Get Mystery Box with random crypto!

በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ201 | ትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ኅዳር 30/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲው አሳውቋል፡፡

አቀባበል ሰኞ ታኅሣሥ 01/2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ታኅሣሥ 02/2016 ዓ.ም እንዲሁም ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ታኅሣሥ 03/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፦
አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ዓባያ ካምፓስ

የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች፦
የስም ዝርዝራችሁ ከ“A” እስከ “S” የሚጀምር በጫሞ ካምፓስ፣ አርባ ምንጭ ከተማ
የስም ዝርዝራችሁ ከ“T” እስከ “Z” የሚጀምር በሳውላ ካምፓስ፣ ሳውላ ከተማ

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➢ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ሁለት ኮፒ፣
➢ ሁለት ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student