Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌሎች አራት ኢትዮጵያዊያን የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ ለሞት እና ለመቁሰል አደጋ የተዳረጉት፣ በተባራሪ ጥይት እና ከባድ መሳሪያ አረሮች ፍንጣሪ ሳቢያ መኾኑን ኢምባሲው መግለፁን ዘገባው አመልክቷል።

ከአገሪቱ መውጣት የሚፈልጉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በአውቶብስ ወደ መተማ ለመሸኘት እየመዘገበ መሆኑን ኤምባሲው መግለፁን የጠቀሰው ዘገባው፣ የኤምባሲው ሠራተኞች ካርቱምን ለቀው ለኢትዮጵያ ቅርብ በሆነችው የሰሜን ሱዳኗ ገዳሪፍ ከተማ ሥራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news