Get Mystery Box with random crypto!

በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ 21 ሺህ 695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደሉ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ 21 ሺህ 695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደሉ ካቢኔው ወሰነ!

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፤ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኘው ግኝትቶች ላይ ነው የውሳኔ ሃሳብ ያሳለፈው፡፡

በመሆኑም በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆኑ፤ በጥናቱ የተገኘው ህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ 21 ሺህ 695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል ነው ውሳኔ የተላለፈው፡፡

በዚህም በዋናነት በ1997 ዓ.ም ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በዕጣ እንዲተላለፍ፤የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወጥቶላቸው ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንዲሰጥ ሲሉ ወስነዋል፡፡

ካቢኔው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን ይህ ችግርና ስርዓት አልበኝነት 1997 ጀምሮ እየተንከባለለ የመጣ መሆኑን እና ወደፊት እንዳይደገም በፅናት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news