Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.41K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 515

2021-02-13 16:48:14
በአዲስአበባ ከ2ሚሊዮን ጄሪካን በላይ በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸ ፓልም የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ!

በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ጀሞ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት ሊያዝ የቻለው ፌዴራል ፖሊስ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ጥብቅ ክትትል ነው፡፡ (ኢቢሲ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
14.4K views13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 15:27:07
በ24 ሰዓት ውስጥ አራት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያንን ተያዙ

በአዲስ አበባ ከተማ በማታለል ወንጀል ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያን የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ አገራት የገንዘብ ኖቶችን በ24 ሰዓት ውስጥ እያባዛን እንሰጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጋር በጋራ በተደረገ ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

በፓስፖርት ስማቸው ናዋ ሳምፕሰን እና ጁዲ አያምባንግ ተብለው የሚጠሩት እነዚህ ካሜሮናዊያን ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ቆይታቸው ማርክ እና ሳምሶን በሚሉ ሃሰተኛ ስሞች እንደሚጠቀሙ የጠቀሰው ኮሚሽኑ የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ጭምር እንዳላቸው ተገልጿል።

ሃሰተኛ ገንዘብ ለማተም የሚጠቀሙባቸውን የተለያዩ መሣሪያዎች፣ የአሜሪካን ዶላር፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ገንዘብ፣ ድርሃምና የኬንያ ሽልንግ ትክክለኛ ገንዘቦችን ጨምሮ ሰነዶችና ፓስፖርቶች ተይዘዋል ።

በተያያዘም ሀሰተኛ የኢትዮጵያን የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ ከነበሩ ሶስት ኢትዮጵያዊያን ተጠርጣሪዎች መካከል ዮሴፍ ተከስተብርሃን እና ተክለብርሃን ገ/መስቀል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

በተደረገባቸው ጥብቅ ክትትልና ድንገተኛ ፍተሻ 40 ሺህ ሃሰተኛ ባለ አንድ መቶ ብር የገንዘብ ኖቶች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ሶስተኛው ተጠርጣሪ በፍለጋ ላይ ስለመሆኑም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.9K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-13 12:20:22 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው!

የካቲት 06/2013

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው፡፡

ከነዚህ መካካል

#ወለጋ

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 13፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሬት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

#ቀብሪ_ደሀር

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡

#አዲግራት

የአዲግራት ዩንቨርሲቲም ለስምንተኛ ጊዜ 2ሺህ 576 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ዩንቨርሲቲው በትይግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ስለደረሰበት ተማሪዎች ቀሪ ትምህርታቸውን በመቐለ ዩንቨርሲቲ እንዲያጠቅቁ ተደርጎ ዛሬ እየተመረቁ ነው፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ሁርካቶ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::

#መቀሌ

በሌላ በኩል በቅርቡ ተማሪዎችን አስመርቆ የነበረው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ቀሪ 608 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዙር እያስመረቀ ይገኛል::

#አርሲ

አርሲ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን የህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን እያስመረቀ ነው!

አርሲ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዙር በአራት የትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 23 የህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 22ቱ ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ፣ በቀዶ ጥገና፣ በውስጥ ደዌ፣ የህፃናት ህክምና እና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ ዘርፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል።

በምረቃ መርኃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

#ኮተቤ

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ ተከታታይ እንዲሁም በማታ የትምህርት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2ሺህ 39 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

በዛሬው እለት ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 2ሺህ 39ኙ ወንዶች ሲሆኑ 1ሺህ 29ኙ ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምሩቃኑ በሰለጠኑበት ዘርፍ ለሀገር የሚጠቅም ስራ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሀነ ጠና በበኩላቸው ተመራቂ ተማሪዎች የተመረቁት በቀለም ትምህርት በቻ ሳይሆን በአንድነትም በመሆኑ ህብረብሄራዊነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ብቁ ዜጋን በማምረት የእውቀት ፋና ወጊ የሆኑ መምህራንን በማፍራት አንጋፋ ስም ያለው ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ከ80 ሺ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተገልጿል።

