Get Mystery Box with random crypto!

#AAU በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተ | ትምህርት ሚኒስቴር

#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ታህሳስ 05 እና 06/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በየተመደባችሁበት የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች

ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ከመምጣታችሁ በፊት https://portal.aau.edu.et ላይ በመግባት Freshman የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የግል መረጃቻችሁን እንድታሟሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡-

➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➢ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ፡፡

Note:

በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡

ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት ታህሳስ 08/2016 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ ከታህሳስ 08 እስከ 12/2016 መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦
https://portal.aau.edu.et/ ወይም http://aau.edu.et

@News_For_Student
@News_For_Student