Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.41K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 512

2021-02-27 20:34:14
ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለትግራይ መልሶ ማቋቋም የሚውል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ!

ድጋፉ ክልሉን መልሶ ለመገንባት ሁሉም እንዲረባረብ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

በትግራይ ክልል የተካሄደውን የሕግ ማስከበር ስራ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያግዝ የቆየው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሁንም የክልሉ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ኑሮው እስኪመለስ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ድጋፉ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አለመሆኑን መሆኑን ተናግረው ተቋሙ ወደፊትም የክልሉን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መደገፉን እንደሚቀጥልበት ገልፀዋል።

አሁን ወቅቱ የትግራይ ህዝብ ከሁሉም ወገኖቹ ወንድማዊ ፍቅርና ድጋፍ የሚፈልግበት ነው ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በበኩላቸው ድጋፉ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለትግራይ ህዝብ ያለውን አጋርነት ያሳየበት መሆኑን ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.0K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 19:48:16
ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ስናይፐር፣ ብሬን፣ ሽጉጥና ከ5 ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጥይቶች ተያዙ!

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል ከጭነት ጋር ተመሳስሎ በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ስናይፐር፣ ብሬን ፣ ሽጉጥ ፣ ከ5ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጥይቶች እንደተያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡

መነሻውን ጎንደር ያደረገ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 99483 አይሱዙ ተሽከርካሪ በጉሌሌ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መንደር ሰባት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት መያዙ ነው የተገለጸው።

በተደረገው ክትትልም 2 ብሬን ፣ 2 ስናይፐር ፣ 38 ትልቁ እና 25 ትንሹ ኢኮልፒ ሽጉጦች ፣ 5992 የክላሸ ኮቭ ጥይት ፣ 892 የኢኮልፒ ሽጉጥ ጥይት ፣ 5 የስናይፐር ጥይት ፣ የብሬን እግር እና ሁለት የብሬን ዝናር ህገወጥ የጦር መሳሪያውን ሲያዘዋወሩ ከተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ 2 ሺህ ተተኳሽ የክላሽንኮቭ ጥይቶችን በድብቅ ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.5K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 19:28:09
በኮምቦልቻ ከተማ ተተኳሽ ጥይቶች ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሁለት ሺህ ተተኳሽ የክላሽንኮቭ ጥይቶችን ሸሽገው በድብቅ ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የታክቲክ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ሰይድ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ጥይቶቹን ትናንት በከተማው ቀበሌ ሶሰት አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በድብቅ ሲገበያዩ እጅ ከፍንጅ ተደርሶባቸው ነው።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረትም ሻጭ፣ ደላላ እና ገዥ በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስረድተዋል።

አስፈላጊውን ማጠራት በማድረግ ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት እንዲያገኙም ይደረጋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ ለሀገር አንድነትና ሰላም ሲባል ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሆን ህገ ወጥ ተግባራት በማጋለጥ እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮማንደር አሊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.3K views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 18:30:09
በአዲስ አበባ ከተማ ሁለት የህዝብ መናፈሻዎች ተመረቁ!

-በመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከንቲባ ቢትወደድ ወልፃዲቅ ስም የተሰየመው ፓርክ እና አምባሳደር የህዝብ መናፈሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ዣንጥራር አባይ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ፣ የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት ተፈራ ዋልዋ እና አሊ አብዲ እንዲሁም ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ የመጀመሪያው ከንቲባ በነበሩት ከንቲባ ቢትወደድ ወልደፃዲቅ ጎሹ መኖሪያ ቤት እና በቅርስነት ተመዝግቦ በሚገኘው አራት ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ከንቲባ ቢትወደድ ወልደፃዲቅ ፓርክ በ101 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፓርኩ የጅምናዚየም ፣የህፃናት መጫዎቻዎች፣ የማንበብያ ስፍራና ሌሎችም አገልግሎቶችን ያካተተ ነው ተብሏል።

