Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.43K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-05 20:00:06
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገልጿል።

#የሁሉም_ነዳጅ_ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በግንቦት ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት :-

1. ቤንዚን ----- ብር 69.52 በሊትር

2. ነጭ ናፍጣ ---- ብር 71.15 በሊትር

3. ኬሮሲን ---- ብር 71.15 በሊትር

4. የአውሮፕላን ነዳጅ ---- ብር 65.35 በሊትር

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ ---- ብር 57.97 በሊትር

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ ---- ብር 56.63 በሊትር

መረጃው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍቢሲ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
6.9K viewsedited  17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 15:58:46 በአዲስአበባ ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ሰዎችን በሀይል የመሰወር ድርጊት ተባብሷል ሲል ኢሰመኮ አስታወቀ

ድርጊቱ በአፋጣኝ ሊቆም እንደሚገባም አሳስቧል!!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከደረሱት አቤቱታዎችና ጥቆማዎች በመነሳት ሲያደርግ በነበረው ክትትል መሠረት በርካታ  የአስገድዶ መሰወርን ድርጊት የሚያቋቁሙ ድርጊቶች መከሰታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በተለይም ይህ አሳሳቢ ሁኔታ በተከሰተባቸው የአዲስ አበባ ከተማ፣ የኦሮሚያ ክልል እና የአማራ ክልል ኮሚሽኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን መንግሥታዊ ኃላፊዎች በማነጋገር፣ በልዩ ልዩ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ቦታዎች በመዘዋወር እና ከቤተሰቦችና ከሌሎች የመረጃ ምንጮች መረጃዎችን ሲያሰባስብ መቆየቱን ብስራት ራዲዮ ከኮሚሽኑ ካገኘዉ መረጃ ተመልክቷል።

አብዛኛውን ጊዜ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ፣ ከሥራ ቦታ ወይም ከመንገድ ላይ የሲቪልና የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታና ደኅንነት ሠራተኞች ያለ ፍርድ ቤት የመያዣ ትእዛዝ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ወዳልታወቀ ስፍራ እየተወሰዱ  እንዲሰወሩ የተደረጉ ሲሆን ፤ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት መሰወር በኃላ የተገኙ መሆናቸው ገለጿል። ሆኖም አሁንም ግን ሌሎች  ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ በግዳጅ እንደተሰወሩ የቀጠሉ ናቸው ብሏል ኮሚሽኑ።

ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል የተወሰኑት ሲያዙ በወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ መሆኑ ተነግሯቸው ወደ መደበኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ የተሰወሩ ሲሆን ከፊሎቹ ደግሞ ምንም ሳይነገራቸው በጸጥታ ኃይሎች ተወስደው የተሰወሩ ናቸው ሲል በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

ለአብነትም በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በማስገደድ ተሰውረው ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ከተለያየ የጊዜ መጠን መሰወር በኃላ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው የተገኙ ሲኖሩ፣ አስገድደው በተሰወሩበት ወቅት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ ገላን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ የቀድሞው ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ ተይዘው እንደቆዩ ለመረዳት ተችሏል። በአስገድዶ መሰወሩ ወቅት ተፈጽሟል ስለተባለ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ ወይም የማሰቃየት ተግባር ኮሚሽኑ ምርመራውን የቀጠለ ሲሆን የምርመራ ሥራው እንደተጠናቀቀ ትክክለኛውን መረጃ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፤ “ይህ አስከፊ የሆነ የአስገድዶ መሰወር ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም መንግሥት አስፈላጊውን ጊዜያዊ እና ዘለቄታዊ እርምጃዎች ሁሉ እንዲወስድ፣ የተሰወሩ ሰዎች ሁሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ፣ በተሰወሩበት ጊዜ ሁሉ የተፈጸሙ ድርጊቶች ላይ የተሟላ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ችግሩ የደረሰበትን አሳሳቢ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ሀገር አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ የሥራ ቡድን በማዋቀር የድርጊቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ማፈላለግ እና ፍትሕን ማረጋገጥ ይገባል” በማለት አሳስበዋል። 

የአስገድዶ መሰወር ወንጀልን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ፤ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስምምነት ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ተቀብላ ልታጸድቅ እንደሚገባም አሳስቧል።

