Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.43K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-18 08:24:57
የአገር አቀፍ የትምህርት ፈተና ቀናት

① በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፈተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ።

② በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 13 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ።

③ የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ።

በመጨረሻም ከ2016 ጀምሮ የትምህርት ካላንደሩን ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚህ ማዕቀፍ ያስተካክሉ በማለት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ ይገልፃል።።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.4K viewsedited  05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 15:31:18
ምርጫ ቦርድ የህወሓትን የስረዛ ውሳኔ እንዲነሳ የቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው ይነሣልኝ ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ውድቅ አደረገ።

ቦርዱን በውሳኔው የህወሓትን ስረዛ ለማንሳት የሚያስችል የሕግ ድጋፍ አለመኖሩን በመጥቀስ በሕጉ መሠረት እንደአዲስ አመልክቶ በሕግ አግባብ መስተናገድ እንደሚችል ገልጷል። የቦርዱ ደብዳቤ ከታች ተያይዟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
3.4K viewsedited  12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 14:15:17
ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በአፋጣኝ እንዲፈታ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ሲፒጄ (CPJ) ጥሪ አቀረበ። መቀመጫውን በአሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ትላንት አርብ ባወጣው መግለጫ “በአገር ውስጥና በውጪ ያሉ የፕሬስ አባላትን ማዋከብ እንዲያቆሙ” ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጥሪ አስተላልፏል።

“የአማራ ድምጽ” የተባለው በዩቲዩብ የሚተላለፍ የግል መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አርታኢ የሆነው ጎበዜ፤ ሚያዝያ 28፤ 2015 በጅቡቲ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ይፋ እንዳደረጉ ሲፒጄ በመግለጫው ጠቅሷል። የጋዜጠኛው ጠበቃ አዲሱ አልማው፤ ጎበዜ ከጅቡቲ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ለሲፒጄ ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ዝም ለማሰኘት እና ለመበቀል በድፍረት ድንበር ተሻግረዋል” ያሉት ከሰሃራ በረሃ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት የሲፒጄ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ፤ እስሩ “በስደት ደህንነት ፈልገው ከሀገራቸው በሄዱ ጋዜጠኞች ላይ ስጋት ይፈጥራል” ብለዋል። “ጎበዜ ያለመዘግየት ሊፈታ ይገባል” ያሉት የሲፒጄ ተወካይ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ስለዋለበት እና ተላልፎ ስለተሰጠበት ሁኔታ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
4.2K viewsedited  11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 14:14:53 መርጌታ ዮሐንስ ባሕላዊ መድሀኒት ቀማሚ ባሉበትሆነዉመጠቀይችላሉ ቦታዉ እሩቅነዉ ካገርዉጭነኝብለዉእዳይጨነቁ  ያስታዉሱ
በ0921807274ደዉለዉመጠየቅይችላሉከምንሰጣቸዉአገልግሎቶች በጥቂቱ
1, #መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
2, ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
3,  ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
4,ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
5, ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
6, መስተፋቅር
7 ;ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
8,ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
9, ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
10, የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
11,ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
12; መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
13, መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
14, ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
15, ለበረከት
16,ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
17,ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
18,ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
19,ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
20, ለሙግት
21,ለሰላቢ
22,ለስንፈት ወሲብ
23,ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
24, ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
25,ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
26, ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)
27,መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)
28,ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)
29, ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)
30;ለአዙሪት
31; ለአስቸጋሪና ተመላላሽ ሲህር
32;ለሪህ በሽታ
33;ለጉልበት ድርቀት
34;የወገብ ህመም
35;የከረመ ደረቅ ሳል
36;ለደም ግፊት
37;የከፋ የሆድ ድርቀት
38;በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው
39;የአእምሮ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ከሰው  መገለል፣እንቅልፍ ማጣት
40;ክብደት ለመቀነስ
41;የእንቅርት በሽታ
42; የሳይነስ ህመም
43;የሆድ ድርቀትና የሆድ ህመም
44;የወር አበባ ችግር ካለ
45;ውጥረትና የአእምሮ ጭንቀት
46;ለከፍተኛ ራስ ምታት
47;ማስታወስ፣ንቃት፣ተነሳሽነት ለሌላቸው
48;ለድምፅ መታፈን
49;ከአጫሽነት ለመላቀቅ
50;ራስን ስቶ በስቃይ ለሚኖር
0921807274 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም አካውንታችን  Https://, @yohans63
3.9K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 06:59:25 የማለዳ ዐበይት ዜናዎች