አምባሳደር መናፈሻ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም የሚሰጠው አገልግሎት ዘመኑን የተከተለ ባለመሆኑ እንዲታደስ ተደርጓል።

49 ሚሊየን ብር ወጭ የተደረገበትና አንድ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው አምባሳደር የህዝብ መናፈሻ የልጆች መጫወቻ ፣የማንበቢያ ክፍል፣ አካል ጉዳተኞች ታሳቢ ያደረገ የውስጥ ለውስጥ መንገድና ሌሎችም አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.9K views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 14:30:39 በትግራይ ቀውስ የምግብ እጥረትን ለመዋጋት 100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ መርሃግብር(WFP) ይፋ እንዳደረገዉ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል በትግራይ ክልል ከባድ የመሰረታዊ ፍላጎቶችን እጥረት ለማቃለል ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ አስቸኳይ ጥሪ አቅርቧል ፡፡

ኤጀንሲዉ ሶስት ሚሊየን የክልሉ ነዋሪዎች ወይም 50 በመቶ ያህሉ አፋጣኝ የምግብ ድጋፍ ያሻቸዋል ብሏል፡፡ባለፈው ሳምንት የአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የፍላጎት መጠነ ሰፊ እንደሆነ መግለጹ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.8K views11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 12:41:04 መንግስት ምላሽ ሰጠ/የኤርትራ ምላሽ"

ሙሉ መረጃው ከስር የሚገኘው link በመጫን ይመልከቱ

on YouTube



9.0K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 12:29:08
ዳንኤል ክብረት በግሉ ምርጫ ይወዳደራል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሀይማኖት መምህርነቱና በሚሰጣቸው ማህበራዊ ሂሶች ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጪው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በግሉ እንደሚወዳደር ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች።

ዳንኤል ክብረት ምርጫውን የሚወዳደረው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር ለማግኘት ሲሆን ፣ የሚወዳደረውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ባለ የምርጫ ክልል መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

ዳንኤል ክብረት ከመንግስት ጋር በቅርበት እየሰራ ከመሆኑም ባለፈ በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሆኖም እያገለገለ ይገኛል። ከዚህ በመነሳትም ምርጫ የሚወዳደረው ብልጽግና ፓርቲን ወክሎ ነው በሚል ብዙዎች ቢገምቱም በግሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚወዳደር ነው ዋዜማ ራዲዮ የሰማችው።

ዳንኤል ክብረት መንግስትን አሁን ላይም እያገለገለ ያለው ከፓርቲ ነጻ ሆኖ በፈቃደኝነት ስለሆነ ምርጫውን በግሉ መወዳደር የፈለገው ከዚህ መነሻ መሆኑንም ነው የተሰማው።

ዘገባው የዋዜማ ራዲዮ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.7K views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 12:15:21 ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ3ሺ 700 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው !

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ3ሺ 700 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርስቲው እያስመረቃቸው ያሉ ተማሪዎች በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ሲሆን ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አቋርጠው የነበሩና በተያዘው አመት ያጠናቀቁ ናቸው።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የፌዴራል እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.2K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 09:06:07
እንደምን አደራቹ የሀገሬ ልጆች

በያላቹበት ሰላማቹ ይብዛልን እያልን
*ዛሬም እንደተለመደው ወደ እናንተ አዳዲስ ዜናዎችን የምናስደምጣቹ ሲሆን

ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የያዝናቸው ዜናዎችን የምናስደምጣቹ ይሆናል

በሌላ በኩል ወደ ዩትዩብ ገፃችን ዛሬ ጎራ ካላቹ ያልተሰሙ ዜናዎች የምናስደምጣቹ ይሆናል

#youtube ገፃችን ከስር ያገኙታል subscribe እንድታረጉም እናሳስባለን

https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg
9.2K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 21:40:05 መታየት ያለበት ዜና/ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን/እነ ስብሀት በግል ሀኪማቸው እንዲታከሙ/የ3ዓመት ህፃን የደፈረው"

ሙሉ ዜናውን ይመልከቱ

on YouTube



10.2K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