Get Mystery Box with random crypto!

#Update ' ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ነው ' - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

#Update

" ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባቸው አሞኜ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ #በፖሊስ አባል መገደላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ።

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑን ፓሊስ ገልጿል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ፤ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም " ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ " በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ ገድሏቸዋል።

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news