Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.43K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-05-11 11:26:50 በትግራይ ክልል 5 መቶ 52 ት/ት ቤቶች ዳግም ወደ መማር ማስተመር ተግባር አልተመለሱም

በትግራይ ክልል ከሚያዚያ 24 ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ስራ መጀመራቸዉን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር የትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ ተናግረዋል።በመቀሌ ከተማ ነዋሪ ከሆኑ ግለሰቦች ብስራት ራዲዮ በሰማዉ መሰረት ፤ በክልሉ ርዕሰ መዲና ጨምሮ በመላዉ ትግራይ ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባሉ ትምህርት ቤቶች ስራ አለመጀመራቸዉን ፤ ተማሪዎችም ወደ ትምህር አለመለሳቸዉን  ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የት/ት ቢሮ እንዳስታወቀዉ ፤ 1 ሺህ 9 መቶ 40 ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቢጀምሩም በአሁኑ ወቅት 5 መቶ 52 ት/ት ቤቶች ስራ እንዳልጀመሩ ገልጿል። የቢሮዉ ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ለዚህ ምክኒያቱ በትምህርት ቤቶቹ የተፈናቃዮች መጠለያ መሆናቸዉ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከ 1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደርጓል። በዚህም ለአንድ ተማሪ በነፍስ ወከፍ 4 ደብተርና 1 እርሳስ በአጠቃላይ ፤ ለ 3 ሺህ 2 መቶ 62 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ብስራት ራዲዮው ሰምቷል።በተለይም በመቀሌ ከተማ ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸዉን ያነሱት ነዋሪዎች ፤ አሁንም ግን የተዘጉ የመንግስት ትምህርት ተቋማት በከተማዋ እንዳሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ከ ሶስት አመታት በላይ ከትምህርት የራቁ እና በጦርነት የተፈተኑ እንደመሆናቸዉ ተማሪዎቹ ትምህርት ከመጀመራቸው አስቀድሞ የስነልቦና ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ነዋሪዎቹ አንስተዋል። በክልሉ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች አሁንም የታጣቂዎች ካምፕ መሆናቸዉን ነዋሪዎቹ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.2K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 20:48:41 የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከጅቡቲ ተያዘ የተባለውን የበይነ መረብ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ በስድስት የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች ላይ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት መፍቀዱን "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል።

ችሎቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው፣ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ባስተባበሩት "የሽብር ድርጊት በርካታ ንጹሃን ዜጎች እንዲሞቱና ንብረት እንዲወድም ኾኗል" በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል።

@sheger_press
@sheger_press
12.4K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 13:25:52
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ምልአተ ጉባኤው መጀመሩን ገልጸዋል ።

ጉባኤው የቤተክርስቲያኗን አብይ ተልዕኮ ለመፈፀም እንደመሳሪያ ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሎ ታምኖባቸው የተጀመሩ ወሳኝ ስራዎች በዝርዝር በማየት ውሳኔ የሚተላለፍበት ጉባኤ እንደሚሆን ተናግረዋል። ቤተክርስቲያን እና ምዕመናን እንደ ሀገር ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች እየገጠማቸው ነው የተባለ ሲሆን የቤተክርስቲያን ቀኖና ቅድምያ ከሚሰጣቸው ነገር አንዱ ሰላም ነውና ሰላምን ለመጠበቅና ለማስረጽ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል። “በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖችንና የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናት መኖራቸውን ያነሱት ብጹእነታቸው በፍጥነት ተጎጂዎችን የምናፅናናበትና የምንደግፍበትን ሁኔታ በጉባኤው እናያለን” ብለዋል።

አያይዘውም አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ጠንክሮ የማስተማር የመምከርና የማስታረቅ ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በግጭት እየተሳተፋ ያሉ ወገኖች ግጭቱን አቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
14.1K viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 20:32:51
2 ህፃናቶችን ገድላ ተሰውራለች ተብላ የተጠረጠረችው ነጋሴ ከበደ ጫካ ውስጥ ተይዛለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.9K viewsedited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 19:16:37
በሽብር ወንጀል የተጠረጠረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ

ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለበት ጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት መግባቱ የተነገረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 1፤ 2015 ፍርድ ቤት ቀረበ። ጎበዜ ከሌሎች አምስት ግለሰቦች ጋር ፍርድ ቤት የቀረበው፤ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ይህን የገለጸው የእነ ጎበዜን ጉዳይ ለመመልከት ዛሬ ተሰይሞ ለነበረው፤ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ጋዜጠኛ ጎበዜን ጨምሮ ስድስት ተጠርጣሪዎች የቀረቡበት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የተከፈተው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት በአቶ ሲሳይ አውግቸው ስም ነው።

ስድስቱን ተጠርጣሪዎች ችሎት ፊት ያቀረባቸው የፌደራል ፖሊስ፤ ግለሰቦቹ “የሽብር ድርጊት ተግባር በመፈጸም በንጹሃን ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሳቸው በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው” በእስር ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ፖሊስ ስድስቱን ተጠርጣሪዎች “ህገ መንግስቱን እና ህግ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመቀየር በመንቀሳቀስም” ወንጅሏቸዋል።

ጋዜጠኛ ጎበዜን ወክለው ችሎት ፊት የቀረቡት ጠበቃ አዲሱ አልጋው፤ ፖሊስ “ማን በየትኛው የወንጀል ድርጊት የተሳተፈ እንደሆነ የገለጸው ነገር የለም” ሲሉ የተጠርጣሪዎች የወንጀል ተሳትፎ ፖሊስ በጽሁፍ ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ላይ አለመገለጹን ተናግረዋል። አቶ አዲሱ አክለውም ደንበኛቸው “ጥፋት ፈጽመዋል ከተባለ እንኳን በሚዲያ ስራቸው አማካኝነት ነው። ስለሆነም የምርመራ ሂደቱ መመራት ያለበት በመገናኛ ብዙሃን አዋጁ ነው” የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13.9K viewsedited  16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 09:19:19
አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ እጃቸውን እንደሚሰጡ አስታወቁ !!

መንግስት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማናጋት ሙከራ አድርገዋል በሚል በሽብርተኛነት ከወነጀላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ የተከሰሱበትን ክስ በአደባባይ ለመሞገት መወሰናቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

በፅሁፋቸውም ‹‹ከአገዛዙ አፈና ፣ እስርና ግድያ ሸሽቶ በማምለጥ የሚመጣ መፍትሄ የለም። ትግላችን ሰላማዊና ህጋዊ እስከሆነ ድረስ በገፍ እየታሰርንና እየሞትን አገዛዙ በሀይልና በአፈና ሊያሸንፈን እንደማይችል ተስፋ ልናስቆርጠው ይገባል። በዚህ መጠን ዋጋ ለመክፈል ካልቆረጥን በስተቀር የአገርና የህዝብ ህልውና ከጥፋት ሊድን አይችልምና። ›› ያሉ ሲሆን ‹‹ይህንን በለጋ የልጅነት ዘመኔ ለራሴ የገባሁትን የትግል ቃል-ኪዳንና የምታመንለትን የሰላማዊነትና ህጋዊነት መርህ መሰረት በማድረግ ወደ አገሬ ለመመለስና የዶ/ር ዐቢይን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። ›› ማለታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡

‹‹ስለሆነም በታሰርኩ ቁጥር ከእኔ በላይ ስቃዬን የምትሰቃዩ ቤተ-ዘመዶቸ፣ ጓደኞቸ፣ የሃሳብ ደጋፊዎቸና የትግል አጋሮቸ ይህንን ውሳኔዬን የሞኝነት፣ የአጉል ጀብደኝነት ወይም የመንግስትን የጭካኔ ደረጃ በአግባቡ ያለመረዳት ድክመት አድርጋችሁ እንዳታዩብኝና ያልተገባ ጫና እንዳትፈጥሩብኝ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እማፀናለሁ። ይህንን ውሳኔ በሚገባ አስቤበትና ከልቤ አምኘበት የወሰንኩት ስለሆነ በሞራል ልታግዙኝ ይገባል እንጂ ልታዝኑልኝም ሆነ ልታዝኑብኝ አይገባም እላለሁ። " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
14.0K viewsedited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 09:45:13
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me
0909255008
0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ ቤተሰብ ይውኑ
https://t.me/used_phone_ethiopian
1.4K views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 20:54:42
መረጃ

ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጨምሮ የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ያላቸዉን ሰዎች ዝርዝር ይፋ አደረገ!

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአማራ ክልል እየወሰደ ባለው እርምጃ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።ግብረኃይሉ ፤ የሚዲያና ፕሮፓጋንዳ ክንፍ በመሆን ከሀገር ውስጥ እና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት በወንጀል የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሰረትም በሀገር ዉስጥና በዉጭ የሚኖሩ ሰዎችን ስም ዝርዝር ያወጣ ሲሆን እነርሱም:

1.  ሀብታሙ አያሌው
2.  ምንአላቸው ስማቸው
3.  ብሩክ ይባስ
4.  እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ
5.  ዘመድኩን በቀለ
6.  ልደቱ አያሌው
7.  መሳይ መኮንን
8.  ጎበዜ ሲሳይ
9.  ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
10.  በለጠ ጋሻው እና
11.  ሙሉጌታ አንበርብር ናቸው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.2K viewsedited  17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 17:23:14
ከቀናት በፊት በተፈፀመባቸው ጥቃት የተገደሉት የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ እሁድ ተፈፅሟል።

የአቶ ግርማ የሽጥላ ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመው በትውልድ ስፍራቸው መሃል ሜዳ ነው።

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ የሽኝት ስነስርዓት ተከናውኖ ነበር።

አቶ ግርማ ባለትዳርና የ3 ሴትና የ4 ወንድ ልጆች አባት ነበሩ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.7K viewsedited  14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 14:12:44
ከአላማጣ በተነሱ መንገደኞች ላይ በመተሀራ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

ከሰሜን ኢትዮጵያ አላማጣ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ነበረ የተባለ፣ የኛ ባስ በተሰኘው የህዝብ ማመላለሻ ላይ ባለፈው ሐሙስ ሚያዚያ 19/2015 ምሽት 12፡30 አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ሹፌሩ እና ረዳቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን በቦታው የነበሩ ተሳፋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከአምስት ያላነሱ ተጓዦች ቁስለኛ ሆነው አዳማ ከተማ ለሕክምና መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከተሳፋሪዎች ጋር አብረው ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነዋሪዎች አክለዋል።

ጥቃቱ አድራሾቹ የተኩስ እሩምታ ከፍተው ጉዳት ያደረሱትም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በመተሀራ እና በወለንጭቲ ከተማ መሀል ላይ ነው ተብሏል።

ጥቃቱ ከተፈጸመ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ቁጥራቸው ከአምስት የማይበልጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ቦታው መድረሳቸውን የገለጹት የዓይን እማኞች፤ በየኛ ባስ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ በሚኒ ባስ ይጓዙ የነበሩ ሰዎችን አግተው ሲወስዱ ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ጥቃት አድራሾች የተወሰኑት መደበኛ ሌሎች ደግሞ ወታደራዊ ልብስ የለበሱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ መንገደኞች እነዚህ ኃይሎች የሸኔ ታጣቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምተዋል። ተሳፋሪዎች ከአላማጣ በቆቦ መገንጠያ አድርገው በአፋር በርሃ በኩል ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ እንደነበር ጠቅሰው፤ "የሰው ህይወት እንዲህ ተራ ሲሆን እና በሚዲያዎችም ሆነ በመንግስት ምንም ሳይባል መቅረቱ ያሳዝናል።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.5K viewsedited  11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