Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.41K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 511

2021-03-01 12:30:01 #ሰበር_ዜና

የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ወደ መጋቢት 16 ቀን ተዘዋወረ!

የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ቀደም ሲል ከተያዘለት የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም መዘዋወሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፡፡ የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን አውጥቶ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህም መካከል በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ ያለው የእጩዎች ምዝገባ አንዱ ሲሆን በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ተከታዩ ዋና ተግባር የመራጮች ምዝገባን ማከናወን ነው።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ተግባራትን ማከናወን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል የምርጫ ክልል ቢሮዎች ዝግጅት መዘግየት እና አስፈጻሚዎች ሰልጥነው ከተሰማሩም በኃላ ቢሆን ቢሮዎች ዝግጁ ሆነው ባለመገኘታቸው የቢሮ መከፈት መዘግየቱ፣ በተወሰኑ ክልልሎች አስፈላጊው ቢሮዎች ተዘጋጅተው ባለማለቃቸው የእጩዎች ምዝገባ በጊዜ ሰሌዳው መሰረት መጀመር አለመቻሉ እና ለሁለት ዙር መከፈሉ፣ ለምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት የትራንስፖርት እጥረት እና የገለልተኛ አስፈጻሚዎች ምልመላ ሂደት ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጊዜ የሚወስድ ተግባር መሆኑ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

በዚህም መሰረት ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን በመገምገም ተጨማሪ ቀናት እንደሚያስፈልገው በመረዳት በመጀመሪያ ዙር የእጩዎች ምዝገባ በተጀመረባቸው ክልሎች ለ4 ቀናት ያራዘመ ሲሆን፣ በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልሎችም ላይ የቢሮዎች ዝግጅት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ ችግር ሆኖ እንደነበር ተረድቷል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የገለልተኛ ምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ ተግባርንም እያከናወነ እንደሆነ ይታወሳል፤ 140 ሺህ በላይ እጩ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት የሚሰሩ ግለሰቦችን አዘጋጅቶ ገለልተኝነት ማጣራትን እያከናወነ ሲሆን፣ ይህም ከተጠበቀው ጊዜ በላይ ሊወስድ ችሏል።

በመሆኑም ከክልሎች የሚገኘው የቢሮዎች ትብብር በመዘግየቱ፣ የእጩዎች ምዝገባ ቀናት ከተጀመሩም በኋላ ዝግጁ ያልሆኑ የተወሰኑ ቢሮዎች የነበሩ በመሆኑ ፣ ፓለቲካ ፓርቲዎችም ተጨማሪ ቀናት በመጠየቃቸው እና የእጩዎች ምዝገባ በመራዘሙ፣ እንዲሁም በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ያጋጠመው የቁሳቁስ ማጓጓዝ ተግዳሮቶች በመገምገም እና የእጩ አስፈጻሚዎችን ገለልተኝነት የማጣራት ስራን በተሻለ ጥራት ለማከናወን የመራጮች ምዝገባን ከተያዘለት ቀን የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ መጋቢት 16 ቀን 2013 እንዲዘዋወር ወስኗል።

በመሆኑም የ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16- ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን ቦርዱ ለወደፊትም ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ መረጃዎችን የሚያቀርብ ይሆናል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.8K viewsedited  09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-01 11:26:11
ትራምፕ ዳግም ለፕሬዜዳንትነት ይወዳደሩ ይሆን ?

ዶናልድ ትራምፕ እአአ በ2024 እንደገና ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ፍንጭ መስጠታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ዶናልድ ትራምፕ ፍሎሪዳ በተካሄደ የወግ አጥባቂ የሪፐብሊካን ኮንፈረንስ ላይ የሪፓብሊካኖችን ድምጽ ሊከፋፍል ይችላል በሚል አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ የመመስረት ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸዋል።

ትራምፕ ዴሞክራቱ ጆ ባይደን ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው፤ የአሜሪካ ፖሊሲ "ከቅድሚያ ለአሜሪካ ወደ አሜሪካ መጨረሻ" ተቀይሯል ብለዋል ተተኪያቸውን አጥብቀው በተቹበት ንግግራቸው።

