Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_mereja_news — ኢትዮ መረጃ - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.46K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-29 13:23:42
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ #tikvah

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.4K viewsedited  10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 09:19:27
በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያ ውይይቱ ቀጥሏል!

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት ላይ የሚያደርጉት ውይይት እንደቀጠለ ነው፡፡ ድርድሩ፥ በሁለቱ ወገኖች መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ሁከት እና አለመረጋጋት የማስቆም ተስፋ ተጥሎበታል።

በኬንያ እና በኖርዌይ አደራዳሪነት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል፣ ውይይቱ ባለፈው ማክሰኞ የተጀመረው፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በጎሣ ግጭት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ውጥረት እያየለ በመጣበት ወሳኝ ወቅት ነው።

የሰላም ድርድሩ፣ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቀጠለውን ግጭት እና አለመረጋጋት እንደሚያስቆም ተስፋ የሚያደርጉ ብዙዎች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገውን ውይይት በአዎንታ ተቀብለውታል።

በታንዛንያ የውጭ ግንኙነት ማዕከል መምህር እንደኾኑት አባስ ሙዋሊሙ ያሉ ተንታኞች፣ ኹኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ነው። የቅድመ ድርድር ንግግር መጀመሩ፣ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ የሚወስድ ርምጃ ነው፤ ያሉት ግጭቶቹን ሲከታተሉ የቆዩት ሙዋሊሙ፣ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ የበለጠ መሠራት እንዳለበት ያሠምሩበታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ለሰላም ንግግር መቀመጣቸው፣ ግጭቱ እያሳደረ ያለውን ጫና መረዳታቸውን እንደሚያሳይና አሁን በጋራ ችግሩን ለመፍታት ማሰባቸውን እንደኾነ መምህሩ አስረድተዋል፡፡ ንግግራቸው ስኬታማ የመኾን ዕድል እንዳለው ጠቁመው፣ ነገር ግን ሕገ መንግሥቱን ለመከለስና ኢትዮጵያን አንድ በሚያደርግ መልኩ ለማየት ቢመርጡ የበለጠ ስኬት ሊመጣ እንደሚችል መክረዋል፡፡

Via VOA

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.4K viewsedited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:29:04
መረጃ

በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.9K viewsedited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:53:21 ታንዛንያ

ታንዛኒያ 206 ዜጎቿን በኢትዮጵያዋ የጠረፍ ከተማ መተማ በኩል በተሽከርካሪ ከሱዳን ማስወጣቷን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

በመተማ በኩል ከሱዳን ወጥተው በቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ አገራቸው ከተመለሱት ታንዛኒያዊያን መካከል፣ በሱዳን የአገሪቱ አምባሳደር ሲሊማ ሐጂ እና የጉዞ ሰነድ የሌላቸው የአገሪቱ ዜጎች እንደሚገኙበት ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

በመተማ በኩል ከሱዳን የወጡት አብዛኛዎቹ ታንዛኒያዊያን በሱዳን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ናቸው ተብሏል።

ስመ ጥሩ በኾኑት የሱዳን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በርካታ አፍሪካዊያን ተማሪዎች እንደሚማሩ ይታወቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.2K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 15:56:35
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መሪዎች ጋር በስልክ ተወያዩ!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር ኃይሎች መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ።

ታላቁ የሱዳን ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በመግባባት እንዲፈቱ እና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.6K viewsedited  12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 14:22:21 ኢትዮጲያ በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ ግብረ ሃይል አቋቋመች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በዛሬው እለት የሚኒስቴሩን ሳምንታዊ የስራ ማብራሪያና ከጋዜጠኞች ለተናነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሱዳን ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጋር እና ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይሎች መሪ ዳጋሎን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አምባሳደር መለስ አለም ተናግረዋል።

ለሱዳን ህዝብ ሰላም እንዲመጣ ሁለቱ መሪዎች እድል  መስጠት እንደሚያስፈልጋቸው እና የውስጥ ችግር ለመፍታት በቂ አቅም ያላቸው ስለመሆናቸው  በስልክ ውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  ተናግረዋል።ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተየያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ ሃይል መኖራቸውን ባለሙያዎች እስከ ጋራ ድንበር ተልከው እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር መለሰ ተናግረዋል።

ግጭቱ ኢትዮጵያ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዜጎች ካሉ በምን መልኩ እናስተናግድ በሚል እና ዜጎች የቆንስላ አገልግሎት እያገኙ ወደሃገራቸው እንዲመጡ ግብረ ሀይሉ ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል።ሱዳን ውስጥ ከ 100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አሉ ሁሉም ዜጎች ሰላም እንዲሆኑ እንሰራለን ብለዋል። እስካሁን በ100 የሚቆጠሩ  የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ከሱዳን በኢትዮጵያ ስለማለፋቸውም ጨምረው ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
11.3K viewsedited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 08:50:25 አብን

አብን በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈጸመው ግድያ "የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል የዜሮ ድምር ፖለቲካዊ ሽብር ውጤት" መኾኑን ገልጧል።

አብን ቀደም ሲል በክልሉ አመራሮች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል "ተሸፋፍኖ መቅረቱና ተጠያቂነት አለመስፈኑ"፣ አኹንም የአመራሮች ግድያ "ተባብሶ እንዲቀጥል" ምክንያት መኾኑን አምናለኹ ብሏል።

አብን ግድያው ሳይጣራና የገዳዮች ማንነት ሳይታወቅ፣ ከድርጊቱ "ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት ሲባል በአደባባይ የሚደርጉ ፍረጃዎችንና መግለጫዎችን" እንደሚያወግዝም ገልጧል።

የግድያው ፈጻሚዎች ማንነት እንዲጣራና ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አብን ጨምሮ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.2K views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 07:50:17 የአማራ ክልላዊ መንግሥት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል ግርማ የሺጥላ በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጓሳ በተባለ አካባቢ የተገደሉት "በታጠቁ ጽንፈኛ ኃይሎች" ነው ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

"የጽንፈኛ ኃይሎችን የሽብር ድርጊት" ለማስቆም ርምጃ እንደሚወስድ የገለጠው የክልሉ መንግሥት፣ የግድያውን ፈጻሚዎች ለፍርድ አቀርባለኹ በማለት ቃል ገብቷል።

ግርማ የተገደሉት፣ ከመንግሥትና የድርጅት ሥራ መልስ ከመሃል ሜዳ ከተማ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ሲጓዙ እንደኾነ የክልሉ መንግሥት ጨምሮ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.1K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 22:29:04
"የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል" - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በ2015 ዓም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚመለከት ውይይት አካሄዷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡በ2016 ዓ.ም የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸዋል ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል።

[የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት]

@sheger_press
@sheger_press
13.0K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 20:40:47
እስካሁን የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል!

የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በአቶ ግርማ የሺጥላ እና በግል ጥበቃዎቻቸው በተፈፀመ ጥቃት እስካሁን የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ጥቃቱ የተፈፀመው ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን እየመጡ በነበረበት ሰዓት መንዝ ጓሳ መሆኑን ለማረጋገጠት ችለናል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
12.4K viewsedited  17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