#ጅማ

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው

የጅማ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርኃግብር ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 328 ተማሪዎች በቅድመ እና ድህረ ምረቃ እያስመረቀ ነው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 2ሺህ 707 ወንድ እንዲሁም 1ሺህ 621 ሴት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

1993 ዓ.ም ላይ የተመሰረተው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተደድር ሽመልስ አብዲሳ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊን ጨምሮ በርካታ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡

#via ENA/WALITA/EBC/FBC

#Purpose ETHIO MEREJA NEWS

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.6K viewsedited  09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 22:10:09
የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
14.0K views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 21:15:16
የመተከል ዞን 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ጉዳይ ፦

በመተከል ዞን 8 ትምህርት ቤት ከፀጥታ ጋር በተያያዘ አሁን ድረስ ምዝገባ አልተጠናቀም።

ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ተመዝግበው ፈተናውን እንዲወስዱ ለማድረግ የፀጥታውን ሁኔታም የማረጋገጥ ስራ ከክልሉ ጋር አብሮ እየሰራ እንደሚገኝ በትላንት መገለጫው አሳውቋል።

ነገር ግን በአካባቢው ችግሮቹ ካልተፈቱና የፀጥታ ችግር ካለ በመተከል ዞን 8 የፈተና ጣቢያዎች ያሉትን ተማሪዎች ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ / ሌላ ከተሞች አጓጉዞ የማስፈተን እቅድም እንዳለ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር በአካባቢው ያሉት ችግሮች በሚቀጥለው 1 ወይም 2 ሳምንት ተፈተው ተማሪዎች ባሉበት ሁኔታ/ቦታ ሆነው ይፈተናሉ የሚል እምነት እንዳለው አሳውቋል።

በአካባቢው የከፋ ሁኔታ ከተፈጠረ ግን በትራንፖርት ወደ አሶሳ ከተማ / አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተጓጉዘው እንዲፈተኑ ይደረጋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.1K viewsedited  18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 20:45:24
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በርካታ ሴቶች የመደፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ!

«በክልሉ በሴአግኝንተ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መፈጸሙን በስፍራው ካለው ግብረኃይላችን መረጃ አግኝንተናል» ሲሉ የሴቶች ሚንስትሯ ፊልሰን አብዱላሂ ትናንት ሐሙስ ምሽት በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

የፌዴራሉ መንግስት « ህግ የማስከበር ዘመቻ» ባለው እና ሕወኃት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በሴቶች ላይ በተከታታይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሲደርስባቸው እንደነበር የአይን ምስክሮች ፣ የህክምና ባለሞያዎች እና የረዲኤት ሰራተኞች ሲያስታውቁ ቆይተዋል።

በመንግስት በኩል ለደረሰው ጥቃት እውቅና ሲሰጥ የሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ የመጀመርያው ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን እንዳስታወቀው በትግራይ 108 የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ በክልሉ መዲና የመቀሌ ከተማ በሁለት ወር ውስጥ የተፈጸመ እንደነበር ገልጿል።

ከፊሎቹ ተጠቂዎች ጥቃቱን ያደሩሳበቸው የፌዴራል መንግስቱ ወታደሮች እና አጋሮቻቸው እንደሆኑ ቢገልጹም የጥቃት አድራሾችን ብዛት ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አለመቻሉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንደሚለው የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሪፖርት ያልተደረገባቸው አካባቢዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል አመልክቷል።መንግስት ጾታዊ ጥቃትን እንደማይታገስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.2K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 19:33:07
በምዕራብ ጉጂ ዞን ዱግዳ ዳዋ ወረዳ ኦነግ ሸኔ መሬት ቆፍሮ የደበቀው ከ452 ሺህ ብር በላይ ተገኘ!

