Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.41K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-18 19:36:49
ልዩ መረጃ

ወቅታዊ እና እውነተኛ የመረጃ እጦት ለገጠማቸሁ የቱን ልመን? ብላችሁ ለተወዛገባችሁ ፣ እነሆ ሀገራዊ እና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን ካሉበት አጣርቶ እና ፈልፍሎ የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ።

ልዩ መረጃ እንደስሙ የልዩ መረጃ ቋት ቻናል ነው
https://t.me/+w_WxZh6ZsHY2Nzdk
https://t.me/+w_WxZh6ZsHY2Nzdk
3.5K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 17:33:39
የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጡ ሰብአዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዉሞን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብትን እንዲያከብርና የታሰሩ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን እንዲፈታ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ትናንት ማምሻ ባወጣዉ መገለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አማራ ክልል በተፈጠረዉ ሁከት ምክንያት ያሰሯቸዉን 7 የመገናኛ ዘዴ ባልደረቦች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ከእስረኞቹ ባንዷ ላይ ተፈፀመ የተባለዉን አካላዊ ጥቃት እንዲያጣሩ ጠይቋል።

መግለጫዉ እንዳለዉ ባለስልጣናቱ «ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ሁሉም ወገን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብቱን ማስከበር አለባቸዉ።»ባለፈዉ ሳምንት በአማራ ክልል የመብት ጥሰትና ሁከት መቀስቀሱ እንዳሳሰበዉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታዉቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቀባይ ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸዉ፣ አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸዉንም ድርጅቱ «አሳሳቢ» ብሎታል።የመንግስት ኃይላትም ሆኑ ሌሎች ታጣቂዎች «የሰብአዊ ርዳታ ሰራተኞችን ያለማጥቃት ኃላፊነት አለባቸዉ።» ይላል መግለጫዉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
4.9K viewsedited  14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 17:38:21
ሱዳን ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን ራሳችሁን ጠብቁ!

በሱዳን ካርቱም በመሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና በጀነራል አብዱልፈታል አልቡርሃን በሚመራው የሱዳን ብሔራዊ ጦር መካከል በካርቱም እያካሄዱት ባለው ውጊያ ሳቢያ 5 ኢትዮጵያዊያን ተገለዋል። ኢትዮጵያዊያን በተቻላችሁ አቅም ከቤት ባለመውጣት ራሳችሁን ጠብቁ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.3K viewsedited  14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 16:28:02
ማስታወቂያ!!

የተባበሩት ኤምሬትስ የሰጠውን ስኮላርሽፕ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች ሁሉ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት በፈቀደው መሰረት ቀደም ሲል በተማሪዎች ቃል የተገባላችሁ ተማሪዎችና በዕድሉ ለመጠቀም ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች Application Form link:
http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en --
በመግባት ከዛሬ 09/08/15 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ከላይ በተቀመጠው ሊንክ በመግባት፡-
1. የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ኮፒ (Grade 12 Result) copy
2. ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ (Grade 9-12 transcript) copy
3. CV/ Curriculum Vitae copy
4. የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ (Birth Certificate) copy እና ሌሎች በሊንኩ የተጠቀሱ መረጃዎችን እንድትሞሉ እናሳስባለን ።
መረጃዎች ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር በቀጣይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
 
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.6K viewsedited  13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 19:33:55 በካርቱም የሞቱ ሰዎች ቁጥር 56 መድረሱ ተሰምቷል!!

ትናንት በሱዳን በሀገሪቱ ጦር እና አርሴስኤፍ ሀይሎች መካከል የተጀመረው ውጊያ አዳሩንም ቀጥሏል።

ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ዶክተሮች ኮሚቴ እንደገለጸው በጦርነቱ ምክንያት እስካሁን በካርቱም የሟቾች ቁጥር ወደ 56 ከፍ ብሏል።

የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል በትናትናው እለት የተከሰተውን ግጭት ትክተሎ በሁለቱም ወገኖች በርካታ የሰራዊት አባላትም ሞተዋ የተባለ ሲሆን፤ ከ600 ገደማ ሰዎች መቁሰላቸውን የሱዳን ዶክተሮች ማእከላዊ ኮሚቴን አስታውቋል።

በተጨማሪም የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል “የሱዳን አየር ኃይል ተዋጊ ጄት መትቼ ጣልኩ” አለ።

በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው “ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ)” ተብሎ የሚጠራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል “የሱዳን አየር ኃይል ተዋጊ ጄት መትቼ ጣልኩ” ብሏል። የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ “Sukhoi Su-30MKI” የተባለ የጦር ጄት ዛሬ ጠዋት ላይ መትቶ መጣሉን አስታውቋል።

በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው “ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ)” ተብሎ የሚጠራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና በሱዳን ጦር መካከል ትናንት የተቀሰቀሰው ውጊያ ዛሬም ቀጥሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.1K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 19:21:00
ልዩ መረጃ

ወቅታዊ እና እውነተኛ የመረጃ እጦት ለገጠማቸሁ የቱን ልመን? ብላችሁ ለተወዛገባችሁ ፣ እነሆ ሀገራዊ እና አለምአቀፋዊ መረጃዎችን ካሉበት አጣርቶ እና ፈልፍሎ የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ።

ልዩ መረጃ እንደስሙ የልዩ መረጃ ቋት ቻናል ነው
https://t.me/+w_WxZh6ZsHY2Nzdk
https://t.me/+w_WxZh6ZsHY2Nzdk
10.2K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 18:35:31
ሰበር

በሱዳን ካርቱም በተከሰተው ጦርነት የሀገሪቱ ጦር አዛዥ የሆኑት አልቡርሀን በሌላ አካባቢ ያለው ንጦር ወደከተማ እንዲመጣ እጠራለሁ ባሉት መሠረት የኢትዮጵያን መሬት ወሮ ይዞ የነበረው የሡዳን ጦር ያለበትን የአልፋሽጋን ቦታ ጥሎ መውጣቱ ተሠምቷል

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.0K viewsedited  15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 04:35:21
ውድ ቤተሰቦቻችን እንኳን አደረሳችሁ !

ውድ የኢትዮ መረጃ የክርስትና እምነት ተከታይ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
3.4K viewsedited  01:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:17:15
ሱዳን
በጎረቤት ሀገረ ሱዳን መዲና ካርቱም ግጭት መቀስቀሱና በረካታ ሰወች መሞታቸውና መቁሰላቸው ተሰማ!!!

የተኩስ ልውውጡ በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ እና በሀገሪቱ መከላከያ ሀይል ወታደሮች መካከል እንደሆነ ተገልጿል። ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የተኩስ ልውውጡ ከደቂቃዎች በፊት የጀመረ ሲሆን የከተማው ነዋሪዎች በድርጊቱ መደናገጣቸውን ዘግቧል።

የተኩስ ልውውጡ በካርቱም የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ሲሆን የከባድ መሳሪያ ድምጽም እየተሰማ ነው ተብሏል።

በሱዳን የሲቪል አስተዳድር ለመመስረት ውይይቶች ሲካሄዱ የቆዩ ሲሆን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ወደ ብሔራዊ ጦሩ የሚዋሀድበት ጊዜ ላይ ስምምነት መፍጠር አልተቻለም። ከሰሞኑ የሀገሪቱ መከላከያ ቃል አቀባይ ሱዳን በታሪካዊ እጥፋት ላይ እንደምትገኝ ገልጾ ካርቱም ዲሞክራሲያዊት አልያም ወደ ለየለት እርስ በርስ ጦርነት ልትገባ ትችላለች ሲል አሳስቦ ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.9K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 20:39:14 መረጃ

ህወሓት በሱዳን የሚገኙ አባላቱን ጨምሮ  “የቡድን ትጥቆቹን የማስረከብ ሂደት” ከመጪው ሰኞ ጀም እስከ የካቲት 16 እንደሚከናወን የተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ

በትግራይ ክልል የሚገኙ የቡድን ትጥቆችን ሰብስቦ ለመከላከያ ሰራዊት የማስረከብ ሂደት በመጪው ሰኞ ሚያዝያ 9 ፤ 2015 እንደሚጀመር ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ጎረቤት በሆነችው ሱዳን ሀገር የሚገኙ ኃይሎችን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ የትግራይ ታጣቂዎችን የማሰባሰብ ስራም በአጭር ጊዜ እንደሚጀምር ኮሚሽኑ ገልጿል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽኑ ይህን የገለጸው፤ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ከተወያየ በኋላ ትላንት አርብ በሰጠው መግለጫ ነው። የተሃድሶ ኮሚሽኑን በኮሚሽነርነት የሚመሩት ተሾመ ቶጋ እና ሁለት ምክትሎቻቸው የተገኙበት ይህ ውይይት፤ በውጊያ ላይ የቆዩ ኃይሎችን “ትጥቅ የማስፈታት፣ እንዲበተኑ የማድረግ እና እንደገና ወደ ህብረተሰቡ የመዋሃድ” ሂደትን በተመለከተ “ቀሪ ስራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ” ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር ተብሏል።

