Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን እንዲመስል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው! ጄኔራል ብ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን እንዲመስል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው!

ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ፣ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን እንዲመስልና በቴክኖሎጂ የዳበረ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናገሩ።

ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአባሉ እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችን እንዲመስል እና ከወቅቱ ጋር እንዲዘምን ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከለውጡ በኋላ ወደ ሠራዊቱ የሚቀላቀሉ ወጣቶች ፍላጎት መጨመሩን የገለፁት ጄኔራል ብርሀኑ፣ ከመላ ሀገሪቱ በተመለመሉ ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱ እና ለሙያው ፍቅርና ክብር ያላቸው ተተኪ ወታደሮችን ለማፍራት ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፤ በዚህም አበረታች ለውጦች እየተገኙ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

በተለይም ከዚህ በፊት፣ በውሳኔ ሰጪ ቦታዎችና የተመረጡ ሙያዎች፣ በከፍተኛ ወታደራዊ አመራሩ በአንድ ብሔር ተወላጆች ብቻ ተይዞ መቆየቱን አውስተው ከለውጡ በኋላ የማመጣጠን ስራዎች በመሰራታቸው ትልቅ ውጤት ተገኝቶበታል፤ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሠራዊቱ ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እንዲዘምን ሁለንተናዊ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news