በሌላ በኩል አንድን ሰው የሚገኝበትን ቦታና ሁኔታ ሳይታወቅ በእስር መያዝ ማለት በተለይ በከባድ ወንጀል ተጠርጥሯል የተባለን ሰው ለወንጀል ምርመራ በሚል ምክንያት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ እንዳይገናኝ አድርጎ በእስር የማቆየትን ተግባር ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ናቸው ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.1K viewsedited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:07:22
መቐለ

አምባሳደር ማይክ ሀመር ትግራይ ክልል፣ መቐለ ይገኛሉ።

በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ለመነጋገር ዛሬ መቐለ ገብተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሀመር መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ በትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና በአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በትግራይ ቆይታቸውም በፕሪቶሪያ ስምምነት አፈፃፀም፣በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከክልሉ ቴሌቪዥን በተገኘው መረጃ ፤ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ጋር ​​ተወያይተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.4K viewsedited  10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 12:50:50
በመስኪዶች አካባቢ እያጋጠሙ ያሉ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ተቀራርቦ መነጋገር አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑ ተገለፀ።

በቅርቡ በአንዳንድ አካባቢዎች መሰኪድ ፈርሷል በሚልየተፈጠረዉንችግር ከሚመለከተው አካል ጋር ተቀራርቦ ለመነጋገርና የጋራ መፍትሄ ለማበጀት በፌዴራል እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት አማካኝነት የተቋቋመ ኮሚቴ ከኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዷለም ጋር ተወያይቷል።

በውይይት መድረኩ ላይ ከፌዴራል መጅሊስ ፣ ከአዲስ አበባ መጅሊስ እና ከኦሮሚያ መጅሊስ የተወከሉ የሐይማኖት አባቶች በሰላም ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተገኙ ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማው ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተገኝተዋል።

በተለይ በመስኪዶች አካባቢ ላጋጠመው ችግሮች ከሚመለከተው የትኛውም የመንግስት አካል ጋር በመነጋገር መፍትሄ ለማመንጨትና ችግሩንም በዘላቂነት ለመፍታት ታስቦ የተቋቋመ ኮሚቴ መሆኑን ከመጅሊስ ተወክለው የመጡት አመራሮች ገልፀዋል።

መስኪዶች በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ፈርሰዋል በሚል ምክኒያት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሁለት መስኪዶች ላይ በሁለት የጁምዓ ሶላት ቀናት አመፅ ለመቀስቀስ ሞክረዋል። እነዚህ አካላት በቀሰቀሱት ግጭት ምክኒያት የንብረትና የአካል ጉዳት እንዲሁም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። ይህ አላስፈላጊ ጉዳት መድረሱ በፍፁም አግባብ እንዳልነበረና ከመፈጠሩ በፊት ሊወገድ የሚችል ችግር እንደነበር በዚህ ውይይት ላይ ለመግባባት ተችሏል።

የመጅሊስ ተወካይ የኮሚቴው አባላት በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለፁት ለሚፈጠሩ ማንኛውም ችግሮች ተቀራርቦ መነጋገርና መወያየት መፍትሄ ያመጣል ብለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለፁት የሐይማኖት ተቋማት የሰላም ዘብ እንዲሁም ግንባር ቀደም የሰላም ጠበቃዎችም ናቸው ያሉ ሲሆን፣ የትኛውንም ችግር መፍታት የሚቻለው በንግግርና በውይይት ብቻ መሆን አለበት ብለዋል።

የተፈጠሩት ችግሮች ከሀይማኖቱ አባቶች እና ከመንስት አቅም በታች በመሆናቸው ይህ ኮሚቴ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር በቅርበት መነጋገር መጀመሩ የሚበረታታ ነው ያሉት አቶ ብናልፍ አፋጣኝ መፍትሄም እንደሚያስገኝ እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል

ይህ ኮሚቴ ለዚህ ወቅታዊ ችግር መፍትሄ በጋራ ማፈላለግ ዋነኛ ተልዕኮው ነው ያሉት አቶ ብናልፍ በዚህ አላስፈላጊ ግጭት ምክኒያት ያጋጠሙ ጉዳቶችና ጥፋቶች ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።
7.5K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:14:44
ሩሲያ ምዕራባዊያን ለዩክሬን F-16 የጦር ጀት አውሮፕላን ከሰጡ የከፋ ጉዳት እንደሚገጥማቸው አስጠነቀቀች።

