Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያ ውይይቱ ቀጥሏል! የኢትዮጵያ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያ ውይይቱ ቀጥሏል!

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት ላይ የሚያደርጉት ውይይት እንደቀጠለ ነው፡፡ ድርድሩ፥ በሁለቱ ወገኖች መካከል ለዓመታት የዘለቀውን ሁከት እና አለመረጋጋት የማስቆም ተስፋ ተጥሎበታል።

በኬንያ እና በኖርዌይ አደራዳሪነት፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል፣ ውይይቱ ባለፈው ማክሰኞ የተጀመረው፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በጎሣ ግጭት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ውጥረት እያየለ በመጣበት ወሳኝ ወቅት ነው።

የሰላም ድርድሩ፣ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቀጠለውን ግጭት እና አለመረጋጋት እንደሚያስቆም ተስፋ የሚያደርጉ ብዙዎች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገውን ውይይት በአዎንታ ተቀብለውታል።

በታንዛንያ የውጭ ግንኙነት ማዕከል መምህር እንደኾኑት አባስ ሙዋሊሙ ያሉ ተንታኞች፣ ኹኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ ነው። የቅድመ ድርድር ንግግር መጀመሩ፣ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ የሚወስድ ርምጃ ነው፤ ያሉት ግጭቶቹን ሲከታተሉ የቆዩት ሙዋሊሙ፣ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ የበለጠ መሠራት እንዳለበት ያሠምሩበታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ለሰላም ንግግር መቀመጣቸው፣ ግጭቱ እያሳደረ ያለውን ጫና መረዳታቸውን እንደሚያሳይና አሁን በጋራ ችግሩን ለመፍታት ማሰባቸውን እንደኾነ መምህሩ አስረድተዋል፡፡ ንግግራቸው ስኬታማ የመኾን ዕድል እንዳለው ጠቁመው፣ ነገር ግን ሕገ መንግሥቱን ለመከለስና ኢትዮጵያን አንድ በሚያደርግ መልኩ ለማየት ቢመርጡ የበለጠ ስኬት ሊመጣ እንደሚችል መክረዋል፡፡

Via VOA

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news