Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.46K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-20 07:04:30
በስራ ቱርክ ሀገር መሄድ የምትፈልጉ

Marvel Educational Consultancy  ፍላጎታቹን በአጭር ጊዜ አብረን እናሳካ ይላችኋል።

በዚህ ወሳኝ እድል ተጠቅመው ህልማችሁን አሳኩ።

ያለምንም ቅድመ ክፍያ

ለበለጠ መረጃ:

0916860674
0948715848

አድራሻ: ሀዋሳ አቶቴ መ/ኢየሱስ ቸርች ጎን
አዲስ አበባ: 22,  ፌስቲቫ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
7.1K views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 07:04:30 መርጌታ ዮሐንስ ባሕላዊ መድሀኒት ቀማሚ ባሉበትሆነዉመጠቀይችላሉ ቦታዉ እሩቅነዉ ካገርዉጭነኝብለዉእዳይጨነቁ  ያስታዉሱ
በ0921807274ደዉለዉመጠየቅይችላሉከምንሰጣቸዉአገልግሎቶች በጥቂቱ
1, #መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
2, ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
3,  ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
4,ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
5, ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
6, መስተፋቅር
7 ;ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
8,ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
9, ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
10, የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
11,ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
12; መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
13, መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
14, ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
15, ለበረከት
16,ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
17,ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
18,ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
19,ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
20, ለሙግት
21,ለሰላቢ
22,ለስንፈት ወሲብ
23,ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
24, ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
25,ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
26, ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)
27,መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)
28,ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)
29, ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)
30;ለአዙሪት
31; ለአስቸጋሪና ተመላላሽ ሲህር
32;ለሪህ በሽታ
33;ለጉልበት ድርቀት
34;የወገብ ህመም
35;የከረመ ደረቅ ሳል
36;ለደም ግፊት
37;የከፋ የሆድ ድርቀት
38;በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው
39;የአእምሮ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ከሰው  መገለል፣እንቅልፍ ማጣት
40;ክብደት ለመቀነስ
41;የእንቅርት በሽታ
42; የሳይነስ ህመም
43;የሆድ ድርቀትና የሆድ ህመም
44;የወር አበባ ችግር ካለ
45;ውጥረትና የአእምሮ ጭንቀት
46;ለከፍተኛ ራስ ምታት
47;ማስታወስ፣ንቃት፣ተነሳሽነት ለሌላቸው
48;ለድምፅ መታፈን
49;ከአጫሽነት ለመላቀቅ
50;ራስን ስቶ በስቃይ ለሚኖር
0921807274 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም አካውንታችን  Https://, @yohans63
7.7K views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 19:15:57 በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሰላሳ በላይ ወረዳዎች እጅግ አስከፊ በሆነ የሰላም ችግር ውስጥ መሆናቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደኣ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ይህን ያሉት የትውልድ አካባቢያቸው እና በፓርላማ ወደ ወከላቸው ሰሜን ሸዋ ዞን ሰላሌ በማቅናት ከሕዝቡ ጋር ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ሕዝቡ አለበት ያሉትን ሰቆቃ አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት መረጃ ነው፡፡

በተፈጠረው የሰላም እጦት በተለይም በገጠራማ አካባቢ የሚገኙ የጤና ጣቢያዎች እና የጤና ኬላዎች በመዘጋታቸው ወላድ እናቶች እንዲሁም የሰው ልጅ ሕይወት በሕክምና እጦት እየጠፋ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ከ98 በላይ የሚሆኑ አንደኛ እና ኹለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመዘረፋቸው እንዲሁም ንብረቶቻቸው በመውደሙ፤ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የመማር ማስተማር ሂደቱ መቆሙን ገልጸው፤ ከ55 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በዞኑ ባሉ በርካታ አካባቢዎች ላለፉት ሦስት እና አራት ዓመታት በነበረው የሰላም ችግር እና አለመረጋጋት የውሃ፣ የመብራት እንዱሁም የመንገድ መሰረተ ልማቶች እንደሌሉም አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም በኦሮሚያ ክልል ባሉ በርካታ ሥፍራዎች መሰል ችግሮች ቢኖሩም የዚህን ዞን ለየት የሚያደርገው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተፈናቀሉ፣ እየተገደሉ፣ እየተዘረፉ እና እየተሰቃዩ ድምጽ የሚሆናቸው አካል መጥፋቱ እና ያሉበትን ችግር ተረድቶ እልባት የሚሰጥ አካል አለመኖሩን ነው ብለዋል፡፡