1፤ የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች ያቋረጡት የምግብ ዕርዳታ እንዲቀጥል ጥሪ ማድረጉን ቪኦኤ ዘግቧል። በክልሉ የምግብ ዕርዳታ ሥርጭቱ ባለፈው ወር ከተቋረጠ ወዲህ፣ ወደ ክልሉ እየገቡ ያሉት መጠነኛ የሕጻናት አልሚ ምግቦችና የግብርና ግብዓቶች ብቻ መኾናቸውን ኮሚሽኑ መግለጡን ዘገባው ጠቅሷል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከሽሬ ከተማ የዕርዳታ መጋዘኔ ከፍተኛ መጠን ያለው የዕርዳታ እህል ተዘርፏል በማለት፣ የዕርዳታ ሥርጭት ማቋረጡ ይታወሳል። የአሜሪካው ዓለማቀፍ የልማትና ዕርዳታ ድርጅትም በተመሳሳይ ምክንያት የዕርዳታ ሥርጭት ለጊዜው አቋርጫለኹ ብሏል።

2፤ ዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት የጅቡቲ መንግሥት በሕገወጥ መንገድ ገብታችኋል ብሎ ያስወጣቸው 6 ሺህ  ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች አፋር ክልል ደዋሌ መግባታቸውን አስታውቋል። ድርጅቱ፣ በምሥራቃዊው መስመር ማለትም በፑንትላንድ፣ ሱማሌላንድና ጅቡቲ በኩል ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት ለሚሰደዱ 1 ሚሊዮን ያህል ፍልሰተኞች የ58 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከለጋሾች ጠይቋል። በምሥራቁ መስመር ባሕር አቋርጠው የሚጓዙት ፍልሰተኞች አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን መኾናቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ ለጋሾች ይህንኑ መስመር ዘንግተውታል በማለት ወቅሷል። ድርጅቱ የገንዘብ ድጋፉን የጠየቀው፣ በስደት ወቅት እንግልት ለሚገጥማቸው ፍልሰተኞችና ለተመላሾች የተለያዩ ድጋፎችን ለመስጠት ነው።

3፤ ኢትዮጵያ፣ ሱማሊያና ኬንያ በጋራ ድንበር ጸጥታ ዙሪያ ለመተባበር የሚያስችላቸውን የጋራ ፕሮጀክት መርቀዋል። ከብሪታኒያ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው የጋራ ፕሮጀክቱ መሠረቱ የተጣለው፣ በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ማንዴራ አውራጃ እንደኾነ የኬንያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የፕሮጀክቱ ዓላማ፣ በአገራቱ የጋራ የድንበር አካባቢ ሰላም፣ ጸጥታ፣ ልማትና ድንበር-ዘለል ትብብሮችን ማረጋገጥ ነው። ሦስቱ አገራት የጋራ ፕሮጀክቱን የጀመሩት፣ በነውጠኛው አልሸባብ ላይ የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ ከተስማሙ ከጥቂት ስምንታት በኋላ ነው።

4፤ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኢትዮጵያው "ቦርከና" ጋዜጣ "በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት እየተፈጠረ ይኾን?" በማለት ያተመውን ሃተታ "በሐሰትና ግምታዊ ድምዳሜ የተሞላ" በማለት ተችቷል። ሚንስቴሩ በመግለጫው፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በቅርቡ ስለ ሱዳኑ ግጭት በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያን ጎሸም ያደረጉ አስመስሎ አቅርቧል በማለት ወቅሷል። ጋዜጣው "ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሥመራ መሄድ ፈልገው፣ የኤርትራ መንግሥት ሁለት ጊዜ ፍቃድ ነፍጓቸዋል" እንዲኹም "ኤርትራ ለአማራ ፋኖዎች ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠቷ የዐቢይ ካድሬዎች ኢሳያስን እየተቹ ነው" በማለት የጻፋቸው ነገሮች "ሐሰት" መኾናቸውንም ሚንስቴሩ ገልጧል። ሚንስቴሩ፣ ኤርትራ አዲስ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገች እንደኾነ ጋዜጣው ያሰራጨውን ወሬም "የተሳሳተ" በማለት አስተባብሏል።

