Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.29K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-01-28 07:00:07
#አቢሲንያ_ባንክ
አቢሲንያን የሞባይል ባንክ አገልግሎት ወደ *815# በመደወል ብቻ ያለ ኢንተርኔት ወይም በስማርት ፎን መገልገል ይቻላል።ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

#BoAmobile #mobilebanking #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
22.6K views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-27 11:00:08
#አቢሲንያ_ባንክ
አቢሲንያን የሞባይል ባንክ አገልግሎት ወደ *815# በመደወል ብቻ ያለ ኢንተርኔት ወይም በስማርት ፎን መገልገል ይቻላል።ለበለጠ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!

#BoAmobile #mobilebanking #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
24.2K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-06 08:32:51
አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ያሰራ ሆቴል እና መሰል ተቋም እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣው የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው የቱሪስት አገልግሎት ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ይመር ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን እንደተናገሩት ቢሮዉ በአዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀፅ 22 ቁጥር 6-13 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዙሪያ ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴት እየተሸረሸረ በመሆኑ የደንብ ረቂቅ አውጥቷል።

በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የገፅታና የውበት አጠባበቅ እንዲሁም የጌጣጌጥ አጠቃቀም ስነ-ስርዓት ላይ ቢሮዉ ያወጣዉን የደንብ ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ጉዳዩን የጋራ አድርጓል።በረቂቅ ደንቡ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሆቴሎችና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የሚለብሷቸው ልብሶች እና የሚያደርጓቸው ጌጣጌጦች የኢትዮጵያን ባህል እና እሴት የጠበቁ መሆን እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ገንዘብ ቅጣትና ከባድ የሚባል እርምጃ ድረስ በረቂቅ ደንቡ ተጠቅሷል፡፡በዚህም መሰረት አጭር ቀሚስ አስለብሶ የመስተንግዶ ስራ ሲያሰራ የተገኘ የሆቴል ተቋምም ሆነ መሰል አገልግሎት ሰጪ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያቀጣ ወ/ሮ ገነት ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡በሌላ በኩል ከጌጣ ጌጥ ጋር ተያይዞ ጆሮ ላይ ከአንድ በላይ ጌጥ አድርጎ መገኘትን ረቂቅ ደንቡ ይከለክላል ሲሉ ወ/ሮ ገነት ይመር ጨምረዉ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡

በመመሪያዉ ላይ የቢሮዉ የቱሪዝም ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ መስተንግዶ ማህበር፣ የአዲስ አበባ ሆቴሎችና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር፣ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ተቋም እና የአዲስ አበባ ሆቴሎች ስራ አስኪያጅ ማህበር መሳተፋቸው ተመላክቷል፡፡ደንቡ በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴልና መሰል ተቋማት ወጥ የሆነ ስርዓት እንዲሰፍን ከማገዙም በላይ ባህልና ወጉን ያልጠበቀ የአለባበስ ስነ-ስርዓትን በመቆጣጠር ኢትዮጵያዊ አለባበስና መስተንግዶ ስርዓትን ለማስከበር እና ባለሙያዎች ከሚደርስባቸዉ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ለማስቀረት አጋዥ ነዉ ተብሏል።

የወጣዉ ረቂቅ በአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ታይቶ በካቢኔ ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆና ተብሎ ይጠበቃል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቢሮዉ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት ያወጣዉን ደንብ ከፍትህ ተቋማት ጋር ሙሉ በሙሉ የማስፈፀም መብት እንዳለዉ ተጠቅሷል፡፡
13.7K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-16 14:03:28 የኤርትራ መንግስት በቀይባህር ጉዳይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ አሳወቀ

የኤርትራ መረጃ ሚኒስቴር ባወጣዉ አጭር መግለጫ በቀይባህር ጉዳይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥ አሳዉቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስለ ውሀዊ አካሎችና ስለ ባህር በሮች የተባለውንና ''ተብሏል'' የተባለው ነገር ቁጥር የለውም ያለዉ ሚኒስቴሩ በዚም ያልተገረመ ታዛቢ የለም ሲል ገልጿል።

የኤርትራ መንግስትም እንደሁልጊዜው በእንደዚህ ዓይነቱ ጉዳዮች ላይ ለውይይት እንደማይታደም ማረጋገጡን ዳጉ ጆርናል ከሚኒስቴሩ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

ይህ ነገር ይመለከተናል የሚሉ ሁሉም አካላት ጉዳዩን እንዳይነኩት የኤርትራ መንግስት አስጠንቅቋል። በቅርቡ በመንግስት የመገናኛ ብዙኃን በተሰራጨ መልዕክት ጠ/ሚ ዐቢይ የባህር በር ጉዳይን አንስተዉ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ማወያየታቸዉ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.8K viewsedited  11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 21:31:49
#Update

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ 13 አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ .ም ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል።

ይህንን በተመለከተም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተላከው ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማለዳ እንዲደርስ ተደርጓል።

መረጃው የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
3.4K viewsedited  18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 20:55:17 ትግራይ

በትግራይ ክልል ረሃብ 'በከፍተኛ መጠን' መጨመሩን ተመድ አስታወቀ!!

