Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.41K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 514

2021-02-15 21:45:07
ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር «ወረራ ፈጽሞብኛል» ስትል ከሰሰች!

ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ድንበሬን ተሻግሮ «ወረራ ፈጽሞብኛል» ስትል ከሰሰች። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት እሁድ እንዳስታወቀው ድርጊቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረውን የድንበር ውዝግብ የሚያባብስ ነው ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ የሱዳንን ድንበር ተሻግራ መግባቷ አሳዛኝ ነው ያለው መግለጫው ውጤቱ አደገኛ እና ተቀባይነት የሌለው እንዲሁም በቀጣናው ደህንነት እና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሏል።

በኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቃባይ በኩል በጉዳዩ ላይ ለጊዜው የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም ቀደም ሲል የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ መግባቱን አስታውቆ ነበር።

የአሁኑ የሱዳን ክስ ከመሰማቱ በፊት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ቅዳሜ በፌስ ቡክ ገጹ እንዳስታወቀው ሱዳን ውስጥ ከጥቅምት ወር የመጨረሻ ቀናት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸሙ ዝርፍያ እና የማፈናቀል ተግባራት እንዲቆም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሱዳን መንግሥት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል።

አምባሳደር ዲና አያይዘው «ኢትዮጵያ የሁለቱን ሃገራት የድንበር ይገባኛል ጥያቄን በሦስተኛ ወገን መሸማገል አትፈልግም፤ የሱዳን ጦር በኃይል የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች ለቆ መውጣት ይኖርበታል ።» ማለታቸውም ተዘግቧል።

ሱዳን ባለፈው ወር « የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ድንበሬን ተሻግሮ ገብቷል » ስትል የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ድርጊቱን አስተባብሎ ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.0K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 18:05:10
ማባሪያ ያጣው የትራፊክ አደጋ!

በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 1121 የትራፊክ አደጋ መመዝገቡ የተነገረ ሲሆን በዚህም ምክንያት 449 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በሌላ በኩል 461 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ 487 ሰዎች ደግሞ ለቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከ28.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡

ለአደጋ መንስኤ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ቀዳሚው ሆኖ ስለመመዝገቡ አብመድ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.2K viewsedited  15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 17:21:13
ብልጽግና ፓርቲ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገለጸ!

ብልጽግና ፓርቲ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ወቅት የሚጠቀምበትን ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አህመድ፣ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የሚያሸንፉበት እንደሚሆን ገልጸው፣ ብልጽግና ፓርቲ የጀመረውን ውጥን አሳክቶ የሚያሳይ መሆኑን ያለፉት አመታት ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መጻኢ እድልና ተስፋ ብርሃን መሆኑን ለማመላከት የመወዳደሪያ ምልክቱ እየበራ ያለ አምፖል መሆኑን ያሳወቀው የብልጽግና ፓርቲ፣ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ፓርቲው የመወዳደሪያ ምልክቱን እየበራ ያለ አምፖል ያደረገበት ምክንያት ኢትዮጵያውያን ብርሃንን ተከትለው ወደ ብልጽግና መጓዝ እንዲችሉ እንዲሁም ህብረትን እና ውበትን ለማመላከት መሆኑ ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.6K views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 16:42:04
የሞቱ ሰዎች አስከሬን ተገኘ!

ቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል አካባቢ በባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ሹፍርና ላይ የተሰማራው ግለሰብ ከጠፋ ከቀናት በኋላ ህይወቱ አልፎ መገኘቱን የሹፌሩ የስራ ባልደረቦች ነግረውኛል ሲል አሐዱ ሬዲዮ ዘግቧል።

አቶ ንጉሴ መክብብ የሟች የስራ ባልደረባና ጓደኛ ሲሆኑ አቶ ማናየ እንየው የተባሉት የባጃጅ አሽከርካሪ በጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም መጥፋታቸውን ተናግረው የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም የሟች ሬሳ መገኘቱን ገልፀዋል።

ግለሰቡን ጨምሮ ሌላ አንድ በአሮጌ ዕቃ ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ግለሰብ አስከሬን አብሮ መገኘቱም ተነግሯል።

ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ በርካታ ሰዎች እየጠፉ እስካሁን አለመገኘታቸውን የተቀሱት የአከባቢው ነዋሪዎች የተጠናከረ ቁጥጥር ሊኖር እንደሚገባ ጠቁመዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.2K views13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 14:26:14
#ሰበር_መረጃ!