ትራምፕ ትናንት በተካሄደው በኮንሰርቫቲቭ ፖሊቲካል አክሽን ኮንፈረንስ (ሲፒኤሲ) ላይ መገኘታቸው በሪፐብሊካን ፓርቲ ላይ አሁንም ያላቸውን ተጽዕኖ ያሳያል ተብሏል።

ሐሙስ በተጀመረው ጉባኤ ለትራምፕ ድጋፍ የሚሰጥ ሲሆን የቴክሳሱ ሴናተር ቴድ ክሩዝን እና የትራምፕ ልጅ ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየርን ጨምሮ ሌሎችም ደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።

(BBC)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2.9K viewsedited  08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-01 10:24:10
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአልሸባብ ታጣቂዎች ላይ በወሰደው እርምጃ ዘጠኝ የቡድኑን አባላት ገደለ !

በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ሀይል ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአልሸባብ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ ዘጠኝ ታጣቂዎችን ገደለ።

በሶማሊያ ደቡባዊ ምስራቅ በሰራዊቱ የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅት ሲያደርግ በነበረው አልሸባብ የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደው እርምጃ በጥቂቱ ዘጠኝ ታጣቂዎች ሲገደሉ ከ11 በላይ የሚሆኑት ቁስለኛ ሆነዋል ነው የተባለው።

በባይ ክልል የከሳህደር ከተማ የደህንነት ምክትል ኮሚሽነር መሀመድ ሙክታር በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እርምጃ መውሰዱን አረጋግጠዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአልሸባብ ቡድን ላይ ይህን እርምጃ በመውሰዱ ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን ሚዲል ኢስት ሞኒተር እና ጋሮዌ ዘግበዋል።

የከሳህደር ከተማ አስተዳደር ኮሚሽነር አብደራዛቅ አብዲ አስተዳደራቸው እና የክልሉ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና በህብረቱ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አልሸባብ ጥቃት ሊያደርስ እንደሚችል መረጃው ደርሷቸው እንደነበረ መገለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.2K viewsedited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-01 08:18:03
በምስራቅ ወለጋ 11 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

ባለፈው ሀሙስ ዕኩለ ቀን የኦነግ ሼኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አስራ አንድ ሰዎች ሲገደሉ ከሀያ በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዋዜማ ራዲዮ ገልፀዋል። እስከ ዓርብ ከሰዓት በኋላ ድረስ የሟቾቹ አስከሬን አለመነሳቱን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የኦነግ ሼኔ ታጣቂዎች በድጋሜ ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ በሚል ነዋሪዎች ቀበሌውን ለቀው እየወጡ መሆኑንም ለዋዜማ ገልፀዋል። በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ሀላፊዎች የችግሩን መከሰት አምነው ዝርዝሩን ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

በቅርቡ የመከላከያ ሀይል በኦነግ ሽኔ ታጣቂዎች ላይ የከፈተውን ሰፊ ዘመቻ ተከትሎ ታጣቂዎቹ ይዞታቸውን ለቀው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየሸሹ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

[ዋዜማራዲዮ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.3K viewsedited  05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 21:37:31 እንደምን አመሻቹ

ይህ ዩትዩብ ቻናል ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮ መረጃ NEWS የተከፈተ #YouTube ነው subscribe በማረግ የድምፅ መረጃዎችን ያገኛሉ

#Subscribe ያርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg
638 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 20:21:20 ኦፌኮ እና ኦነግ በዘንድሮው ምርጫ ባንሳተፍም ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ።

መንግስት በፓርቲያቸው ላይ የሚያደርገውን ማዋከብ እና እስር እስካላቆመ ድረስ በምርጫው ለመሳተፍ እንደማይሞክሩ ኦነግና ኦፌኮ ተናግረዋል።

በስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚወዳደሩ የእጩዎች ምዝገባ ከየካቲት 08 እስከ 21 ድረስ ተካሄዶ ባሳለፍነው ቅዳሜ መጠናቀቁ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን በመገምገም የምርጫ ክልል ቢሮዎች ለመከፈት በመዘግየታቸው፣ የትራንስፓርት መጓተት የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ የምዝገባ ቀንን በማራዘሙ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች እጩዎችን ለመመዝገብ ችግር ስላጋጠመን ይራዘምልን ብለው መጠያቃቸውን ተከትሎ ለአራት ተከታታይ ቀናት አራዝሚያለሁ ሲል አስታውቋል፡፡

