Get Mystery Box with random crypto!

በ2016 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግ | ትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችው ተማሪዎች፤ የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 03 እና 04/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
- የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሚዛን አማን በሚገኘው ዋናው ጊቢ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ጊቢ

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ ከ9ኛ እስከ 2ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
➢ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣
➢ ዘጠኝ 3 x 4 የሆ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student