የቡድን ሰባት ሀገራት ጉባኤ በጃፓኗ ሂሮሽማ በመካሄድ ላይ ሲሆን የዩክሬን ጉዳይ ዋነኛ መወያያ አጀንዳ ሆኗል።ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በውይይቱ ላይ የተገኙ ሲሆን የቡድን ሰባት አባል እና ሌሎች ሀገራት የሩሲያን ጥቃት ለመመከት F-16 የተሰኘውን የጦር አውሮፕላን እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።

አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት ለዩክሬን F-16 የተሰኘውን ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን ለመስጠት ከስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው ተገንጿል።
ሀገራቱ የዩክሬንን ወታደሮች ለማሰልጠን የስልጠና ፕሮግራም ስለማውጣታቸው ሮይተርስ ዘግቧል።

ሩሲያ በበኩሏ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የጦር አውሮፕላኑን ከሰጡ የከፋ ጉዳት እንደሚደርስባቸው አስጠንቅቃለች።የሩሲያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አሌክሳንደር ግሩሽኮ እንዳሉት የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን F -16 የጦር አውሮፕላንን ከሰጡ ጦርነቱን ከማባባስ እና ከማወሳሰብ ውጪ መፍትሔ አያመጣም ብለዋል።

ዩክሬን ከወራት በፊት ጀምሮ F -16 የጦር አውሮፕላን እንዲሰጣት ስትወተውት የነበረ ቢሆንም ጥያቄው ውድቅ ሲደረግባት ቆይቷል።የኔቶ አባል ሀገራት የዩክሬንን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉት F-16 የጦር አውሮፕላንን ብንሰጥ ጦርነቱ ዩክሬንን አልፎ ወደ ሌሎች ሀገራት ይስፋፋል በሚል ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.6K viewsedited  18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 19:31:42 በተሽከርካሪ ታግዘው የሞባይል ስልክ ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 25 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ከተጠርጣሪዎቹ 6ቱ ሴቶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ “ሿሿ” ብለው በሚጠሩት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር እንደሚቆጥቡ በምርምራ ደርሼበታለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።

ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ሁለት ሚኒባስ ታክሲዎች እንዲሁም ለወንጀል ሥራቸው የሚጠቀሙባቸውን 4 ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን መያዙን ፖሊስ ገልጿል።

በተጨማሪም 14 ዘመናዊ ሞባይል ስልኮች እና ገንዘብ ስለመገኘቱም የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያስረዳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
6.7K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 15:57:09
Update

በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ቁጥር 20 ደረሰ

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራክ አደረጋ ህይወታቸው ያለፈ የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ብዛት 20 መድረሱ ተገለጸ።
መምህራኑን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሸከርካሪ ጋረ ዋሻ በተባለ አካባቢ መንገዱን ስቶ ገደል ውስጥ በመግባቱ እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉንም የመደ ዋለቡ ዩኒቨርሲቲ ፕረተዝዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ተናግረዋል።

ህይወታቸው ካለፈ መምህራን በተጨማሪም 20 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳጥ መድረሱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
የሞቱት መምህራን ከፍተኛ ልምድ እና በመማር ማስተማር ላይ ብዙ ልምድ ያላቸው ናቸው ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.0K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 13:16:10
አሳዛኝ ዜና

በትራፊክ አደጋ 15 የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ህይወታቸው አለፈ

15 የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን ህይወት ማለፉን ገልፀዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.5K viewsedited  10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 08:00:49
የሱዳን ጦር መሪ አል ቡርሃን ተቀናቃኛቸዉንና ምክትላቸው ዳጋሎን ከስልጣን አነሱ

የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ምክትላቸውን እና የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች (RSF) አዛዥ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቱ በመባል የሚታወቁትን ከስልጣናቸው አሰናብተዋል፡፡

ጄኔራል ቡርሃን እና ሄሜቲ ከጥቅምት 2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ የገዢው ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር እና ምክትል ሆነው አገልግለዋል።ጀነራል ቡርሃን በዛሬዉ እለት በተለቀቀው አዋጅ የቀድሞ የአማፂ ቡድን መሪ የነበሩትን ማሊክ አጋርን ምክትል አድርገው ሾመዋል።