በተለይም በዞኑ በሚገኙ እንደ ኩዩ፣ ደገም፤ ደራ፣ ግራር ጃርሶ፣ ያያ ጉለሌ፣ ደብረሊባኖስ፣ ዋጫሌ እና ጅዳ በመሳሰሉ ወረዳዎች ሕዝቡ ያለበት ሰቆቃ እጅግ አስከፊ ነው ያሉት ታዬ ደንደኣ፤ መንግሥት ባስቸኳይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የሕዝቡን ሰላም እንዲያስጠብቅ ጠይቀዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.5K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 11:49:49
#ማስታወሻ
የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ማጠናቀቂያ ጊዜ ተገልጿል!!

በ2014 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በልዩ ኹኔታ በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተና ተዘጋጅቶ እንዲላክና አጠቃላይ ሂደቱ እስከ ሰኔ 30/2015 ድረስ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታውቋል።

ፈተናውም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተሰጠው ትምህርት መሠረት ከማዕከል በጋራ ተዘጋጅቶ ለተቋማት መላክ እንዳለበት አመላክቷል።

በዚህም መሰረት በሴሚስተሩ በተሰጠው ትምህርት የተቋማት የውስጥ ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንደሚያዝ ተገልጿል።

ተማሪዎችም በ2016 ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ ሆነው ለመገኘት የኹለቱ ድምር አማካይ 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስቴሩ አመላክቷል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ፈተናውን በማስተዳደርና ውጤት በመግለጽ በ2016 የፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ለይተው እስከ ሰኔ 30/2015 እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ሥራ በማጠናቀቅ የ2016 የትምህርት መርሐ ግብር የተስተካከለ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.4K viewsedited  08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 08:22:30
የአማራ ክልል ከዚህ ቀደም የሚያነሳቸው “የማንነት እና የወሰን፣ የተዛባ ትርክት፣ የህገ መንግስት ማሻሻል፣ ዜጎች በየትኛውም አካባቢ መብታቸው ተጠብቆ መኖርን” የተመለከቱ ጥያቄዎች፤ “በውል እንደገና መመርመር እና መፈተሽ” እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለእነዚህ ጥያቄዎች “መውጫ መንገድ ማስቀመጥ ይገባል” ብለዋል።

ዶ/ር ይልቃል ይህን ያሉት፤ የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተካፈሉበት ኮንፈረንስ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 10፤ 2015 በባህር ዳር ከተማ በተጀመረበት ወቅት ባሰሙት ንግግር ነው። “በአማራ ክልል ያደሩ፣ የነበሩ እና ትግል እየተካሄደባቸው ያሉ ጥያቄዎች አሉ” ያሉት ርዕስ መስተዳድሩ፤ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ የክልሉን ህዝብ ጥያቄዎች ለማስመለስ “በሂደት ላይ የሚገኝ” መሆኑን ለኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።(ኢትዮጵያ-ኢንሳይደር)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.8K viewsedited  05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 07:20:08
Unleash the Future of AI with The AI Insider's BTC Giveaway !

(Participate)

The AI Insider is giving away $2000 in Bitcoin. This is not just for the win, but to help you stay ahead in the AI world.

Here's how you can participate:
Find the link to the giveaway on The AI Insider’s Telegram post (here) and then, pursue to follow the page. 
Engage in 7 simple tasks related to their community. Each task you complete increases your chances to win. 
   
