Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.46K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-03 20:24:23 ፖሊስ አዛዡ ተገደሉ

በአማራ ክልል፤ የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው “በግለሰብ በተፈጸመባቸው ጥቃት” ተገደሉ።

በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በተከፈተባቸው ተኩስ ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። ለወረዳዋ ፖሊስ አዛዦች ህልፈት ምክንያት የሆነውን ተኩስ ከፍቷል የተባለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ጥቃት የተፈጸመባቸው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 26፤ 2015 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ጋሻዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የፖሊስ አዛዦቹ ላይ ተኩስ የተከፈተባቸው፤ በዛሬው ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች እየተሰጠ ያለውን “የስምንተኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና እየተጓዙ በነበረበት ወቅት” መሆኑን የኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊው አስረድተዋል።

ሁለቱ የፖሊስ አዛዦች “ግልገሌ” የተባለች ቀበሌ ላይ ሲደርሱ “መንገድ ላይ ሲጠብቃቸው ነበር” በተባለ ግለሰብ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አቶ ጌታሁን ተናግረዋል።

በዚህ ጥቃት በጥይት የተመቱት የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ዘውዱ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ፤ ሹፌራቸው “እግሩ ላይ ተመትቶ” ጉዳት እንደደረሰበት ኃላፊው አክለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.5K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 19:52:38
በሀዋሳ ከተማ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትንና ውርጃን በሠላማዊ ሰልፍ አወገዙ ፡፡

ሠልፈኞቹ ድርጊቶቹን ያወገዙት በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወርና የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ነው። የተቃውሞ ሰልፉን ያስተባበሩት በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ 22 የቃለሕይወት አብያተ ክርስትያን ናቸው።

በሃዋሳ ዩኑቨርሲቲ የህግ መምህር እና ተመራማሪ አቶ ብርሃኑ ገኔቦ በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ የተመሳሳይ ጾታ ግኑኝነት ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚያስከትል ገልጸዋል።

Via DW
@sheger_press
@sheger_press
10.6K viewsedited  16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 08:05:49
የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ክልል ተቀያይረው ውይይት እያካሄዱ ነው

ከሰሞኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመከረው የገዥው ፓርቲ ብልጽግና ማዕከላዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ክልል ተቀያይረው ክልል አቀፍ የአመራር ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

ውይይቱን የሚመሩት የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ሲሆኑ፤ የክልል አመራሮች ውይይቱ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ያስቀመጠውን አቅጣጫ በየደረጃው ለሚገኙ የክልል አመራሮች ለማስረጽ ያለመ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ ሀዋሳ ተጉዘው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልልን የአመራሮች ወይይት እየመሩ ነው፡፡ በአንጻሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ወደ ባህር ዳር ተጉዘው የአማራ ክልል አመራሮችን ውይይት እየመሩ ነው፡፡

የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ኡመር የሲዳማ ክልል የአመራሮች ውይይትን እየመሩ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ውይይት ያልጀመሩ ክልሎች እንደሚጀመሩም ታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.5K viewsedited  05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 07:26:54 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምግብ እርዳታን ላልተፈለገ ዓላማ በማዋል ተሳትፏል መባሉን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አጣጥሏል።

