Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.43K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-27 18:42:49
NewsAlert

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በአማራ ክልል የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኾኑት ግርማ የሺጥላ ዛሬ "በነውጠኛ ጽንፈኞች" መገደላቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ዐቢይ በዚኹ መልዕክታቸው፣ "በሐሳብ የተለየን ኹሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሳት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው" ብለዋል።

ግድያው "አስነዋሪና አሰቃቂ" መኾኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ካልተወገደ "ወደመጨራረስ እንደሚወስደን ጉልህ ማሳያ ነው" በማለትም ድርጊቱን አውግዘዋል።

ግርማ ዛሬ የተገደሉት በተወለዱበት አካባቢ መኾኑንም ዐቢይ ጨምረው ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.0K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 13:00:36
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኞች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አሳስቧል።

በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችን " ከነገ በኋላ አላስተናግድም " ሲል አሳውቋል።

የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ከምዝገባው መጠናቀቅ በኃላ ይፋ ይደረጋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ ተፈታኞች እስካሁን ድረስ የመፈተኛው ቀን ይፋ #አለመደሩግን በማወቅ ከሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ በተጋጋ መንፈስ ዝግጅታቸሁን አድርጉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.1K viewsedited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 10:35:25
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልዕክት

በሱዳን ለዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እየተሰጠ ነው!

በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኝበት አካባቢ የውጊያ ቀጠና በመሆኑ ፣ በአካባቢው የመብራት አገልግሎት በመቋረጡ፣የምግብ ቁሳቁስ ለማግኘትም ሆነ ከኤምባሲ ወጥቶ ለመግባት ስላልተቻለ በዚህ ሁኔታ ዜጋን መርዳት ስለሚያዳግትና የዲፕሎማቶች ህልውናም አደጋ ላይ ስለሚወደቀ በኤምባሲው የተወሰኑ ሰራተኞች እዲቀሩ ተደርጎ አምባሳደሩን ጨምሮ ቀሪዎቹ ደግሞ ከገዳሪፍ ስራቸውን እያከናውኑ ይገኛሉ።ለዜጎች ሊደረግ የሚችለው ድጋፍም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.5K viewsedited  07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:31:20
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me
0909255008
0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ ቤተሰብ ይውኑ
https://t.me/used_phone_ethiopian
301 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 07:18:52 ኢጋድ የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተወካዮች ታንዛኒያ ዛንዚባር ውስጥ ንግግር መጀመራቸውን መግለጡን ሮይተርስ ዘግቧል። ኢጋድ የኹለቱ ወገኖች ንግግር ወደ ፖለቲካዊ ስምምነት ያመራል ብሎ እንደሚጠብቅ ቃል አቀባዩ ኑር መሐመድ ሼክ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሮይተርስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክሎ የሚደራደረውን ቡድን የሚመሩት የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን መኾናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ሰምቻለሁ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
3.1K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 21:48:25
በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌሎች አራት ኢትዮጵያዊያን የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ ለሞት እና ለመቁሰል አደጋ የተዳረጉት፣ በተባራሪ ጥይት እና ከባድ መሳሪያ አረሮች ፍንጣሪ ሳቢያ መኾኑን ኢምባሲው መግለፁን ዘገባው አመልክቷል።

ከአገሪቱ መውጣት የሚፈልጉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በአውቶብስ ወደ መተማ ለመሸኘት እየመዘገበ መሆኑን ኤምባሲው መግለፁን የጠቀሰው ዘገባው፣ የኤምባሲው ሠራተኞች ካርቱምን ለቀው ለኢትዮጵያ ቅርብ በሆነችው የሰሜን ሱዳኗ ገዳሪፍ ከተማ ሥራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.6K viewsedited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 15:54:25
በክልሎች የሚካሄደው የሽግግር ፍትሕ ምክክር መድረክ ከሚያዝያ እስከ ነሐሴ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ተገለጸ

በክልሎች የሚካሄደው የሽግግር ፍትሕ ምክክር መድረክ በ58 ከተሞች ከሚያዝያ እስከ ነሐሴ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ ሲስተዋሉ ከቆዩ ችግሮች በመነሳት ሙሉ ፍትሕ የሚሰጥበት፣ ዘላቂ ሰላም፣ እርቅና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አውስቷል፡፡ የሽግግር ፍትሕ ስርዓትን ስኬታማ ለማድረግም ሒደቱን በተሟላና በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር የሚያስችሉ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸው ነው የተጠቆመው፡፡

በዚህ ረገድ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማርቀቅ ስራ ለመጀመር የሚያስችለው የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ አማራጮች መነሻ ሰነድ ሚኒስቴሩ ባደራጀው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን መጠናቀቁ ተጠቅሷል፡፡ በክልሎች ደረጃ የሚካሄደው ምክክር በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ 58 ከተሞች ከሚያዝያ እስከ ነሃሴ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ለማከናወን መርሐ ግብር መውጣቱ ተገልጿል፡፡

የመጀመሪያ ምዕራፍ በቅርቡ በአዳማ ከተማ የተካሄደ ሲሆን ÷በዚህም ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚወክሉ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላት በከፍተኛ ንቃት እና የባለቤትነት ስሜት ተሳትፈዋል፡፡ በመድረኩ የፖሊሲ አማራጭ ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችል ሰፊ ግብዓት የማሰባሰብ ስራ መከናወኑም ተጠቁሟል፡፡