በጦርነት በተጎዳው የትግራይ ክልል ለከፋ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን እና፣ በቅርቡ የምግብ ርዳታ መቆሙን ተከትሎ፣ ሁኔታዎች እየተባባሱ ሊሄዱ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ፤ሰኞ ዕለት ይፋ ባደረገው ወቅታዊ ሪፖርት፣ በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨማሪ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚኖሩ 8.8 ሚሊየን ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
4.3K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 14:57:29
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ነገ ፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ይሰጣሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ አዲስ ማለዳ ከምክር ቤቱ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 29/2015 ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን ያጸድቃል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.5K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 14:30:58 የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲዳራጅ ተወሰነ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት በዛሬው ቀጣይ ዉሎው የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተካተቱበት «የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል» በሚል ስያሜ አዲስ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏልመደበኛ ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባካሄዱት ሕዝበ ውሳኔ በአንድ ክልል የመደራጀት ፍላጎታቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በአንድ ክልል እንዲደራጁ በዛሬው እለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ መወሰኑን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል፡፡

«የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል» በሚል በአዲስ የተደራጁት በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጎፋ፣ በጌዲዮ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በኮንሶ ዞኖችና በደራሼ፣ በቡርጂ፣ በአማሮ፣ በኧሌና በባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ናቸው፡፡    

ቀድሞ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ውስጥ የነበሩ የሀድያ፣ የሀላባ፣ የከምባታ ጠምበሮ፣ የስልጤ፣ የጉራጌ  ዞኖችና የየም ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በነባሩ ክልል የሚቀጥሉ ይሆናል።

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛው የፓርላማ ዘመን፣ በ1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜው ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውስጥ በስድስት ዘኖችና በአምስት ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ የጌዴኦ ፣ የወላይታ ፣ የጋሞ ፣ የጎፋ ፣ የኮንሶ እና የደቡብ ኦሞ ዘኖች እንዲሁም የቡርጂ፣ የአማሮ፣ የደራሼ፣ የባስኬቶ እና የኧሌ ልዩ ወረዳዎች  ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ ክልል ለመመስረት ያቀረቡትን ጥያቄ በመቀበል በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 47/3/(ለ)መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያደራጂ እና በጋራ ክልል የመመሥረት ጥያቄው የሕዝቡን ይሁንታ ስለማግኘቱ የሕዝበ ውሳኔውን ውጤት ሪፖርት ለምክር ቤቱ እንዲያቀርብ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መምራቱ ይታወሳል::

በመጨረሻም የተከበሩ አፈ ጉባኤ  አቶ አገኘሁ ተሻገር የውሳኔ ሀሳቡ እንዲጸድቅ ለድምጽ አቅርበው ቤቱ በሙሉ ድምጽ ደግፎ አጽድቆታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.2K viewsedited  11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 14:28:54
በቤኒሻንጉል ክልል የኢቦላ ቫይረስ እንዳይከሰት ስጋት መኖሩ ተነገረ

በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን የኢቦላ ቫይረስ ተጠርጣሪዎች መገኘት እና ሞት መመዝገቡን ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል የሚል ስጋት እንዳለ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቃል።

በተለይ በሱዳን የተፈጠረውን የእርስ በእርስ ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ክልሉ በአጎራባች ወረዳዎች በኩል በከፈተኛ  ሁኔታ ከመግባታቸው ጋር ተያይዞ በሽታው ሊገባ እንደሚችል ተገልጿል።

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብተሰብ ጤና ጣቢዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍቃዱ አየለ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በሱዳን ዳባላይ በምትባል ስፍራ ከ150 በላይ በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች እንዳሉ የተነገረ ሲሆን እሱን ለማጣራት ከዓለም የጤና ድርጅት እና ከሌሎች አካላት አካላት ጋር በመሆን ጥናት እየተደረገ ይገኛል።

በሽታው ቢያጋጥም ለይቶ ማቆያ የተዘጋጀ ሲሆን በሽታው በቀላሉ ሊገባ የሚችል በመሆኑም በባለሙያዎች  የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።የበሽታው ምልክቶች  ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ የጉሮሮ ፣ የሆድና የመገጣጠሚያ ህመም ፣ ድካም፣ የምግብ ፍለጎት መቀነስ እና በተለያዩ የሰውነት ቀዳዳዎች ደም መፍሰስ  ናቸው፡፡

በመሆኑም በሽታው ከታየበት ሀገር  የጉዞ ታሪክ ያለውና ምልክቶቹ ከታዩ በአቅራቢያ ወደ ሚገኘው የህክምና ተቋማት እንዲሄዱ ማድረግን ጨምሮ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራ በመስራት መረጃ በትክክል መያዝ እንዳለበት አቶ ፍቃዱ አየለ ተናግረዋል።

ከፌደራል ጤና ኢንስቲትዩት እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ  ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
6.4K viewsedited  11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 09:32:42 በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል

በኦሮሚያ ክልል ከግንቦት 19 እስከ ግንቦት 26  ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ25 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ36  ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መረጃ ጥናት እና አገልግሎት ዲቪዥን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋዎቹ በምዕራብ አርሲ ገዳ አሳሳ ፣ምዕራብ ጉጂ ቡሌ ሆራ ፣ምስራቅ ሀረርጌ ሆሮ ጉድሩ፣ ምስራቅ ወለጋ ሲቡ ስሬ ወረዳዎች እና ምስራቅ ጉጂ አዶላ ዋቱ ፣ሮቤ ከተማዎች እንዲሁም ሻሸመኔ ከተማ አብቹ ክ/ከተማ የደረሱ ናቸው።


አደጋዎቹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት የተመዘገቡ ሲሆን የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት ተሽከርካሪ፣ በህዝብ ማመላለሻ ፣በሶስት እግር (ባጃጅ)እና በሞተር ሳይክል ተሸርከርካሪዎች የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡።

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር 3፣የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
7.5K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