Get Mystery Box with random crypto!

#AssosaUniversity በ2015 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታትላችሁ | ትምህርት ሚኒስቴር

#AssosaUniversity

በ2015 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታትላችሁና የማለፊያ ነጥብ ያመጣቹ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችው አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 01 እና 02/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በመሆኑም በተገለፁት ቀናት ብቻ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት በአካል በመገኝት እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች፣
➢ 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

@News_For_Student
@News_For_Student