Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.46K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 518

2021-01-30 17:48:33
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ።

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ዓመት ድረስ የሚማሩ እንደሆነ ተመልክቷል።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ከሰተ ለገሰ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው 13 ሺህ ተማሪዎችን ይቀበላል።

ተማሪዎችን ከአውቶቡስ መነኸሪያ እና መቀሌ ከተማ ተቀብለው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማስገባት የተማሪዎች ህብረት አመራሮች ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ያለምንም ችግር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የምግብ ፣ መኝታ ፣ መማሪያ ክፍሎች የኤሌክትሪክ መብራት እና የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መሰናዳታቸውን ዶክተር ከሰተ አስታውቀዋል።

የጊቢው የማፅዳት ስራ መጠናቀቁን አመልክተው የመማር ማስተማር ስራው የሚካሄደው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያስችል መንገድ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከሁሉም የሀገራችን ክልሎች ለሚመጡ ተማሪዎች ከጥር 28 እስከ 30/ 2013 ዓ.ምባሉት ቀናት ውስጥ የእንኳን ደህና መጣችሀ አቀባበል ይደረጋል ብለዋል።

ከአቀባበሉ በኋላ የመማር ማስተማሩ ሥራ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የመማሪ ማስተማር ስራ ሲጀመር በመልካም ሥነ-ምግባር ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል። (ENA)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.2K views14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 16:58:00
በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ 21 ሺህ 695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደሉ ካቢኔው ወሰነ!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፤ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኘው ግኝትቶች ላይ ነው የውሳኔ ሃሳብ ያሳለፈው፡፡

በመሆኑም በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆኑ፤ በጥናቱ የተገኘው ህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ 21 ሺህ 695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል ነው ውሳኔ የተላለፈው፡፡

በዚህም በዋናነት በ1997 ዓ.ም ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በዕጣ እንዲተላለፍ፤የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወጥቶላቸው ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንዲሰጥ ሲሉ ወስነዋል፡፡

ካቢኔው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን ይህ ችግርና ስርዓት አልበኝነት 1997 ጀምሮ እየተንከባለለ የመጣ መሆኑን እና ወደፊት እንዳይደገም በፅናት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.5K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 13:53:03
ኢትዮጵያ ከግለሰቦችና ድርጅቶች በላይ ናት!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ድረ ገጻቸው ያሰፈሩት ሙሉ ጽሁፍ እንደሚከተለው ምስል ላይ ቀርቧል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.0K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 13:53:03
12.3K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 11:10:05
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን እንዲመስል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው!

ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ፣ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን እንዲመስልና በቴክኖሎጂ የዳበረ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናገሩ።

ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአባሉ እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችን እንዲመስል እና ከወቅቱ ጋር እንዲዘምን ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከለውጡ በኋላ ወደ ሠራዊቱ የሚቀላቀሉ ወጣቶች ፍላጎት መጨመሩን የገለፁት ጄኔራል ብርሀኑ፣ ከመላ ሀገሪቱ በተመለመሉ ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱ እና ለሙያው ፍቅርና ክብር ያላቸው ተተኪ ወታደሮችን ለማፍራት ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፤ በዚህም አበረታች ለውጦች እየተገኙ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

በተለይም ከዚህ በፊት፣ በውሳኔ ሰጪ ቦታዎችና የተመረጡ ሙያዎች፣ በከፍተኛ ወታደራዊ አመራሩ በአንድ ብሔር ተወላጆች ብቻ ተይዞ መቆየቱን አውስተው ከለውጡ በኋላ የማመጣጠን ስራዎች በመሰራታቸው ትልቅ ውጤት ተገኝቶበታል፤ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሠራዊቱ ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እንዲዘምን ሁለንተናዊ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.8K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 10:12:13
#Report

በዓለም ኣቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 የ24 ሰዓታት ሪፖርት፦

- በመላው ዓለም 14,996 ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 ሳቢያ ሞተዋል፡ 589,158 ሰዎች በቫይረሱ መያቸው ተረጋግጧል።

- አሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓት የ3,652 ዜጎቿን ህይወት ስታጣ፤ 169,033 ሰዎች ለቫይረሱ መጋለጣቸው ተረጋግጧል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 1,245 ሰዎች ሲሞቱ፤ 29,079 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ብራዚል 1,099 ዜጎቿን በ24 ሰዓት ውስጥ በኮቪድ-19 ስታጣ ፤ 58,691 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።

- ሜክሲኮ 1,506 ዜጎቿ ባለፉት 24 ሰዓት ሞተዋል፤ አጠቃላይ በሀገሪቱ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 155,145 ደርሷል።

- በኮቪድ-19 የሚሞቱባት ዜጎች ቁጥር እየጨመረ በመጣው ጀርመን ባለፉት 24 ሰዓት 832 ሰዎች ሞተዋል።

- ሩስያ 534፣ ፈረንሳይ 510 ፣ ስፔን 513 ፣ ጣልያን 477 ዜጎቻቸው በ24 ሰዓት ውስጥ ካጡ ሀገራት መካከል ናቸው።

- በደቡብ አፍሪካ የሟቾች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል፤ባለፉት 24 ሰዓት የተጨማሪ 528 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። ባለፉት 5 ቀናት ብቻ 2,759 ሰዎች ሞተዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ሪፖርት እንደሚያስረዳን 102,635,253 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፥ የ2,216,418 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 74,329,277 ሰዎች አገግመዋል።

ውድ የቲክቫህ አባላት ከወረርሽኙ እራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን ትጠብቁ ዘንድ አደራ እንላለን ፤ በሽታው ሳናውቀው በርካቶችን ከጎናችን እንዳያሳጣን እንጠንቀቅ ! ዘውትር የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ(ማስክ) ማድረጎን፣ የእጆን ንፅህና መጠበቆን፣በየትኛውም ቦታ ርቀቶን መጠበቆን፣ሰዎች በብዛት ከሚሰበሰቡበት ቦታ መራቆን አይዘንጉ።

መረጃው የቲክቫህ ነው

@ethio_mereja_news
13.6K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 19:00:06
በትግራይ ክልል በሰሜን እዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ተያይዞ 349 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ሲወጣ 124ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ!

በትግራይ ክልል በሰሜን እዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ተያይዞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግና የፌደራል ፖሊስ የደረሱበትን የምርመራ ውጤት ይፋ አደረጉ።

መግለጫውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ በጋራ ሰጥተዋል።

በዚህም በሀገር ክህደት ወንጀል፣ በሀገር ሉዋላዊነት ላይ በተቃጣ ጥቃት እና በሽብር ወንጀሎች የተጠረጠሩ 349 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸው ሲሆን 124ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ 680 የሰው እና የሰነድ ምስክርነት ቀርቦባቸዋል።

ከማይካድራ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘም 279 ሰዎች በወንጀሉ መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 36ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
15.1K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