Get Mystery Box with random crypto!

ራያ ፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸዉን መመዝገብ ጀመሩ የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ራያ ፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸዉን መመዝገብ ጀመሩ

የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የመማር ማስተማር ስራቸዉን አቋርጠዉ የነበሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ዳግም ትምህርት ለመጀመር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን አስታዉቀዋል።ከነዚህም ዉስጥ የራያ ፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎቻቸዉ ጥሪ ማቅረባቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በአክሱም ዩኒቨርስቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና 4ኛ አመት ተማሪ የሆነዉ በርናባስ የሺጥላ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገረዉ ፤ ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ ለዩኒቨርስቲው መረጃ እንደሰጡ እና የኦንላይን ምዝግባ መከናወኑን ገልጿል። ዩኒቨርስቲው ባወጣዉ ማስታወቂያ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዉ ትምህርታቸዉን ከሚከታተሉ ተማሪዎች ዉጭ ሁሉም ተማሪዎቹ ምዝገባዉን እንዲያከናዉኑ ጥሪ አድርጓል።

ከሁለት አመታት በላይ ከትምህርት የራቀዉ በርናባስ ፤ ያሳለፋቸዉ ግዚያት ተስፋ አስቆራጭ የነበሩ ቢሆንም ዳግም ትምህርት ለመጀመር ተስፋ ማድረጉን ተናግሯል። የቅርብ ጓደኞቹን ዋቢ አድርጎ እንደነገረን ከሆነም ተማሪዎች ትምህርት በተቋረጠባቸዉ ግዜያት በርካታ ተማሪዎች ወደ ሌላ የስራ መስክ የገቡ እና ሌላ ትምህርት የጀመሩ በመሆኑ ወደ ዩኒቨርስቲው የሚመለሱ ተማሪዎች ሊቀንስ እንደሚችል ጠቁሟል።

በተመሳሳይ የመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርስቲዎችም ባስቀመጧቸዉ የስልክ ቁጥሮች ተማሪዎቻቸዉ እየደወሉ አልያም የጽሁፍ መልዕክት እየላኩ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። አክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ እስከ ሚያዚያ 18 ድረስ እንዲመዘገቡ ቀነ ገደብ አስቀምጧል። ዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርት የሚጀምሩባቸዉን ቀናት ወደፊት እንደሚያሳዉቁም አስታውቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news