Get Mystery Box with random crypto!

በማራቶን ውድድር አጋማሽ ላይ መኪና በመሳፈር ሶስተኛ የወጣችው አትሌትን ያገኘችውን ሜዳሊያ ተቀማች | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በማራቶን ውድድር አጋማሽ ላይ መኪና በመሳፈር ሶስተኛ የወጣችው አትሌትን ያገኘችውን ሜዳሊያ ተቀማች!

የአውስትራሊያ ዜግነት ያላት የአልትራ ማራቶን አትሌት የሆነችው ጆአሲያ ዛከርዘቭስኪ በቅርቡ በተካሄደው ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረች አዘጋጆቹ ባደረጉት ማጣራት የሩጫውን የተወሰነ ክፍል መኪና መጠቀሟን በማወቃቸው ሽልማቷን ነጥቀዋል።

የ47 ዓመቷ ጆአሲያ ዛከርዜውስኪ 80 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን አልትራስ ማራቶን በእንግሊዝ ከማንቸስተር እስከ ሊቨርፑል ከተማ ድረስ በተደረገው ውድድር 3ኛ ሆና አጠናቃለች። ውድድሩን አቋረጣ መኪና ብትጠቀምም ሜዳሊያዋን እና ዋንጫዋን ተረክባ ነበር። የውድድሩን ደንቦች አዘጋጆቹ ከመረመሩ በኋላ ዛከርዘቭስኪ በውድድሩ አጋማሽ ላይ በታሪክ ፈጣኑ ሰው ከሆነው ዩሴን ቦልት የበለጠ ፈጣን እንደሆነች ገልፀዋል።ጆአሲያ ዛከርዜቭስኪ በውድድሩ ወቅት በጓደኛዋ መኪና በመሳፈር እንጂ ፍጥነቷ በሩጫው እንዳልሆነ ተረጋግጧል።የአልትራ ማራቶን ከ60፣ 80 እስከ 150 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው የማራቶን ውድድር ነው።[ዳጉ ጆርናል]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news