Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.41K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 516

2021-02-12 16:11:07
ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊነት ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ!

ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊነት መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነጻ እና ፍትሀዊ እንዲሆን፣ ውጤቱም በመራጮች፣ በተፎካካሪ ፓርቲዎች እና በታዛቢዎች ተቀባይነት እንዲኖረው የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

ምክር ቤቱ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ሁለንተናዊ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ መንግስትን አሳስቧል፡፡

በህግ ማስከበር ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸውና ችግር ውስጥ ላሉ አካላት የሚመለከተው አካል ሁሉ ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በተጨማሪ በትግራይ ክልል ደርሷል ተብሎ በተለያዩ አካላት የተገለጹ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት በአስቸኳይ ተጣርተው ውጤቱ ለህዝብ እንዲገለጽ አሳስቧል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.0K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 15:37:07
በመተከል ዞን 120 ሽፍቶች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ!

በቤኒሻንጉል ጉሚዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ 120 ሽፍቶች በዞኑ ለተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ፡፡

የምዕራብ ዕዝ ህብረት ዘመቻ ኃላፊ ተወካይ ኮ/ል ፋሲል ይግዛው፣ ሽፍቶቹ በህወሓት ቡድን የሀሰት ትርክት ጫካ ገብተው እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

በጫካ የነበሩ የሽፍታው ቡድን አባላት በሠላማዊ መንገድ እንዲገቡ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ እንዲሁም ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ እንደሰሩ ተገልጿል።

በጫካ ሽፍቶችን ሲመራ የነበረው ላቀው ደረጄ እና አዲሱ ፈጠነ በሰጡት አስተያየት፣ የህወሓት ቡድኑ መቐሌ በመጥራት ሲያሰለጥናቸው እንደነበረ ተናግረው፣ አሁን ግን በአካባቢያቸው በተጀመረው የሠላም እና የልማት እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ለመሆን እጃቸውን መስጠታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.7K views12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 14:55:09
“ልዩነት ሳይኖራችሁ ለአላማችሁ በፅናት ቁሙ” ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ ይህንን ያሉት ሠላም ለማስከበር ወደ ደቡብ ሱዳን ለሚያመሩ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻላቃ አባላት ነው።

ወደ ጁባ ለሰላም ማስከበር የሚዘምቱ የሠራዊት አባላት በበኩላቸው በሄዱበት ሁሉ ስኬታማ ሥራ በመሥራት የሀገራቸውን ሥም ለማስጠራት ዝግጁ ነን ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.7K views11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 14:28:15
አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ወደትግራይ ክልል በመግባት የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ ተሰጥቷል- የሰላም ሚኒስቴር

የሰላም ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሰላም ማስከበር ሂደቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ላለፋት 3 ወራት የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዩ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ26 በላይ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጥምረት የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ተግባራን ለማገዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።

ባለፉት 3 ወራት በተለያዩ ጊዜያት ቦታው ተገኝተው ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች አለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 75 አባላት ወደትግራይ ክልል መግባትና የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት (UN-OCHA) በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል (ECC) በምክትል ሰብሳቢነት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፉንና የመልሶ ማቋቋም ሂደቱን የማስተባበር ሂደቱን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅንጅት እያስተባባረ እንደሚገኝም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.0K views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 12:54:03
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ወላጆች እና ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ !

ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 በወረቀት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በቂ የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ወላጆች እና ማህበረሰቡ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡

በጋምቤላ ክልል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናውን በመደበኛ፣ በግል እና በማታ 3653 ያህል ተማሪዎች ይወስዳሉ።

ለፈተናው 17 የፈተና ጣቢያዎች ዝግጁ መሆናቸውን ተገልጿል።

ፈተናውን ለመስጠት ልዩ ልዩ የፈተና ቁሳቁሶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የፈተና ሂደቱን ሊያስተባብሩ የሚችሉ አካላትን የመምረጥ ስራ እንደሚከናወን ክልል አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.1K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 11:42:10
"ሼር አድርገን እንሳፈር" ከሚሉ ዘራፊዎች ይጠንቀቁ !

