Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል በባህርዳር እና በሌሎችም ትልልቅ ከተሞች ታግዶ የነበረው የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በአማራ ክልል በባህርዳር እና በሌሎችም ትልልቅ ከተሞች ታግዶ የነበረው የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል።

በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል እንደገና መደራጀት ጋር ተያይዞ በተከሰተው አለመግባባት በትልልቅ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደቆየ ሲገለጽ ነበር።

ካሳለፍነው ረቡዕ ግንቦት 2/2015 ምሽት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ መለቀቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከነዋሪዎቹ አረጋግጧል።የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩት ጎንደር፣ ባህርዳር እና ወልዲያ ከዕረቡ ምሽት ጀምሮ መስራት እንደጀመረ ታውቋል፡፡

የሞባይል ዳታ አገልግሎት በአማራ ክልል በጎንደር፣ በባህርዳር እና በወልዲያ ከተማ ከተዘጋ ከኹለት ሳምንታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ የተዘጋበት ዋና ምክንያት በክልሉ ከሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይልና ከክልሉ ልዩ ኃይል ጋር በተገናኘ በተፈጠረው ውጥረት እንደነበር ተነግሯል፡፡

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news