መድረኩ በቀጣይ ሁለት ሣምንታት በ15 የተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እንደሚካሄድም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.8K viewsedited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 20:07:33 የነዳጅ ክፍያን በሲቢኢ ብር እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል ይቻላል፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ደንበኞች የነዳጅ ክፍያዎቸውን በሲቢኢ ብር እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ የተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የባንኩ ደንበኞች በሲቢኢ ብር አማካኝነት በማንኛውም የስልክ አይነት፣ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች መክፈል እንደሚችሉ እና ለዚህም ዲጂታል ደረሰኝ እንደሚያገኙ ገልጿል።

ባንኩ ይፋ ባደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚቻልም ተጠቅሷል፤ ይህ መተግበሪያም ከደንበኞች የቁጠባ ሐሳብ ጋር የሚገናኝ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ባንኩ ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና በቀላሉ የነዳጅ ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ ‘ሲቢኢ ብር’ እና ‘ነዳጅ’ መተግበሪያ ለዚህ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ደንበኞች እነዚያን አገልግሎት በመጠቀም ተጠቃሚ እንዲሆኑም አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በሪኦ ሀሰን የነዳጅ ክፍያ በዲጂታል መከናወኑ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

Via:- EBC

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.7K viewsedited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:12:31
ራያ ፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸዉን መመዝገብ ጀመሩ

የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የመማር ማስተማር ስራቸዉን አቋርጠዉ የነበሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ዳግም ትምህርት ለመጀመር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን አስታዉቀዋል።ከነዚህም ዉስጥ የራያ ፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎቻቸዉ ጥሪ ማቅረባቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በአክሱም ዩኒቨርስቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና 4ኛ አመት ተማሪ የሆነዉ በርናባስ የሺጥላ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገረዉ ፤ ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ ለዩኒቨርስቲው መረጃ እንደሰጡ እና የኦንላይን ምዝግባ መከናወኑን ገልጿል። ዩኒቨርስቲው ባወጣዉ ማስታወቂያ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዉ ትምህርታቸዉን ከሚከታተሉ ተማሪዎች ዉጭ ሁሉም ተማሪዎቹ ምዝገባዉን እንዲያከናዉኑ ጥሪ አድርጓል።

ከሁለት አመታት በላይ ከትምህርት የራቀዉ በርናባስ ፤ ያሳለፋቸዉ ግዚያት ተስፋ አስቆራጭ የነበሩ ቢሆንም ዳግም ትምህርት ለመጀመር ተስፋ ማድረጉን ተናግሯል። የቅርብ ጓደኞቹን ዋቢ አድርጎ እንደነገረን ከሆነም ተማሪዎች ትምህርት በተቋረጠባቸዉ ግዜያት በርካታ ተማሪዎች ወደ ሌላ የስራ መስክ የገቡ እና ሌላ ትምህርት የጀመሩ በመሆኑ ወደ ዩኒቨርስቲው የሚመለሱ ተማሪዎች ሊቀንስ እንደሚችል ጠቁሟል።

በተመሳሳይ የመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርስቲዎችም ባስቀመጧቸዉ የስልክ ቁጥሮች ተማሪዎቻቸዉ እየደወሉ አልያም የጽሁፍ መልዕክት እየላኩ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። አክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ እስከ ሚያዚያ 18 ድረስ እንዲመዘገቡ ቀነ ገደብ አስቀምጧል። ዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርት የሚጀምሩባቸዉን ቀናት ወደፊት እንደሚያሳዉቁም አስታውቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.4K views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 09:44:01
በማራቶን ውድድር አጋማሽ ላይ መኪና በመሳፈር ሶስተኛ የወጣችው አትሌትን ያገኘችውን ሜዳሊያ ተቀማች!

የአውስትራሊያ ዜግነት ያላት የአልትራ ማራቶን አትሌት የሆነችው ጆአሲያ ዛከርዘቭስኪ በቅርቡ በተካሄደው ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረች አዘጋጆቹ ባደረጉት ማጣራት የሩጫውን የተወሰነ ክፍል መኪና መጠቀሟን በማወቃቸው ሽልማቷን ነጥቀዋል።

የ47 ዓመቷ ጆአሲያ ዛከርዜውስኪ 80 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን አልትራስ ማራቶን በእንግሊዝ ከማንቸስተር እስከ ሊቨርፑል ከተማ ድረስ በተደረገው ውድድር 3ኛ ሆና አጠናቃለች። ውድድሩን አቋረጣ መኪና ብትጠቀምም ሜዳሊያዋን እና ዋንጫዋን ተረክባ ነበር። የውድድሩን ደንቦች አዘጋጆቹ ከመረመሩ በኋላ ዛከርዘቭስኪ በውድድሩ አጋማሽ ላይ በታሪክ ፈጣኑ ሰው ከሆነው ዩሴን ቦልት የበለጠ ፈጣን እንደሆነች ገልፀዋል።ጆአሲያ ዛከርዜቭስኪ በውድድሩ ወቅት በጓደኛዋ መኪና በመሳፈር እንጂ ፍጥነቷ በሩጫው እንዳልሆነ ተረጋግጧል።የአልትራ ማራቶን ከ60፣ 80 እስከ 150 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው የማራቶን ውድድር ነው።[ዳጉ ጆርናል]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.8K viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