Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል 5 መቶ 52 ት/ት ቤቶች ዳግም ወደ መማር ማስተመር ተግባር አልተመለሱም በትግራ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በትግራይ ክልል 5 መቶ 52 ት/ት ቤቶች ዳግም ወደ መማር ማስተመር ተግባር አልተመለሱም

በትግራይ ክልል ከሚያዚያ 24 ጀምሮ በክልሉ የሚገኙ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ስራ መጀመራቸዉን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር የትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ ተናግረዋል።በመቀሌ ከተማ ነዋሪ ከሆኑ ግለሰቦች ብስራት ራዲዮ በሰማዉ መሰረት ፤ በክልሉ ርዕሰ መዲና ጨምሮ በመላዉ ትግራይ ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባሉ ትምህርት ቤቶች ስራ አለመጀመራቸዉን ፤ ተማሪዎችም ወደ ትምህር አለመለሳቸዉን  ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የት/ት ቢሮ እንዳስታወቀዉ ፤ 1 ሺህ 9 መቶ 40 ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቢጀምሩም በአሁኑ ወቅት 5 መቶ 52 ት/ት ቤቶች ስራ እንዳልጀመሩ ገልጿል። የቢሮዉ ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ለዚህ ምክኒያቱ በትምህርት ቤቶቹ የተፈናቃዮች መጠለያ መሆናቸዉ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ከ 1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደርጓል። በዚህም ለአንድ ተማሪ በነፍስ ወከፍ 4 ደብተርና 1 እርሳስ በአጠቃላይ ፤ ለ 3 ሺህ 2 መቶ 62 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ብስራት ራዲዮው ሰምቷል።በተለይም በመቀሌ ከተማ ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸዉን ያነሱት ነዋሪዎች ፤ አሁንም ግን የተዘጉ የመንግስት ትምህርት ተቋማት በከተማዋ እንዳሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ከ ሶስት አመታት በላይ ከትምህርት የራቁ እና በጦርነት የተፈተኑ እንደመሆናቸዉ ተማሪዎቹ ትምህርት ከመጀመራቸው አስቀድሞ የስነልቦና ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ነዋሪዎቹ አንስተዋል። በክልሉ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች አሁንም የታጣቂዎች ካምፕ መሆናቸዉን ነዋሪዎቹ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news