Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምግብ እርዳታን ላልተፈለገ ዓላማ በማዋል ተሳትፏል መባሉን ሰሞኑን ባ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምግብ እርዳታን ላልተፈለገ ዓላማ በማዋል ተሳትፏል መባሉን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አጣጥሏል።

በምግብ እርዳታ ዝርፊያና ለራስ ጥቅም በማዋል የተሳተፉ የሠራዊቱ ክፍሎች ወይም ተቋማት የሉም በማለት የገለጠው መግለጫው፣ ሠራዊቱ ከተረጅዎች እርዳታ ሊነጥቅ ይቅርና ለእርዳታ ፈላጊዎች እርዳታ ለመስጠት በቂ የሎጂስቲክስ አቅርቦት ያለው ተቋም ነው ብሏል። ሠራዊቱ፣ በድርጊቱ በግለሰብ ደረጃ ተሳትፈው የተገኙ አባላቱ ካሉ ግን ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ሠራዊቱ ይህንኑ መግለጫ ያወጣው፣ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት በውስጥ ምርመራው በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ወታደሮችንና የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመመገብ እንደዋለ ደርሶበታል የሚል ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news