የቀድሞ ታጣቂዎችን እንዲበተኑ ከማድረግ በፊት መጠናቀቅ ያለበት አንዱ ስራ “ትጥቅ ማስፈታት” መሆኑን በመግለጫው የጠቀሱት ኮሚሽነር ተሾመ ቶጋ፤ እስካሁን የተከናወነው እንደተጠበቀ ሆኖ “የቡድን መሳሪያዎችን የማስረከብ ስራ ቶሎ መጠናቀቅ እንዳለበት” ከስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል። የቡድን መሳሪያዎችን የማስረከብ ሂደቱ፤ “ከሰኞ ጀምሮ በጣም ባጠረ ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም” ገልጸዋል። 

የተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴየር ጄነራል ደርቤ መኩሪያ በበኩላቸው፤ በትግራይ ክልል እና በመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው የቡድን ትጥቆች የመረካከብ ሂደት ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 16፤ 2015 ባሉት ጊዜያቶች ለማጠናቀቅ ከመግባባት ላይ መደረሱን አብራርተዋል። የቡድን መሳሪያዎች የሚባሉት “ቡድን፣ ኃይል፣ ሻምበል አሊያም ሻለቃ” በተሰኙ ወታደራዊ አደረጃጀቶች ደረጃ የሚያዙ እንደ መትረየስ፣ ዲሽቃ፣ ላውንቸር የመሳሰሉ የጦር መሳሪያዎች መሆናቸውን ለወታደራዊ ጉዳዮች ቅርበት ያላቸው አንድ ምንጭ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። 

እንደዚህ አይነት የቡድን መሳሪያዎች በነፍስ ወከፍ ደረጃ ከሚያዙ የጦር መሳሪያዎች፤ በተኩስ አቅምም ሆነ በሚሸፍኑት ረዘም ያለ ርቀት የሚለዩ መሆናቸውን እኚሁ ምንጭ አስረድተዋል። እንደ መድፍ፣ ታንክ፣ ጸረ-ታንክ፣ የአየር መቃወሚያ፣ ሚሳኤል ያሉት የጦር መሳሪያዎች ደግሞ “ከባድ መሳሪያ” በሚለው ምድብ የሚካተቱ መሆናቸውን ዘርዝርዋል። ብርጋዴየር ጄነራል ደርቤ በትላንቱ መግለጫቸው፤ በደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መሰረት፤ የከባድ መሳሪያዎች የማስረከብ ሂደቱ ቀደም ሲል መከናወኑን አስታውሰዋል። 

በዚህ ርክክብ ውስጥ የአየር ኃይል ትጥቆች ጭምር እንደነበሩበት የተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። “ብዙ ጊዜ የማይገለጸው የአየር ኃይል ትጥቅ ነው። ግን በርከት ያለ ትጥቅ የነበረ፤ ክልሉ ሰብስቦ በስነ ስርዓት ለመከላከያ ያስረከበው ትጥቅ አለ። … መከላከያ በተሟላ መንገድ የአየር ኃይል ባለሙያዎች ልኮ ርክክብ ተደርጓል” ሲሉም ብርጋዴየር ጄነራል ደርቤ አጽንኦት ሰጥተዋል። 

በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ጥቅምት 23፤ 2015 በፕሪቶሪያ ከተማ በተፈረመው ግጭት ማቆም ስምምነት መሰረት፤ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የማስፈታት ሂደት ቅድሚያ ተሰጥቶት የሚከናወን ተግባር ነው። የጦር መሳሪያዎችን የማስፈታቱ ሂደት፤ የሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች የጦር አዛዦች ከሚያደርጉት ስብሰባ፤ አስር ቀናት በኋላ ሊከናወን እንደሚገባ በግጭት ማቆም ስምምነት ስድስተኛ አንቀጽ ላይ ሰፍሯል። ከዚህ ስምምነት መፈረም አንድ ሳምንት በኋላ በኬንያ ናይሮቢ የተገናኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የትግራይ ኃይሎች አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ታደሰ ወረደ፤ የግጭት ማቆሙን ተግባራዊ የሚያደርግ ስምምነት ተፈራርመዋል። ቀላል የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ አጠቃላይ ሂደት፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት በተፈረመ በ30 ቀናት ውስጥ ሊጠናቀቅ ከስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረ ቢሆንም፤ ሂደቱ ከአራት ወራት በኋላም አልተጠናቀቀም። 