በዚህ የመጀመሪያ ዙር እጩዎችን ካላስመዘገቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ና የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ይገኙበታል ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም በጉዳዩ ላይ ፖርቲዎቹ ምን እንደሰሩ ጠይቋል፡፡

የኦፌኮ ተቀዳሚ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ቀናቱ ቢጨመሩም ባይጨመርም ለውጥ አይመጣም ብለዋል፡፡

መንግስት የጠየቅናቸውን ነገሮች ከግምት እስካላስገባ ድረስ ምን ይዘን ነው የምንገባው ብለው ጠይቀዋል ፡፡

"እጩዎቻችን በእስር ላይ ሆነው ፤ ቢሮዎቻችንም ቢሆኑ ሆን ተብሎ እየተዘጉ መወዳዳር አንችልም" ሲሉም ፕሮፌሰር መረራ ተናግረዋል፡፡

ከበርካታ ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ለመወዳደር የተዘጋጀው ኦነግ ፤ በአባሎቹ ላይ የእስር እና የእንግልት ዘመቻው እንደቀጠለ ተናግሯል፡፡

ምንም ለውጥ ባለመኖሩ የተነሳም በዚህ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ከእኔ ይልቅ መንግስት ወሳኝ ሆኗል ብሏል ኦነግ፡፡

በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከፍተኛ ግምት ከሚሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የነበረው ኦነግ በውስጣዊ ችግሮቹ እና በፓርቲ አመራሮች እስር ታጅቦ ምርጫውን ሲጠብቅ እንደነበር ተናግሯል፡፡

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ቃላ ቀባይ የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ እስርን ጨምሮ ጽህፈት ቤቶቻችን ተዘግተው አልቀዋል ብለውናል፡፡

ሁኔታው ገዢው ፖርቲ ብቻውን ለመወዳር መወሰኑን አሳይቷል ይላሉ አቶ በቴ፡፡

ኦነግ በመንግሥት ይደርስብኛል በሚለው ጫናና በአመራሮቹ መካከል የተፈጠረው ቅራኔ በምርጫ ተሳትፎው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረበትም ተናግሯል፡፡

የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ በቴ በዚህ ምርጫ ባንሳተፍም ሰላማዊ ትግላችን ግን ይቀጥላል ብለዋል ፡፡

ምርጫ አንዱ የትግል መንገድ እንጂ ብቸኛ አይደለም የሚሉት ቃል አቀባዩ መሳሪያችንን ጥለን ወደ ሀገር የገባነው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ነው ብለዋል ፡፡

ይህንንም እያደረግን ነው የሚሉት አቶ በቴ ደጋፊዎቻችንም ሆኑ አባሎቻችን ይህንን ተገንዝበው ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀጥሉ አድርገናልም ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ምክትል ቢሮ ሀላፊው አቶ ግዛቸው ጋቢሳ በበኩላቸው ፓርቲዎቹ እያሰሙ ያሉት ቅሬት ትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ የተዘጋ የማንኛውም ፓርቲ ጽህፈት ቤትም ሆነ አባል የለም የሚሉት አቶ ግዛቸው ህግ ከተጣሰ ግን የብልጽግና አመራር እና አባላትን ጨምሮ ማንኛውም ግለሰብ በህግ ይጠየቃል ብለዋል።

በክልሉ ቅሬታ ካላቸው ፓርቲዎች በተጨማሪ ሌሎች ፓርቲዎች የምርጫ ዝግጅታቸውን በማካሄድ ላይ እንደሆኑም አቶ ግዛቸው ተናግረዋል።

(ethio fm)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.2K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 16:36:58 ከ1 ሚሊየን በላይ ብር የሚገመት የዲሽ የሳተላይት መፈለጊያ ቁሳቁሶች በህገወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል ተያዘ፡፡

