Get Mystery Box with random crypto!

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ምልአተ ጉባኤው መጀመሩን ገልጸዋል ።

ጉባኤው የቤተክርስቲያኗን አብይ ተልዕኮ ለመፈፀም እንደመሳሪያ ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሎ ታምኖባቸው የተጀመሩ ወሳኝ ስራዎች በዝርዝር በማየት ውሳኔ የሚተላለፍበት ጉባኤ እንደሚሆን ተናግረዋል። ቤተክርስቲያን እና ምዕመናን እንደ ሀገር ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች እየገጠማቸው ነው የተባለ ሲሆን የቤተክርስቲያን ቀኖና ቅድምያ ከሚሰጣቸው ነገር አንዱ ሰላም ነውና ሰላምን ለመጠበቅና ለማስረጽ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል። “በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖችንና የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናት መኖራቸውን ያነሱት ብጹእነታቸው በፍጥነት ተጎጂዎችን የምናፅናናበትና የምንደግፍበትን ሁኔታ በጉባኤው እናያለን” ብለዋል።

አያይዘውም አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ጠንክሮ የማስተማር የመምከርና የማስታረቅ ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በግጭት እየተሳተፋ ያሉ ወገኖች ግጭቱን አቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ አባታዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news