ቡድኑ በዱግዳ ዳዋ ወረዳ ወልጌዪ ቀበሌ መሬት በመቆፈር 452 ሺህ 800 ብር በላይ ቀብሮ መደበቁን የዞኑ ፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ገልጿል፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ደስታ ኢታና እንደገለፁት ገንዘቡ በህብረተሰቡ ጥቆማ እና በፀጥታ አካላት ክትትል ከተደበቀበት ስፍራ ወጥቷል፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ምክትል ዳይሬክተር እና የሰላም ማስከበር የስራ ሂደት ባለቤት ኮማንደር ፍቅሬ ዴክሲሳ የአካባቢው ህብረተሰብ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንዳለ ገልፀዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.6K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 18:22:12
ንግድ ባንክ የወለድ ምጣኔ ጭማሪ አደረገ!

ንግድ ባንክ በየአመቱ በአማካኝ የማስመዘግበው የእድገት መጠን እየቀነሰ በመምጣቱ በአንዳንድ አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጌያለሁ ሲል በዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ አቤ ሳኖ በኩል አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ለቤቶች ልማት 9.5 በመቶ የነበረዉ የወለድ መጠን ወደ 10.5 በመቶ፣ የማዳበሪያ 9.25 በመቶ የነበረዉ የወለድ መጠን ወደ 10 በመቶ፣ የኮርፖሬት ቦንድ ብድር 9 በመቶ የነበረዉ የወለድ መጠን ወደ 10 በመቶ፣ የዉጭ ምንዛሬ በአንድ ፔሬድ ማለትም በ90 ቀናት 5.5 በመቶ የነበረዉ ወደ 9.5 በመቶ ከፍ ማድረጉን ባንኩ ተናግሯል።

በሌላ በኩል ለኤሌክትሪክ ኃይል፣ ለመድሀኒት አቅርቦት፣ ለስኳር፣ ለማዳበሪያ እንዲሁም ለዘይት የሚያስፈልጉ የውጭ ምንዛሬዎች ላይ ያለው የወለድ መጠን ወደ 4.5 በመቶ ዝቅ ማድረጉን ባንኩ ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.3K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 17:25:31
ዐቃቤ ሕግ በሙለር ሪል ስቴት ባለቤት ላይ የሙስና ክስ መሰረተ

ከዚህ ቀደም ለኦነግ ሸኔና ሕ.ወ.ሓ.ት የጥፋት ቡድኖች የፋይናንስ ምንጭ ሆነዋል በሚል ክስ የቀረበባቸው የሙለር ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋኪሮስ አሁን ደግሞ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ተጨማሪ ክስ ቀርቦባቸዋል።

አቶ ሙሉጌታ የቀረበባቸው የሙስና ክስ በቦሌ ክፍለከተማ ያለአግባብ 50 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት በመውሰድ እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደግሞ 11 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ወረዋል በሚል ነው። (አዲስ ዘይቤ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.8K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-12 16:43:10
“ለምርጫ የማስመዘግበው ዕጩ የለኝም” የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)

ለቀጣዩ አገራዊ ምርጫ በዕጩነት ላቀርባቸው የነበሩት ተወዳዳሪዎች በሙሉ በእስር ላይ ይገኛሉ ያለው ፓርቲው የገጠመው ውስጣዊ መፈረካከስ በብልጽግና ፓርቲ ጣልቃ ገብነት የተፈጸመ ነው የሚል ዕምነት እንዳለው የፖርቲው ቃል አቀባይ አቶ በቴ ኡርጌሳ ነግረውኛል ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች የሚገኘው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሜቲ ፅህፈት ቤት በፖሊስ መጠበቅ ከጀመረ ስድስት ወራት አልፎታል ያሉት አቶ በቴ ብልፅግና የራሱን ከፍተኛ አባላት ከማዕከላዊ አባልነት ሲያግድ ማንም በጸጋ ነው የተቀበለው እኛ በፖርቲያችን ውስጥ ያንን ውሳኔ ስንሰጥ ግን ማንም ሊያከብርልን አልቻለም ሲሉ አማረዋል።

የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ ከሰኞ የካቲት 8 እስከ 21 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.5K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