በምግብ እርዳታ ዝርፊያና ለራስ ጥቅም በማዋል የተሳተፉ የሠራዊቱ ክፍሎች ወይም ተቋማት የሉም በማለት የገለጠው መግለጫው፣ ሠራዊቱ ከተረጅዎች እርዳታ ሊነጥቅ ይቅርና ለእርዳታ ፈላጊዎች እርዳታ ለመስጠት በቂ የሎጂስቲክስ አቅርቦት ያለው ተቋም ነው ብሏል። ሠራዊቱ፣ በድርጊቱ በግለሰብ ደረጃ ተሳትፈው የተገኙ አባላቱ ካሉ ግን ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ሠራዊቱ ይህንኑ መግለጫ ያወጣው፣ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት በውስጥ ምርመራው በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ወታደሮችንና የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመመገብ እንደዋለ ደርሶበታል የሚል ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.8K viewsedited  04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 18:32:37
ህወሓት ከምርጫ ቦርድ መሠረዙን ተከትሎ በዚህ ስያሜ ለሚመጣ ማንኛዉም የተደራጀ ፖለቲካ ድርጅት በምርጫ ቦርድ አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 69 መሠረት ስያሜዉን መዉሰድ ይችላል። ነገር ግን ምርጫ ቦርድ ለ አንድ ወር ባደረገው ስብሰባ እና ጥናት መሰረት ዉድቅ አድርጎታል።የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.0K viewsedited  15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 14:07:19 " የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ከዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና እና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር ሳይጋጭ እንደሚከናወን አሳውቋል።

በ208 የትምህርት ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ፣ ከመውጫና ከ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲከናወን የሚረዳ ዕቅድ ተዘጋጅቷል " ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት እንደሚሰጥ ዶ/ር ኤባ አስታውሰዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎቻቸውን የምረቃ መርሃግብር ከመውጫ ፈተና በኋላ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎቹ ምርጫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሲጠናቀቅ ማካሄድ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ኤባ ፤ በዘንድሮው ዓመት 180 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸው ለ208 የመመረቂያ ፕሮግራሞች የሚውሉ የፈተና ዓይነቶች መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።

" የመውጫ ፈተና የሥርዓተ ትምህርቱ አካል ሆኖ ይቀጥላል " ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈትነው 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች እንደሚያልፉ አስረድተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የሚሰጥ በመሆኑ የተማሪዎች ስም ዝርዝር ተልኮ ወደ ዳታ ማዕከል መግባቱን አመላክተዋል።

ለተማሪዎች ለፈተና የሚሆን ልዩ የመታወቂያ ቁጥር ይሰጣቸዋል ያሉት ዶክተር ኤባ፤ በተሰጣቸው ቁጥር መሠረት በኦንላይን መፈተን እንዲችሉ የሚረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በማዕከል ደረጃ የተዘጋጀውን የፈተና ሥርዓት ለመሞከር እንደ አገር ሞዴል ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቀው፤ በዚህም ጉድለቶች ካሉ ለማስተካከልና ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።

ለፈተናው መሳካት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደራጀ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ለመውጫ ፈተናው የሚውሉ ኮምፒዩተሮች፣ የኢንተርኔት አገልግሎትና ጄኔሬተሮች ዝግጅት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.8K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 13:11:58
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺ ሰራተኞችን ልቀጥር ነው ብዬ ማስታወቂያ አላወጣሁም አለ።

ይህን መረጃ ኢትዮ መረጃ NEWS መዘገቡ የሚታወስ ነው።

በቅድምያ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን።

እኛ 20 ሺህ ሰራተኞች ለመቅጠር በየትኛውም የማህበራዊ ትስስር ገፃችን ላይ ጥሪ አላቀረብንም ፤ መሰል ሀሰተኛ መረጃዎች የሚሰራጩት ሆን ተብሎ ተመሳስለው በተከፈቱ #ሀሰተኛ_ገፆች ነው " ሲል የሚመለከተው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ክፍል ገልጾልናል።

በመሆኑም " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 20 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ሊቀጥር ነው " በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.1K viewsedited  10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 09:54:03
በጎደሬ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አንድ የፖሊስ አዛዥ ተገደለ

ከደቡብ  ምዕራብ ክልል ሚዛን ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ በመጓዝ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት  ጥቃት የአንድ ፖሊስ አዛዥ ተገድሏል። በጥቃቱ አንድ የፖሊስ  አባል ላይ ጉዳት መድረሱን በጋምቤላ ክልል የጎደሬ ወረዳ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳኜ ወርቅነህ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በደቡብ ምዕራብ ክልል የኪ ወረዳ  ልዩ ስሙ ባያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  ነው። ጥቃቱ ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም  ከምሽቱ 1 ሰዓት 30 ደቂቃ አካባቢ ተፈፅሟል።

