Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ እጃቸውን እንደሚሰጡ አስታወቁ !! መንግስት ህገ መንግ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ እጃቸውን እንደሚሰጡ አስታወቁ !!

መንግስት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማናጋት ሙከራ አድርገዋል በሚል በሽብርተኛነት ከወነጀላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ የተከሰሱበትን ክስ በአደባባይ ለመሞገት መወሰናቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

በፅሁፋቸውም ‹‹ከአገዛዙ አፈና ፣ እስርና ግድያ ሸሽቶ በማምለጥ የሚመጣ መፍትሄ የለም። ትግላችን ሰላማዊና ህጋዊ እስከሆነ ድረስ በገፍ እየታሰርንና እየሞትን አገዛዙ በሀይልና በአፈና ሊያሸንፈን እንደማይችል ተስፋ ልናስቆርጠው ይገባል። በዚህ መጠን ዋጋ ለመክፈል ካልቆረጥን በስተቀር የአገርና የህዝብ ህልውና ከጥፋት ሊድን አይችልምና። ›› ያሉ ሲሆን ‹‹ይህንን በለጋ የልጅነት ዘመኔ ለራሴ የገባሁትን የትግል ቃል-ኪዳንና የምታመንለትን የሰላማዊነትና ህጋዊነት መርህ መሰረት በማድረግ ወደ አገሬ ለመመለስና የዶ/ር ዐቢይን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። ›› ማለታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡

‹‹ስለሆነም በታሰርኩ ቁጥር ከእኔ በላይ ስቃዬን የምትሰቃዩ ቤተ-ዘመዶቸ፣ ጓደኞቸ፣ የሃሳብ ደጋፊዎቸና የትግል አጋሮቸ ይህንን ውሳኔዬን የሞኝነት፣ የአጉል ጀብደኝነት ወይም የመንግስትን የጭካኔ ደረጃ በአግባቡ ያለመረዳት ድክመት አድርጋችሁ እንዳታዩብኝና ያልተገባ ጫና እንዳትፈጥሩብኝ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እማፀናለሁ። ይህንን ውሳኔ በሚገባ አስቤበትና ከልቤ አምኘበት የወሰንኩት ስለሆነ በሞራል ልታግዙኝ ይገባል እንጂ ልታዝኑልኝም ሆነ ልታዝኑብኝ አይገባም እላለሁ። " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news