“የቡድን ትጥቅን በተመለከተ ከጠቅላላው ታጣቂ ምዝገባ እና ከdemoblization ስራ ጋር የሚያያዝ ነው ሆኖ የነበረው። በዚህ መሰረት እየተሰራ ነው የመጣው” ሲሉ በትላንቱ መግለጫ ያስረዱት ብርጋዴየር ጄነራል ደርቤ፤ የማስረከብ ሂደቱን ለማከናወን አስቀድሞ “መነጋገር” እና “ትጥቆችን ወደ ተለያዩ ቦታዎች ማሰባስብ” ያስፈልግ እንደነበር አስገንዝበዋል። “ትጥቅ ሲሰበሰብ በጥንቃቄ፣ በመመካከር ነው የሚሆነው እና ይሄ ስራ እየተሰራ እንደቆየ ተረድተናል” ሲሉም አክለዋል።

በአንድ ሳምንት ውስጥ “ይጠቃለላል” የተባለው የቡድን መሳሪያ የማስረከብ ሂደትን ተከትሎ የሚከናወነው፤ “የነፍስ ወከፍ ትጥቅ የመመዝገብ እና የማስተዳደር” ስራ መሆኑን የተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። ለምዝገባ ሂደቱ እና በስተኋላ ላይ ለሚደረገው ታጣቂዎችን የመበተን ስራ እንዲረዳም፤ “በተለያየ ቦታ ያሉትን የቀድሞ ታጣቂዎች የማሰባሰብ እና ለስራ በሚመች መንገድ ማደራጀት” በአጭር ጊዜ እንደሚጀመርም ብርጋዴየር ጄነራል ደርቤ በትላንቱ መግለጫቸው አመልክተዋል። ይህ የማሰባሰብ ስራ “በሱዳን አካባቢ ያለው ኃይልንም” እንደሚጨምርም ተናግረዋል።  

“ጠቅላላ ተዋጊውን ኃይል እና የያዘውን የነፍስ ወከፍ ትጥቅ” የመመዝገብ ሂደት የሚፈጸመው፤ ታጣቂዎች “በያሉበት” እንደሚሆን ከመግባባት ላይ መደረሱንም ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ከዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው፤ የምዝገባ ሂደቱን ለማከናወን “ከሚወስደው ጊዜ እና ከሚያስፈልገው ሀብት አንጻር” ተመዝኖ መሆኑንም አስረድተዋል። ከቀድሞ ታጣቂዎች የሚሰበሰበው የነፍስ ወከፍ ትጥቅ ከተመዘገበ በኋላ፤ በክልሉ የሚደራጀው መደበኛ ፖሊስ እና የአካባቢ ሚሊሺያ “እንዲታጠቀው” እንደሚደረግም ብርጋዴየር ጄነራል ደርቤ ገልጸዋል።

ይህ የሚሆነው ግን የክልሉ መንግስት ከፌደራል መንግስት ጋር በሚያደርገው ንግግር መሰረት መሆኑን አስታውቀዋል። ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኃላፊዎች ጋር ውይይት ካደረጉት የትግራይ ክልል አመራሮች አንዱ የሆኑት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፤ “ከቡድን መሳሪያ ጋር በተያያዘ ያሉትን [ቀሪ] ስራዎችን በአጠረ ጊዜ አጠናቅቆ” ታጣቂዎችን ወደ መበተን እና መልሶ ከህብረተሰቡ ጋር ወደ መዋሃድ “በፍጥነት መገባት” እንዳለበት አሳስበዋል። “Demobilized የሆኑ የሰራዊት አባላት ወደ ህብረተሰቡ ሲመለሱ፣ በተገቢው መልሶ የሚቋቋሙበትን ሁኔታ የመስራት ኃላፊነት ትልቅ እንደሆነ እንገነዘባለን” ያሉት ጌታቸው፤ በዚህ ሂደት ረገድ ሊመጡ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ከፌደራል መንግስት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል።    

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
6.0K viewsedited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