Remember, this opportunity is not just about the Bitcoin. It's about being part of something bigger, exploring the future of AI.  
Giveaway ends May 22nd, so why wait? Join The AI Insider community today and let's shape the future together.

Bonus: Complete all tasks and watch your odds skyrocket! Participate (here)
8.8K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 20:12:25
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ተፃፈ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ ፃፈ።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፤በደብዳቤው በሸገር ከተማ እያፈረሱ ስላሉ መስጂዶች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል።

" በቅርቡ በአዲስ መልኩ' ሸገር ከተማ ተብሎ ' በተመሠረተው ከተማ ህገወጥ በሚል በርካታ መስጂዶች በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት እየፈረሱብን ይገኛል " ያለው ምክር ቤቱ በመስጅዶች ፈረሳ ጉዳይ ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጋር በስልክ በመነጋገር መፍትሄ ላይ እንደደረስን ብናምንም የከተማ አስተዳደሩ ግን በረመዳን ወር ለጊዜው የመስጂዶች ፈረሳውን እንዲቆም በማድረግ ከረመዳን በኋላ የመስጂዶች ፈረሳ በአዲስ መልክ በብዛት ቀጥሏል "ሲል ለጠ/ሚኒስትሩ በፃፈው ደብዳቤ አመልክቷል።

በመሆኑም የመስጂዶች ፈረሳ ጉዳይ በከተማ አስተዳደሩ" ህገ-ወጥ "ስለተባለ ብቻ በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን የህዝበ ሙስሊሙ የኃይማኖት ዋነኛ ህልውና በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ደብዳቤ ብንፅፍም እስካሁን ምላሽ አላገኘም ብሏል።

" በስልክም በጉዳዩ ላይ ለመነጋጋር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም "ሲል አክሏል።

"ተጨማሪ መስጅዶች የማፍረስ ተግበሩ ለክልሉ ፕሬዜዳንት ደብዳቤ ከፃፍንና በጉዳዩ ላይ በአካል በመገናኘት ለመነጋገር ቀጠሮ እየጠየቅን ባለንበት ወቅት መስጅዶች እየፈረሱ መሆኑ የጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችን እንዲሁም ሕዝበ ሙስሊሙም በእጅጉ አሳዝኗል"ብሏል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በደብዳቤው ፥ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፤እንደ ጠቅላይ ሚኒስተርና እንደ የብልጽግና ፓርቲ መሪ ለመስጂዶች ፈረሳ ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሄ የመስጠት ሙሉ ስልጣኑ እንዳላቸው በማመን ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
10.1K viewsedited  17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 19:29:01
የፌደራል መንግስት “ደመወዝ የመክፈል ጫና ውስጥ ለገቡ” ክልሎች፤ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩን የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ

የገንዘብ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፤ ትላንት ረቡዕ ግንቦት 9፤ 2015 ከተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ነው። የሚመሩት የሚኒስቴር መስሪያ ቤትን የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለማቅረብ በፓርላማ ለተገኙት አቶ አህመድ ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል፤ ክልሎች የገጠማቸውን የበጀት እጥረት የተመለከተው አንዱ ነበር።

ጥያቄውን በንባብ ያቀረቡት ዶ/ር ሚልኪያስ አየለ የተባሉ የቋሚ ኮሚቴው አባል፤ ክልሎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀመር መሰረት በጀት የሚደለደልላቸው መሆኑን አስታውሰዋል። ሆኖም “አንዳንድ ክልሎች” “ቀድሞ በነበረ የማዳበሪያ እዳ ምክንያት” የተደለደለላቸው በጀት “ሙሉ ለሙሉ እንዳማይተላለፍላቸው” ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ክልሎቹ “ደመወዝ መክፈል እንኳ እንዳልቻሉ” የጠቀሱት የፓርላማ አባሉ፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ችግር ለመፍታት “ከአጭር ጊዜ አኳያ ምን አስቧል?” ሲሉ ጠይቀዋል።

