Get Mystery Box with random crypto!

ታንዛንያ ታንዛኒያ 206 ዜጎቿን በኢትዮጵያዋ የጠረፍ ከተማ መተማ በኩል በተሽከርካሪ ከሱዳን ማ | ኢትዮ መረጃ - NEWS

ታንዛንያ

ታንዛኒያ 206 ዜጎቿን በኢትዮጵያዋ የጠረፍ ከተማ መተማ በኩል በተሽከርካሪ ከሱዳን ማስወጣቷን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

በመተማ በኩል ከሱዳን ወጥተው በቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ አገራቸው ከተመለሱት ታንዛኒያዊያን መካከል፣ በሱዳን የአገሪቱ አምባሳደር ሲሊማ ሐጂ እና የጉዞ ሰነድ የሌላቸው የአገሪቱ ዜጎች እንደሚገኙበት ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

በመተማ በኩል ከሱዳን የወጡት አብዛኛዎቹ ታንዛኒያዊያን በሱዳን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ናቸው ተብሏል።

ስመ ጥሩ በኾኑት የሱዳን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በርካታ አፍሪካዊያን ተማሪዎች እንደሚማሩ ይታወቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news