Get Mystery Box with random crypto!

ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው- አቶ ጌታቸው ረዳ በአማ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው- አቶ ጌታቸው ረዳ

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል የተደረገለት ልዑኩ፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነትና ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባህር ዳር ገብቷል።

የልዑኩ ቡድኑ የተለያዩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮችን ያካተተ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙኸን ዘግበዋል።ልዑኩ በባህር ዳር ከተማ ከአማራ ክልል አመራሮችና ህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት እያደረገ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል። በውይይቱ ላይ ተገኝተው ለርእሳነ መሥተዳድሮቹ ጥያቄ ያቀረቡ የከተማዋ ነዋሪዎችም የሠላም ግንኙነቱን ዘላቂ ለማድረግ የአመራሩ ቁርጠኝነት ምን ያክል ነው ጠይቀዋል፡፡

ከባለፈው ጥፋት ተምሮ ሥህተትን ማረም ይሻላል ያሉት ነዋሪዎቹ፣ አመራሩ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ምን ያክል ዝግጁ ነው የሚል ጥያቄም አቅርበዋል።ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ለማጥበብ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያለው ቁርጠኝነት፣ እየሄደበት ያለውን ርቀት እና ዝግጁነት ጠይቀዋል፡፡ 

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ዋጋ የማይጠይቅ የሠላም አማራጭ ሳለ በፖለቲከኞች የጠብ ርሃብ ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ተከስተዋል ብለዋል፡፡ 
ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ አሁን የጦርነትን ምዕራፍ ዘግተን የሠላም አማራጮችን የምናይበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ለሠላም አማራጮች ዝግጁ ነው ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news