student
@News_For_Student