በጎደሬ ወረዳ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አንድ የፖሊስ አዛዥ ተገደለ ከደቡብ ምዕራብ ክልል ሚዛን ከተማ ወደ ጋምቤላ ክልል ማጃንግ ብሔረሰብ ዞን ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ በመጓዝ ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአንድ ፖሊስ አዛዥ ተገድሏል። በጥቃቱ አንድ የፖሊስ አባል ላይ ጉዳት መድረሱን በጋምቤላ ክልል የጎደሬ ወረዳ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳኜ ወርቅነህ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በደቡብ ምዕራብ ክልል የኪ ወረዳ ልዩ ስሙ ባያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ጥቃቱ ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት 30 ደቂቃ አካባቢ ተፈፅሟል። ይህ ግድያ የተፈጸመው የፖሊስ አባላቱ ከደቡብ ምዕራብ ክልል ሚዛን ከተማ ስልጠናቸውን ጨርሰው ወደ ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ በመመለስ ላይ እያሉ ነው ብለዋል።ጥቃቱንም የጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ፈፅመውታል። በጥቃቱ የማጃንግ ብሔረሰብ ዞን የጎደሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ አብዮት ሮኬት ህይወታቸው አልፏል። በሌላ አንድ የፖሊስ አባል ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በቴፒ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል ሲሉ አቶ ዳኜ ወርቅነህ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ድርጊቱን በፅኑ የሚያወግዝ መሆኑን እና አጥፊዎቹም ለህግ እንዲቀርቡ ከፍትህ አካላትና ከሚመለከታቸው ጋር በትብብር እንደሚሰራ ገልፀዋል። @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news 9.8K views06:54