Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.41K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-24 09:44:01
በማራቶን ውድድር አጋማሽ ላይ መኪና በመሳፈር ሶስተኛ የወጣችው አትሌትን ያገኘችውን ሜዳሊያ ተቀማች!

የአውስትራሊያ ዜግነት ያላት የአልትራ ማራቶን አትሌት የሆነችው ጆአሲያ ዛከርዘቭስኪ በቅርቡ በተካሄደው ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረች አዘጋጆቹ ባደረጉት ማጣራት የሩጫውን የተወሰነ ክፍል መኪና መጠቀሟን በማወቃቸው ሽልማቷን ነጥቀዋል።

የ47 ዓመቷ ጆአሲያ ዛከርዜውስኪ 80 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን አልትራስ ማራቶን በእንግሊዝ ከማንቸስተር እስከ ሊቨርፑል ከተማ ድረስ በተደረገው ውድድር 3ኛ ሆና አጠናቃለች። ውድድሩን አቋረጣ መኪና ብትጠቀምም ሜዳሊያዋን እና ዋንጫዋን ተረክባ ነበር። የውድድሩን ደንቦች አዘጋጆቹ ከመረመሩ በኋላ ዛከርዘቭስኪ በውድድሩ አጋማሽ ላይ በታሪክ ፈጣኑ ሰው ከሆነው ዩሴን ቦልት የበለጠ ፈጣን እንደሆነች ገልፀዋል።ጆአሲያ ዛከርዜቭስኪ በውድድሩ ወቅት በጓደኛዋ መኪና በመሳፈር እንጂ ፍጥነቷ በሩጫው እንዳልሆነ ተረጋግጧል።የአልትራ ማራቶን ከ60፣ 80 እስከ 150 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለው የማራቶን ውድድር ነው።[ዳጉ ጆርናል]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.8K viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 09:27:18
አስቸኳይ መረጃ

በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ የሃይማኖት መልክ ያለው ፀብ ተነስቷል።

በርካታ መኖርያ ቤቶች እንዲሁም ሆቴሎች እየወደሙ ነው፣አስቸኳይ መፍትሔ ያስፈልጋል።(ayu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.1K views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 08:06:48
መንግስት "ሸኔ" ብሎ የሚጠራኝ ማንነቴን እና አላማዬን ለማጥላላት ነዉ ሲል የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አስታወቀ

በትናንትናው እለት መንግስት "ሸኔ" ሲል ከሚጠራዉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር በታንዛንያ ድርድር ሊያደርግ መሆኑን መዘገቡ ይታወሳል። ሰራዊቱ ድርድሩን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀው ለድርድሩ ያስቀመጣቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ማግኘታቸዉን ተናግሯል።

በመግለጫው አያይዞም ፤ መንግስት "ሸኔ" ሲል የሚጠራኝ ማንነቴን እና አላማዬን ለማጥላላት ነዉ ሲል ሲል ሰራዊቱ ገልጿል። መንግስት በተለይም በኦሮሚያ ክልል እና በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለሚደርሱ ጥቃቶች "ሸኔን" ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል።

በርካታ የፖለቲካ ተንታኞችም "ሸኔ" የተሰኘ አደረጃጀት እንደሌለ ሲገልጹ መቆየታቸዉ ይታወቃል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድሩ ግልጸኝነት እንዲኖረዉ በሶስተኛ ወገን አደራዳሪነት መከወኑ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሷል። ይህም በመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን እና ድርድሩ እንደሚከናወን ማረጋገጫዉን ሰጥቷል።

የሰላም ድርድሩ ሁለቱንም ወገኖች ወደ አንድ የሚያመጣ ፣ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን እና ወደ ዲሞክራሲ የሚወስድ መሆኑን በመግጫዉ ጨምሮ መጥቀሱን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.4K views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:33:28
ኦነግ ሸኔና የኢትዮጲያ መንግስት በታንዛኒያ ከማክሰኞ ጀምሮ ንግግር እንደሚጀምሩ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ተናገሩ

ይህ የተነገረው በዛሬው እለት በተካሄደው "ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናጽና" የምስጋና እና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ በተከነወነው መርሃ ግብር ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ከኦነግ ሸኔ ጋር የፊታችን ማክሰኞ በታንዛኒያ ንግግር እንደሚጀምር በመድረኩ ገልፀዋል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በሰላም ስምምነቱ እልባት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የማመስገንና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።

በጨመረ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት፣ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
415 viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:04:15
በጦርነት ይብቃ
ሰላም ይፅና መርሃግብር ላይ ጌታቸው ረዳ የተናገረው

"የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፋጠን የጠሚ አብይ አህመድ ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው። አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈጣን እርምጃዎች የተጀመረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ መስራት አለበት እላለሁ።

የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ከማንም ጋር ጦርነት መግባት አንፈልግም። ከአማራም ከአፋርም የሚያቀራርብ እንጂ የሚያቃቅር ነገር የለንም።

ትናንት በአፋር በኩል የሰላም ባስ አገር አቋራጭ አልፏል። ሐጂ አወል ይህንን ለማጠናከር መስራት ይገበዋል።

በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘም ዶክተር ከፋለ ኃላፊነት ወስደህ መስራት አለብህ ለማለት እፈልጋለሁ።

ዶክተር አብይ በጀመረው እጁ በሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን በሆደ ሰፊነት ለመፍታት መስራት እንደለበት ለመጠቆም እፈልጋለሁ!