5፤ ደቡብ ሱዳን የግብጹ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በሱዳን ግጭት ዙሪያ ለመምከር የመሪዎች ስብሰባ እንዲካሄድ ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሃሳብ ማቅረባቸውን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴሯ በኩል አረጋግጣለች። ፕሬዝዳንት ሲሲ ይህንኑ ሃሳብ ያቀረቡት፣ ውጭ ጉዳይ ሚንስትራቸውን ሳሜ ሽኩሪን ከአራት ቀናት በፊት ወደ ጁባ በላኩበት ወቅት እንደኾነ ሚንስቴሩ ገልጧል። ፕሬዝዳንት ኪር በበኩላቸው፣ የመሪዎች ጉባዔ ከተካሄደ የሁሉንም የሱዳን ጎረቤቶች መሪዎች ያካተተ ይሁን የሚል መልስ መስጠታቸውንና የፕሬዝዳንት ሲሲን ምላሽ እየተጠባበቁ መኾኑን ሚንስቴሩ ጨምሮ አመልክቷል።

Via ፦ [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
6.9K viewsedited  03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 20:40:34 የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በፕሬዝዳንት ዢ ፑንግ ግብዣ በመጭው ዕሁድ ቻይናን እንደሚጎበኙ የቻይናው ሲጂቲኤን ዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ፕሬዝዳንት ዢ ፒንግ፣ የኹለቱን አገራት ግንኙነት ወደ "ስትራተጂካዊ አጋርነት" ለማሳደግ ባለፈው የአውሮፓዊያን ዓመት ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ማስታወሳቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ቻይናባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የሾመቻቸው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑኳ ኤርትራን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.0K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 19:58:49
በአማራ ክልል በባህርዳር እና በሌሎችም ትልልቅ ከተሞች ታግዶ የነበረው የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል።

በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል እንደገና መደራጀት ጋር ተያይዞ በተከሰተው አለመግባባት በትልልቅ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደቆየ ሲገለጽ ነበር።

ካሳለፍነው ረቡዕ ግንቦት 2/2015 ምሽት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ መለቀቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከነዋሪዎቹ አረጋግጧል።የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩት ጎንደር፣ ባህርዳር እና ወልዲያ ከዕረቡ ምሽት ጀምሮ መስራት እንደጀመረ ታውቋል፡፡

የሞባይል ዳታ አገልግሎት በአማራ ክልል በጎንደር፣ በባህርዳር እና በወልዲያ ከተማ ከተዘጋ ከኹለት ሳምንታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የተዘጋበት ዋና ምክንያት በክልሉ ከሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይልና ከክልሉ ልዩ ኃይል ጋር በተገናኘ በተፈጠረው ውጥረት እንደነበር ተነግሯል፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.3K viewsedited  16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 16:59:16
#Update

" ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባቸው አሞኜ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ #በፖሊስ አባል መገደላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ።

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑን ፓሊስ ገልጿል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ፤ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም " ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ " በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ ገድሏቸዋል።

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.9K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 14:27:54
ሰበር ዜና

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ሀላፊ አቶ አለባቸው አምኜ በቢሯቸው ውስጥ በሽጉጥ ተመተው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል።
የቂርቆስ ክፈለ ከተማ ወረዳ ሰምንት ዋና ስራ አሰፈጻሚ በቢሯቸው ውስጥ በስራ እያሉ እንደተመቱ ነው የአዩዘሀበሻ ምንጮች የገለፁት።

ዋና ስራ አሰፈጻሚውን በመምታት የተጠረጠረው የአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ባልደረባ እንደሆነ የአዩዘሀበሻ የመረጃ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡

ተጠርጣሪው ሀላፊውን በሽጉጥ ከመታ በኋላ ከአንድ ግብረአበሩ ጋር እንደተያዙም አክለው ገልፀዋል።

የአቶ አለባቸው አሞኘ ህይወት የመትረፍ ዕድሉ አነስተኛ መሆኑን ጭምር ነው የተሰማው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.4K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 19:18:37 ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለሚያስገነቡት አዲስ ቤተመንግሥት ተጨማሪ ሦስት ተቋራጮች መቅጠራቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች።

የ"ጫካ" ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው 49 ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ሲገለጽ የቆየ ሲኾን፣ የምዕራባዊያን ዲፕሎማቲክ ምንጮች ግን ወጪው 850 ቢሊዮን ብር ሊደርስ እንደሚችል በመናገር ላይ ናቸው።

ፕሮጀክቱ በ503 ሔክታር ላይ የቅንጡ መኖሪያና መዝናኛ መንደሮችንና ሦስት ሰው ሠራሽ ሐይቆች ግንባታ ያካተተ ሲኾን፣ ግንባታው የሚካሄደው በየካ ክፍለ ከተማ የካ ተራራ ግርጌ ነው።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እስካኹን የ29 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ አካሂዷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.4K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