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠርያ ጣብያ ለኢትዩ ኤፍ ኤም እንዳሳወቀው በቀን 19/06/2013 ዓ.ም ሌሊት 10:45 ላይ በኮንትሮባንድ ቁጥጥር ክትትል እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ መያዝ ተችሏል።

ህገወጥ የመድሀኒት ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የተፈፀመበት የጭነት መኪና ኮድ 3 አዲስ አበባ 98866 መሆኑን ተነግሯል፡፡

989 ብዛት ያላቸውን የዲሽ የሳተላይት ፉይንደር በኮድ 3 አዲስ አበባ 63158 በሆነ ፒክ አፕ ተሽከርካሪ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የጉሙሩክ መቆጣጠርያ ጣቢያዎች የስራ ሂደት ኃላፊ አቶ ዋርዮ ጉዮ ለጣቢያችን ገልጸዋል። በተጨማሪም ኃላፊው አቶ ዋርዮ ጉዮ 10 ኪሎ ግራም የካናቢስ እፅ መያዙንም አሳውቀዋል።

ህገወጥ የመድሀኒት ዝውውር በቁጥጥር ጣቢያው በተደጋጋሚ መከሰቱን የሚናገሩት አቶ ዋርዮ ማህበረሰቡም መድሀኒቶችን ህጋዊ ተቋሞች ወይም ፋርማሲ መደብሮች እንዲገዛ አሳስበዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.8K viewsedited  13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 15:05:31 አንድ ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ሺሻ ሲያዘዋውሩ የነበሩ አሽከርካሪና ረዳቱ ተያዙ!

አንድ ሚሊየን ብር ግምት ያለው ሺሻ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት የሞከሩ አሽከርካሪና ረዳቱን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምርያ የኮሚኒኬሽን ሚዲያ ዲቪዥን አባል ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት ትላንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ነው።

ተሽከርካሪው 162 ካርቶን የሺሻ አፕል ጭነው ከወሊጪቲ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት ሲሞክሩ መያዛቸውን ተናግረዋል።

በከተማው ደምበላ ከፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ ልዩ ቦታው ፈጣን መንገድ በተባለ አካባቢ መያዛቸው የገለጹት ረዳት ኢንስፔክተሯ ፖሊስ አሽከርካሪና ተረዳቱን በቁጥጥር ሰር አውሎ ለህግ ለማቅረብ ምርመራ መጀመሩን አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ ትውልድን የሚያበላሽና ወደ ወንጀል እንዲገቡ የሚያደርግ እፅ ዝውወር ለመከላከል ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ረዳት ኢንስፔክተሯ አስገንዝበዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
3.2K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-28 14:54:10
አሜሪካ በትግራይ ዙሪያ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች እንደሚያሳስባት ተገለፀ!

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ክልል ውስጥ የተፈጸሙ ጭካኔ የተሞላበት ሪፖርቶች በጣም አሳሳቢ መሆኑን ገለፁ፡፡

ግድያዎችን ፣ በግዳጅ መወገድን ፣ ወሲባዊ ጥቃትን እና ሌሎች የሰብአዊ መብቶችን መጣስ አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል ፡፡

ዓለምአቀፉ ማህበረሰብም ተጨማሪ ጥቃቶችን ለመከላከል በጋራ መስራት አለበት ብለዋል ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
3.4K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 22:06:20
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ተማሪዎቹን በራሱ ዩኒቨርሲቲ ሊጠራ መሆኑን አሳወቀ !

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ዝርፊያና ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ ዛሬ በነበረው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ስነስርዓት ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ዩኒቨርሲቲውን ወደነበረበት የቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ያሳወቁት ፕሮፌሰሩ የሁሉም አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን አጠናቆ ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ እንደሚጠራቸው ፕ/ር ገብረእየሱስ አሳውቀዋል።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ላይ በደረሰው ውድመት እና ዝርፊያ ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው ለ12ኛ ጊዜ ያስመረቃቸው ተማሪዎች ያላጠናቀቁትን ትምህርት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በመማር ነው አጠናቀው የተመረቁት።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የዩትዩብ ገፃችን #subscribe ያርጉ

https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.6K viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