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ የቀረበ)

በአዲስ አበባ ከተማ ዕለት ተዕለት የረቀቁ ወንጀሎች ይፈጸማሉ ሰሞኑን ተፈጸመ የተባለ አንድ ወንጀልን ለጥንቃቄ ይረዳቹ ዘንድ ላካፍላቹ።
ማለዳ ጠዋት በስራ መግቢያ እና መውጫ የሚገጥመን የትራንስፖርት ችግር አለ።

ትራንስፖርት በምንጠብቅበት ስፍራ አከባቢም የተለያዩ አጨበርባሪ ሌቦች ፈንጠር ፈንጠር ብለው ይቆማሉ። (ሌቦቹ የጾታ ልዩነት የላቸውም)እርሶም በትራንስፖርት ጥበቃ ላይ እያሉ አንዱ(አንዷ)ወደ እርሶ ጠጋ በማለት "ለምን ሼር አድርገን በኮንትራት አንሄድም"በማለት ሀሳብ ይቀርባል። እርሶም በሀሳቡ እንደተስማሙ የሌቦቹ ተባባሪዎች ወደ እርሶ ጠጋ በማላት በሀሳቡ ይስማማሉ።

በቀጣይም በስልክ እና በአፕልኬሽን የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ወደ ሚገኙት ካንፓኒዎች አንዱ ጋር እንዲደወል በመነጋገር ብዙም ሳይቆይ ተደወለለት የተባለው መኪና እርሶ ከቆሙበት ስፍራ ይደርሳል።

የፊት መቀመጫውን ከሌቦቹ አንዱ ቀድሞ በመያዝ እርሶ እና ቀሪ ሌቦቹ ግን ከጀርባ ካላው ወንበር ላይ እርሶን ከመሀል በማድረግ ጉዞ ይጀመራል። ነገር ግን እዚህ ላይ ማወቅ ያለቦትን አንድ ጉዳይ እናሳውቆት ቀደም ሲል ስልክ በመደወል መኪና እንደሚያዝ በማስመሰል የደወለው ግለሰብ የሌቦቹ ተባባሪ ሲሆን ስልክም የደወለው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ወዳሉት ካንፓኒዎች አይደለም።

በቀጣይም የተሳፈሩበት መኪና ሹፌሩም ተሳፋሪውም ዘራፊ ሊሆኑ ስለሚችሉ ፍጹም ከማያውቋቸው ሰዎች ጋር በኮንትራት ባይሳፈሩ ይመረጣል። በተለይ ከ12ሰዓት በኾላ ስለዚህ ከእንዲህ ዓይነቶቹ ሌቦች እንዲጠነቁ ይህንን ጥቆማ ወደ እናንተ አደረስን። #tikvah

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.5K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 10:27:11
ሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት መውረሯን እንደቀጠለች ነው!

የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝደንት ኦማር ሃሰን አልበሽር በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ ስልጣን የተቆናጠጠው አዲሱ አስተዳደር የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት በወታደራዊ ኃይል የመውረር እንቅስቃሴውን አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው ከሆነ የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል በሁለቱ አገራት ድንበር አካባቢ ተጨማሪ 50 ሺህ ሄክታር መሬት በመውረር በቁጥጥሩ ስር እንዳዋለ መረጃ አግኝቻለሁኝ ሲል ዘግቧል።

የሱዳን ወታደራዊ ኃይል እንደ አዲስ በተቆጣጠረው በዚህ አካባቢ ላይ ከኢትዮጵያ በኩል ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትን ለመከላከል ወታደራዊ ካምፕ እንዲመሰርት የሚጠይቁ ስለመኖራቸውም ተነግሯል።

ኢትዮጵያ ጉዳዩን በንግግር ለመፍታት ዝግጁ እንደሆነችና ከዚህ ቀደምም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ በንግግር ለመፍታት ለሱዳን ጥያቄ ብታቀርብም ሱዳን አሻፈረኝ ማለቷ የሚታወቅ ነው።

ሱዳን እያካሄደችው ላለችው ወረራ እስካሁን ድረስ ጠንከር ያለ ወታደራዊ የአፀፋ ምላሽ ያልሰጠችው ኢትዮጵያ ትዕግስትንና እንነጋገር ማለትን ከፍርሃት አትቁጠሩት እያለች ነው።

ከዚህ ቀደም የሱዳን ምክር ቤት የበላይ ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ሱዳን ሰራዊቷን ወደ ድንበር ያስጠጋችው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጥያቄና ፈቃድ ነው ማለታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ለዚህም ምላሽ የሰጡት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ "ቅዠት ነው" ካሉ በኋላም "አጥፊ ኃይሎች የናንተን ድንበር ተጠቅመው ወደኛ ድንበር እንዳይገቡ ማለት ኑና ገብታችሁ ጭራሽ ያልተከለለና መቶ አመት በዚሁ ሁኔታ ይሁን ተብሎ የቆየውን መሬት ድንበር የኛ ነው በሉ ማለት አይደለም" ሲሉ መልሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.6K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-11 17:02:09 በትግራይ ክልል ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ ብቻ 108 የአስገድዶ ደፈራ ወንጀሎች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከጥር 2 ቀን እስከ ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ እና በደቡባዊው የትግራይ ዞን አላማጣ፣ መሆኒ እና ኩኩፍቶ ከተሞች ክትትል እና ምርመራ በማድረግ፣ በተለይም በመቀሌ የሚገኙ ከፍተኛ ወታደራዊ እና ሲቪል አመራሮችን፣ የጤና ዘርፍ ሰራተኞችን፣ ነዋሪዎችን፣ ተጎጂዎችን እና ተፈናቃዮችን አነጋግሬያለሁ ብሏል።

ኢሰመኮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ በትግራይ ክልል መቀሌን ጨምሮ በአራት ሆስፒታሎች በተገኘ መረጃ መሰረት ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ ብቻ 108 የአስገድዶ ደፈራ ወንጀሎች ተፈጽመዋል።

እንዲሁም በመቀሌ እና የኢሰመኮ ክትትል ቡድን በተዘዋወረባቸው አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ በማዳረስ ረገድ አበረታች እርምጃዎች አሉ ብሏል።

ይሁንና አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎቱ አሁንም አልተሟላም ያለው ኮሚሽኑ ከሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ወደ መቀሌ የተፈናቀሉ ሰዎች የምግብ፣ የንጹሕ መጠጥ ውሃ እና የጤና አገልግሎት አቅርቦት እጥረት አለባቸው።

በተለይም በሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና የጤና ተቋማት አገልግሎት መቋረጥ፣ ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች የህክምና እርዳታ ለማግኘት ረዥም የእግር መንገድ እንዲያደርጉ አስገድዷል።

ኢሰመኮ በአይደር ሆስፒታል የሕፃናት ተኝቶ መታከሚያ ከፍልን በጎበኘበት ወቅት፣ ተኝተው በመታከም ላይ ከነበሩት 20 ከፍተኛ የአዕምሮ ጭንቀት እና ድንጋጤ (trauma) ታካሚ ሕፃናት መካከል 16ቱ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።

ከሕፃናቱ መካከል እጃቸውን፣ እግራቸውንና እና አይናቸውን ጨምሮ የአካላቸውን ክፍል ያጡ ወይም የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት የደረሱባቸው የሚገኙ ሲሆን፣ በተለይ በሕፃናት ላይ ለደረሱት ጉዳቶች አንዱ ምክንያት በመሬት ውስጥ “የተቀበሩ እና በሜዳ ላይ የተጣሉ ፈንጂዎች” የሚደርስ ጉዳት ነው።

ትግራይ ክልል የመሰረታዊ ልማት፣ የማኅበራዊ እና የአስተዳደራዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ የመመለሱ ተግባር ልዩ ትኩረት ይሻል ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

via ኢትዮ ኤፍ ኤም

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.8K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 20:37:03
በአዲስ አበባ ቅዳሜ እና እሁድ የደረሱ የእሳት አደጋዎች ፦

#1

በጉለሌ እጸዋት ማእከል የደረሰው የእሳት አደጋ 2 ሄክታር ቦታ የሸፈነ ነው። በአደጋው ከ200 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፤ ምን ያህል ንብረት ከውድመት እንደተረፈ ለጊዜው አልታወቀም።

#2

በጉለሌ ክፍል ከተማ ወረዳ አምስት ጽዮን ሆቴል አካባቢ በአንድ ሼድ ላይ በደረሰው የእሳት አዳጋ ከ50 ሺህ ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ለውድመት ሲዳረግ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን ተችሏል፡፡

#3

በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ኮሎምብያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመኖርያ ቤት ላይ በደረሰ አደጋ 20 ሺህ ብር በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል፡፡

#4

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ማርያም አካባቢ በአንድ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 100 ሺህ ብር በሚጠጋ ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ከውድመት ማዳን እንደተቻለ ተችሏል።

#5

በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ማርያም አካባቢ ላይ በሚገኝ የእንጨት ክምር ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጋ ንብረት ሲወድም ወደ አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል።

#6

በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 "እፎይታ የገበያ ማዕከል" ላይ በሚገኙ ሱቆች ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የጉዳት መጠን በማጣራት ላይ ይገኛል።

* ዛሬ ሰኞ ቦሌ ዘሀብ ሆቴል ፊት ለፊት እና ኡራኤል አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር (የጉዳት መጠን አልታወቀም)

(የእሳትና የአዳጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን)
Compiled By: ETHIO FM 107.8/tikvah

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.7K viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 19:04:24
አቶ ልደቱ አያሌው በምርጫ የሚሳተፉ ከሆነ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባነት ሊሆን እንደሚችል

የኢትዬጵያውያን ዴሞክራያዊ ፓርቲ መስራች እና የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያለው በዘንድሮ አመት በሚካሄደው 6ኛው ሐገራዊ ምርጫ ላይ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

የጤና ሁኔታቸው ምርጫው ላይ መወዳደር የሚያስችላቸው ከሆነ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት ሊወዳደሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት አቶ ልደቱ በሐገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ምርጫ ብዙም ፋይዳ አለው ብለው እንደማያምኑ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.7K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