Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጲያ በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ ግብረ ሃይል አቋቋመች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ኢትዮጲያ በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ ግብረ ሃይል አቋቋመች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በዛሬው እለት የሚኒስቴሩን ሳምንታዊ የስራ ማብራሪያና ከጋዜጠኞች ለተናነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሱዳን ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጋር እና ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይሎች መሪ ዳጋሎን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አምባሳደር መለስ አለም ተናግረዋል።

ለሱዳን ህዝብ ሰላም እንዲመጣ ሁለቱ መሪዎች እድል  መስጠት እንደሚያስፈልጋቸው እና የውስጥ ችግር ለመፍታት በቂ አቅም ያላቸው ስለመሆናቸው  በስልክ ውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  ተናግረዋል።ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተየያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ ሃይል መኖራቸውን ባለሙያዎች እስከ ጋራ ድንበር ተልከው እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር መለሰ ተናግረዋል።

ግጭቱ ኢትዮጵያ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዜጎች ካሉ በምን መልኩ እናስተናግድ በሚል እና ዜጎች የቆንስላ አገልግሎት እያገኙ ወደሃገራቸው እንዲመጡ ግብረ ሀይሉ ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል።ሱዳን ውስጥ ከ 100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አሉ ሁሉም ዜጎች ሰላም እንዲሆኑ እንሰራለን ብለዋል። እስካሁን በ100 የሚቆጠሩ  የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ከሱዳን በኢትዮጵያ ስለማለፋቸውም ጨምረው ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news