ኢዜማ አባሉ በጥይት ተመተው መገደላቸው አሳወቀ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ትላንት እሑድ ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳወቀ።

ኢዜማ አባሉ በማን እንደተገደለ ወይም በግድያው ዙሪያ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

ፓርቲው የተፈፀመውን የግድያ ወንጀል ያወገዘ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ አሰባስቦ እንደጨረሰ ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.7K views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 11:12:02
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐብይ አህመድ የፓርቲውን ማንፌስቶ እና የመወዳደሪያ ምልክት ዛሬ በይፋ አስተዋውቀዋል ።

ብልጽግና ፓርቲ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶ እና መወዳደሪያ ምልክቱን የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መድረክ ላይ ይፋ አድርጓል።

ፓርቲው "ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ባካሄደው መድረክ ላይ ነው የምርጫ ማኒፌስቶውን እና መወዳደሪያ ምልክቱን ይፋ ያደረገው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.3K viewsedited  08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-15 10:14:14
እንደብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ/የምርጫ ዘመቻ የሚደረግበት ጊዜ ነው።

በዚሁ በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ከግንቦት 24 - ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የማይቻልበት የጥሞና ጊዜ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.5K viewsedited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 17:10:12
206 የብሬን ጥይት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

ትላንት በሰቆጣ ከተማ 206 የብሬን ጥይት በህገ ወጥ መንገድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ የከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የፅህፈት ቤቱ እዳስታወቀው ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ በከተማው 02 ቀበሌ ውስጥ ነው።

የብሬን ጥይቶቹን 'በአገልግል' ውስጥ ደብቀው ሲንቀሳቀሱ የተያዙት ሁለቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ተሰምቷል። (ENA)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.6K viewsedited  14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-14 13:07:06
ሰላም የማስፈንና የማረጋጋት ጥረታችን ውጤታማ ሆኗል። -ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

"ሰላም የማስፈንና የማረጋጋት ጥረታችን ውጤታማ ሆኗል። ዛሬ ከሰላም ወዳዱ የደምቢዶሎ ሕዝብ ጋር በመሆን በቄለም ወለጋ 50 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለውን የደምቢዶሎ-ጋምቤላ ጎዳና አካል የሆነ የመንገድ ግንባታ አስጀምረናል። ቄለም ወለጋ በሀገራችን ከፍተኛ ዕድገት የማስመዝገብ ዐቅም ካላቸው ስፍራዎች አንዱ ነው።

የጋራ ሰላማችንን በማስጠበቅ፣ በጋራ የአካባቢውን ምርታማነት ለማሳደግ እንተጋለን" ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.6K viewsedited  10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 22:15:04
በትግራይ ክልል በዚህ ሳምንት በተነሳው ተቃውሞ ቢያንስ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ!

ከአዲስ አበባ የተላኩ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎችን ወደ መቀለ መምጣትን በመቃወምም ሰልፈኞች በጎዳናዎች ላይ ጎማ ሲያቃጥሉ እንዲሁም በርካቶች ቤት ውስጥ በመቀመጥ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል።

ልዑካኑ ከክልሉ የተለያዩ የማህበረሰብ አባላት ጋር የሰላም ውይይት ለማድረግ ነው የመጡት ተብሏል።

እንግዶቹ በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ምሽት፣ የካቲት 1/2013 ዓ. ም ላይ ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ተከትሎ ነዋሪው ላይ ቁጣ ማስከተሉን የአይን እማኞች ይናገራሉ።

በርካታ ተጋሩዎች የልዑካኑን ቡድን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተወሰደውን ወታደራዊ እርምጃ በመደገፍ ከመንግሥት ጎን ቆመዋል በማለት ይወነጅሏቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የክልሉን ህዝብ ጥሪ ችላ ብለዋልም ይሏቸዋል።

"መቀለ አሁንም ቢሆን ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ የሌለባት ከተማ ናት። የተወሰነ በሚባል መልኩ ወይም ደግሞ ምንም አይነት የሰዎች እንቅስቃሴ የለም።

ሱቆችም ሆኑ የግል ተቋማት ተዘግተዋል። በከተማዋ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም" በማለት አንድ ነዋሪ ለቢቢሲ በዚህ ሳምንት ረቡዕ ዕለት ተናግረዋል።

ከመቀለ በተጨማሪ በሽረ፣ አዲግራት እንዲሁም ከመቀለ 45 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ውቅሮ በተከሰተ ተቃውሞ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን የውቅሮ ነዋሪ የሆነና ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የህክምና ባለሙያ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
14.4K viewsedited  19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