ይህ ግድያ የተፈጸመው የፖሊስ  አባላቱ ከደቡብ ምዕራብ ክልል ሚዛን ከተማ ስልጠናቸውን ጨርሰው ወደ ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ በመመለስ ላይ እያሉ ነው ብለዋል።ጥቃቱንም የጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ፈፅመውታል።

በጥቃቱ የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ አብዮት ሮኬት ህይወታቸው አልፏል። በሌላ አንድ የፖሊስ አባል ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በቴፒ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል ሲሉ አቶ ዳኜ ወርቅነህ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ድርጊቱን በፅኑ የሚያወግዝ መሆኑን እና አጥፊዎቹም ለህግ እንዲቀርቡ ከፍትህ አካላትና ከሚመለከታቸው ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
9.8K views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 19:44:37
"በሌላ አርቲስት የስነ ጥበብ ተቃውሞ የተነሳ ዮናስ ብርሃነ መዋን ማሰር እና በዋስ የመፈታት መብት መከልከል ሕግን የጣሰ እና ተቀባይነት የሌለው ነው።" የኢሰመኮ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ

በሌላ አርቲስት የስነ ጥበብ ተቃውሞ የተነሳ ዮናስ ብርሃነ መዋን ማሰር እና በዋስ የመፈታት መብት መከልከል ሕግን የጣሰ እና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ገለጹ።

ኮሚሽነር ዳንኤል በፌስቡክ ድረ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ባሳፍነው አርብ ሰኔ 2/2015 በፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋለው የፊልም አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ መዋ ከእስር እንዲለቀቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፤ በሌላ አርቲስት የስነ ጥበብ ተቃውሞ የተነሳ ዮናስ ብርሃነ መዋን ማሰር እና በዋስ የመፈታት መብት መከልከል ሕግን የጣሰ እና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። የአርቲስቷ ስነ ጥበብ ተግባር በነፃነት የመናገር መብት አካል እንደሆነና ዮናስ ብርሃነ መዋ በፍጥነት ከእስር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቅ ሲሉም ጠይቀዋል።

የ"ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ አርብ ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ሥነ ስርዓት በኋላ በመንግሥት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.9K viewsedited  16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 17:56:40
ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው- አቶ ጌታቸው ረዳ

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል የተደረገለት ልዑኩ፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነትና ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባህር ዳር ገብቷል።

የልዑኩ ቡድኑ የተለያዩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮችን ያካተተ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙኸን ዘግበዋል።ልዑኩ በባህር ዳር ከተማ ከአማራ ክልል አመራሮችና ህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል። በውይይቱ ላይ ተገኝተው ለርእሳነ መሥተዳድሮቹ ጥያቄ ያቀረቡ የከተማዋ ነዋሪዎችም የሠላም ግንኙነቱን ዘላቂ ለማድረግ የአመራሩ ቁርጠኝነት ምን ያክል ነው ጠይቀዋል፡፡

ከባለፈው ጥፋት ተምሮ ሥህተትን ማረም ይሻላል ያሉት ነዋሪዎቹ፣ አመራሩ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ምን ያክል ዝግጁ ነው የሚል ጥያቄም አቅርበዋል።ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ለማጥበብ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያለው ቁርጠኝነት፣ እየሄደበት ያለውን ርቀት እና ዝግጁነት ጠይቀዋል፡፡ 

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ዋጋ የማይጠይቅ የሠላም አማራጭ ሳለ በፖለቲከኞች የጠብ ርሃብ ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ተከስተዋል ብለዋል፡፡ 
ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ አሁን የጦርነትን ምዕራፍ ዘግተን የሠላም አማራጮችን የምናይበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ለሠላም አማራጮች ዝግጁ ነው ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
10.6K viewsedited  14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