ማሊክ አጋር የሱዳም ሉዓላዊው ምክር ቤት አባል ናቸው።የሉዓላዊው ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አዋጁ በአስቸኳይ እንዲተገበር መመሪያ ሰጥቷል።የጦር አዛዡ አል ቡርሃን ባለፈው ወር የአርኤስኤፍን ቡድን እንዲበተን በማድረግ ተዋጊዎቹን በአማጺነት ከፈረጀ በኃላ በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የስልጣን ሽኩቻ ተፈጥሯል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.8K viewsedited  05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 07:05:20 አጫጭር ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ምክር ቤት የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት በትግራይ ክልል ያቋረጡትን የዕርዳታ ሥርጭት እንዲቀጥሉ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ምክር ቤቱ ከትግራይ የዕርዳታ እህል መዘረፉን ማረጋገጡን ገልጦ፣ "የዕርዳታ ሥርጭት ተቋርጦ መቀጠሉ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል" ብሏል። ምክር ቤቱ፣ ፌደራልና የክልሉ መንግሥት በዕርዳታ ዝርፊያው ላይ ምርመራ አድርገው አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርጉም ምክር ቤቱ አሳስቧል። ሁለቱ ድርጅቶች ባለፈው ወር የዕርዳታ ሥርጭት ያቋረጡት፣ በክልሉ የዕርዳታ እህል ተዘርፎ ገበያ ላይ እንደተሽጠ ደርሰንበታል በማለት ነበር።

2፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ "የኤርትራ ሠራዊት የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ስምምነት ተቆጣጣሪ ሥራን እያደናቀፈ ነው" በማለት መክሰሳቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጌታቸው ይህን የተናገሩት፣ በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ዙሪያ ለተቆጣጣሪ ቡድኑ በሰጡት ገለጻ መኾኑን ዘገባው ጠቅሷል። የተቆጣጣሪ ቡድኑ ሃላፊ ሜጀር ጀኔራል ስቲፈን ራዲና፣ ቡድናቸው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውጭ ሌሎች ኃይሎች ይኑሩ አይኑሩ ለማጣራት በቀጣዩ ወር ደቡባዊና ምዕራብ ትግራይን እንደሚጎበኝ መናገራቸውን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
 
3፤ ዓለም ባንክ የኢትዮጵያ መንግሥት ለአገሪቱ ችግሮች ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን የሚያሰፍኑ መፍትሄዎችን እንዲያመጣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። በመላ አገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መኾኑን የገለጠው ባንኩ፣ የሰላም ግንባታ፣ የእርቅና ዘላቂ ልማት መርሃ ግብሮችን መደገፉን እንደሚቀጥል ገልጧል። ባንኩ ድጋፍ የሚደግፋቸው ዘርፎች፣ የሁሉንም ሕዝብ ፍላጎቶች የሚመልሱ ስለመኾናቸውና ከመድልዖ የጸዱ፣ በሕዝባዊ ምክክርና አሳታፊነት ላይ መመስረታቸውን፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት መስፈኑን በቅድሚያ እንደሚያረጋግጥ አመልክቷል። ባንኩ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ የምግብ ዋስትና፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ ሴቶችን ማብቃትና የማኅበራዊና የአካባቢ ጥበቃ የመሳሰሉ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በማገዝ ላይ እገኛለኹ ብሏል።

4፤ ዘንድሮ ከጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ወደ ብሄራዊ ባንክ የገባው የወርቅ ምርት በከፍተኛ መጠን መቀነሱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር፣ ከቤንሻንጉል ለባንኩ የገባው ወርቅ በ1 ሺህ 400 ኪሎ ግራም እንዲሁም ከጋምቤላ የገባው በ900 ኪሎ ግራም መቀነሱን ዘገባው አመልክቷል። ከሁለቱ ክልሎች የሚገባው ወርቅ የቀነሰው፣ የሕገወጥ ንግድ በመስፋፋቱ እንደኾኑ ተገልጧል። መንግሥት የወርቅ ሕገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር በቅርቡ ግብረ ኃይል ማቋቋሙ ይታወሳል።

5፤ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ጠቅላላ ጉባኤው ተስተጓጉሎበት የነበረው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በቀጣዩ ዕሁድ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤውን ሊያካሂድ መኾኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤውን የሚያካሂደው፣ በኢትዮጵያ ሆቴል አዳራሽ መኾኑን ገልጧል። ምርጫ ቦርድ ባልደራስና እናት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔያቸው በጸጥታ ኃይሎች መሰናከሉን አውግዞ፣ የራሱን አዳራሽ ለፓርቲዎቹ እንደሚፈቅድ ገልጦ ነበር። [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.2K views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