Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል በሰሜን እዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ተያይዞ 349 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በትግራይ ክልል በሰሜን እዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ተያይዞ 349 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ ሲወጣ 124ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ!

በትግራይ ክልል በሰሜን እዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር ተያይዞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግና የፌደራል ፖሊስ የደረሱበትን የምርመራ ውጤት ይፋ አደረጉ።

መግለጫውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሙስናና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ በጋራ ሰጥተዋል።

በዚህም በሀገር ክህደት ወንጀል፣ በሀገር ሉዋላዊነት ላይ በተቃጣ ጥቃት እና በሽብር ወንጀሎች የተጠረጠሩ 349 ሰዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸው ሲሆን 124ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ 680 የሰው እና የሰነድ ምስክርነት ቀርቦባቸዋል።

ከማይካድራ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘም 279 ሰዎች በወንጀሉ መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 36ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news