2021-03-01 20:22:07
#Adwa125
የአድዋ በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ይዘጋሉ።
በምኒሊክ አደባባይ የሚካሄድ ፕሮግራም እስከሚጠናቀቅ ፦
- ከደጎል አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደበባይ የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ
- ከራስ መኮንን ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከአፍንጮ በር ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር
- ከአዲሱ ገበያ ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሰሜን ሆቴል
- ከመርካቶ በአቡነጴጥሮስ ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን አደባባይ
-ከቸርችር ጎዳና ወደ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ዝግ ይሆናል፡፡
በመስቀል አደባባይ ለሚከናወነው ፕሮግራም ፦
-ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር
-ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ቅዱስ ኡራኤል ቤተ- ክርስቲያን
- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሄራዊ ቤተ-መንግስት መስቀለኛ
- ከቸርችር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ መብራት
- ከሚክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ለገሃር መብራት
- በሰንጋተራ ፣ በኮሜርስ ፣ በቴሌ ባር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኢትዩጵያ ንግድ ባንክ
- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር ጋር ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡
ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች ብቻ እንዲጠቀሙ ተብሏል።
በዓሉ በሚከበርባቸው ቦታዎች ከማለዳው 11፡30 ሠዓት ጀምሮ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ክልክል ነው።
በሌላ በኩል
መልዕክት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፦
- 125ኛ የአድዋ በዓልን ለመታደም ወደ ዝግጀቱ ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ ስለሚኖር ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
- በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ከበዓሉ ጋር ተፃራሪ የሆኑ መልዕክቶች ፣ ህጋዊ ከሆነው የፌደራል መንግስት እና የክልል መንግስታት ሰንደቅ ዓላማ ውጪ ይዞ መንቀሳቀስ ፍፁም የተከለከለ ነው።
- ህብረተሰቡ ለጸጥታው አጠራጣሪ የሆኑ ማንኛውም ነገሮች ሲያጋጥሙት ወይም የፖሊስ አገልግሎትን ማግኘት ሲፈልግ በ011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም ይችላል።
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
1.1K views17:22