በመጨረሻ ከይዋጣልን መንፈስ ወጥተን የፍቅር፣ የስራ ቋንቋ መጀመር አለብን። ሰላም እንዲፀና የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መንግስት የበኩሉን ይሰራል"

አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተዳድር ፕሬዝዳንት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.5K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:16:11
ፕሬዝደንት ባይደን የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ እንዲያቆሙ አሳሰቡ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ያለቅድመ ሁኔት በአስቸኳይ ተኩስ አቁም ተስማምተው ሰብአዊ አገልግሎቶች ያለገደብ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

አሜሪካ ቀደም ሲል ባደረገችው ጫና ሁለቱ ወገኖች ተኩስ ለማቆም ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።ጦርነቱ በመባባሱ ምክንያት የተለያዩ ሀገራት በሱዳን ያሏቸውን ዜጎች እያስወጡ ነው። አሜሪካም በሱዳን ያሏትን ሁሉንም ዲፕሎማቶች ማስወጣቷን አስታውቃለች።(alain)


@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2.6K viewsedited  15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 14:10:49
ኢትዮጵያ በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ገንቢ ሚና ትጫወታለች

ኢትዮጵያ በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ገንቢ ሚና እንደምትጫወት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡በውይይታቸው ሀገራቱ የቆየ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይም መክረዋል፡:

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቀጠናው የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን መፍታት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.2K viewsedited  11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 20:14:12 ከመቀሌ አዲስ አበባ

ዛሬ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ የአውቶብስ መጓጓዣ አገልግሎት መጀመሩን ድምጸ ወያኔ ዘግቧል።

ከኹለት ዓመታት በኋላ ዛሬ መንገደኞችን ማጓጓዝ የጀመረው፣ ሰላም ባስ የግል ትራንስፖርት ኩባንያ መኾኑን ዘገባው አመልክቷል።

በዛሬው የመጀመሪያ ጉዞ 54 መንገደኞች ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ እንደተጓዙ ዜና ምንጩ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.1K viewsedited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 14:58:11
በሻሸመኔ ከተማ ቁልፍ በማስቀረፅ ተሽከርካሪ የሰረቀው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ 02 ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ንብረትነቱ የአቶ አብዱልቃድር የሆነ ተሽከርካሪን ቁልፍ በማስቀረፅ አስነስቶ ሊያመጥ የነበረው ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የወረዳ 02 ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን አህመድ ሲሊ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የግል ተበዳይ ተሽከርካሪ የህዝብ ማመላለሻ የሆነ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 ቢ አ.አ 78942 መሆኑን የክስ መዝገቡ ያሳያል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ሚያዚያ 7 ቀን 2015 ሲሆን በእለቱ በሻሸመኔ ከተማ በተሰናዳው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ወደ መኖሪያ ቤታቸው አቶ አሽዱልቃድር ማቅናታቸውን ተከሳሽ ረይኑ አህመድ ሲከታተል ቆይተዋል።ተከሳሹ ከተሽከርካሪው በተጨማሪ የመኖሪያ ቤታቸውን ቁልፍ አስቀርጾ የነበረ ሲሆን አቶ አብዱልቃድር ላይ ቤቱን ከወጪ በመዝጋት መኪናውን አስነስቶ ለመሰወር ይሞክራል።

በዚህ ወቅት በተሽከርካሪ ጥበቃ ላይ የነበረ ግለሰብ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ለፀጥታ አካላት ያሳውቃል። ፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተከሳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል መዝገቡን አጣርቶ ለፍርድ ቤት ያቀርባል። የክስ መዝገቡን የተመለከተው የሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት በፈጣን ችሎት ተከሳሽ ረይኑ ጥፋተኛ በማለት በአምስት ዓመት እስር እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፉን ሳጅን አህመድ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.8K viewsedited  11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 08:28:12 የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ኢድ አልፈጥርን ምክንያት በማድረግ ከትናንት ጀምሮ የሦስት ቀናት ተኩስ አቁም ለማድረግ መወሰናቸውን ትናንት አስታውቀዋል። ኾኖም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የተኩስ ልውውጡ እንደቀጠለ መኾኑን የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ለሰባት ቀናት በተካሄደው ውጊያ 430 ሰዎች መገደላቸውንና ከ3 ሺህ 500 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።

በተያያዘ፣ አሜሪካ ከካርቱም ኢምባሲዋ ዲፕሎማቶቿን ማስወጣት ካስፈለጋት ድጋፍ የሚሰጡ ልዩ ኮማንዶዎቿን ወደ ቀጠናው መላኳን አስታውቃለች።

@sheger_press
@sheger_press
9.2K views05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