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ፤ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ክልሎች ደመወዝ የመክፈል ጫና” ውስጥ መግባታቸውን አረጋግጠዋል። ይህ ችግር በተለይም በአዲስ ክልሎች ውስጥ የሚታይ ቢሆንም “አንዳንድ ነባር ክልሎችም ጭምር” ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አንስተዋል።

ሚኒስትሩ “ደመወዝ የመክፈል ጫና ውስጥ ገብተዋል” በሚል የጠቀሷቸው፤ ደቡብ፣ ሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎችን ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.1K viewsedited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 15:02:48
በአዲስ አበባ አንድ እቁላል ከ14 ብር እስከ 16 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

-‹‹ለእንቁላል ጣይ ዶሮ መኖ በኩንታል ከ 3 ሺህ 680 እስከ 4 ሺህ ብር ወጪ እያስደረገን ነው››--- የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር

በመኖ መወደድ እና ከዚህ ቀደም ተከስቶ በነበረው ወረርሺኝ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶሮዎች መሞታቸው አብዛኛው ዶሮ አርቢ አባላትን ዘርፉ ውስጥ እንዳይቆዩ እያደረጋቸው መሆኑ ተገልጧል፡፡

ይህን ያለው የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር ነው፡፡የማህበሩ ምክትል ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣የመኖው መወደድ የእንቁላል ዋጋ ከዚህም በላይ ከፍ እንዲል ሊያደርገው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።

ሬዲዮ ጣቢያው ባደረገው ቅኝት በአማካይ የ1 እንቁላል ዋጋ ከ 14 ብር አስከ 16 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡አንድ እንቁላል ጣይ ዶሮ ከምታስገኘው ገቢ 75 ከመቶዋ ወጪዋ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ጨምረውም ቀደም ሲል " ዶሮ እና የዶሮ ውጤቶችን ያለ ስጋት መጠቀም ይቻላል " የሚል ትዕዛዝ አስከተሰጥበት ቀን ድረስ በነበረው ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶሮዎች መቀበራቸውን እና ብዙ አርቢዎችም ላይ ኪሳራ ማስከተሉን ተናግረዋል።

በማህበሩ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት 125 አርቢ አባላት መኖራቸውንም ተሰምቷል። ዘርፉ በባንክ በብድር ቢደገፍ ፣ እውቀቱ እና ማምረቻ ቦታው ለወጣቶች በመስጠት ቢታገዝ ፣ ገበሬው ደግሞ በማርባቱ ሂደት በብዛት ቢቀላቀል መሻሻል ሊኖረው ይችላልም ብለዋል፡፡

Via Ethio FM

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.7K viewsedited  12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 09:46:52
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላት ያሉት የአማካሪ ኮሚቴ አቋቋመ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 35 አባላትን ያቀፈ የአማካሪ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከኮሚቴው አባላት ጋር የትውውቅ መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በኮሚቴው እንዲካተቱ የተጋበዙ ግለሰቦች በተለያየ መልኩ ለኮሚሽኑ ስራዎች ድጋፍ የሚያደርጉ እንዲሁም በተለያየ ልምድ እና ሙያ ውስጥ መኖራቸውን ተገልጿል።

አባላቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን እንዲሁም በምክክር ሂደት ላይ ስራዎችን ያከናወኑ ግለሰቦች እና የተቋማት ተወካዮች መሆናቸውም ተጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ይህንን ኮሚቴ ሲያቋቋም በተቋቋመበት አዋጅ 1265/2014 ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎችን መሰረት በማድረግ መሆኑን ጠቅሶ ለኮሚቴው ስራዎችን የሚያከናውንበትን የውስጥ መመሪያ ማዘጋጀቱንም አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በኮሚሽኑ የተከናወኑ ዋና ተግባራትን እና በቀጣይ ሊሰሩ የታቀዱ ስራዎችን በተመለከተ ለኮሚቴው አባላት ገለፃ ማድረጋቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.6K viewsedited  06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